Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከክፍተት ያልራቀው የወር አበባ ጤናና ንጽሕና አጠባበቅ

ከክፍተት ያልራቀው የወር አበባ ጤናና ንጽሕና አጠባበቅ

ቀን:

በልጃገረዶች ላይ በአማካይ ከ11 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ድረስ የሚከሰተውና እንደየእንስቷ እስከ 55 ዓመት ድረስ የሚቆየው የወር አበባ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ለሴቶች ፈተና ነው፡፡ ስለክስተቱ መረጃን ከማግኘት አንስቶ እንዴት ንፅህናን መጠበቅ እንደሚቻል አለመገንዘብና አቅም ማነስ በተለይ የአፍላ ልጃገረዶች ችግር ነው፡፡

ልጃገረዶችና ሴቶች የወር አበባ በታያቸው ቁጥር የንፅህና መጠበቂያዎች ተደራሽ ሊሆንላቸውና ስለክስተቱም መረጃ ሊኖራቸው ቢገባም ይህ ክፍተት አለበት፡፡  

ችግሩ ዓለም አቀፋዊ በመሆኑ በዓመት አንድ ቀን በወር አበባ ጤናና የግል ንፅህና አጠባበቅ ላይ የማስገንዘቢያና የማነቃቂያ ሥራዎች እንዲከናወኑ ተደርጓል፡፡ በዚህም የተነሳ በዓለም ለስምንተኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ ይኸው ቀን በዓውደ ጥናት ታስቦ ውሏል፡፡

‹‹ለወር አበባ ንጽህናና ጤና ተጨማሪ ኢንቨስትመንት የማድረጊያ ጊዜ አሁን ነው፤›› በሚል መሪ ቃል በበይነ መረብ በተካሄደው በዚሁ ዓውደ ጥናት፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጀ ድጉማ (ዶ/ር) የወር አበባ የተፈጥሮ ክስተት ሆኖ ሳለ በወር አበባ ምንነትና ንጽሕና አጠባበቅ ላይ ከግንዛቤ ውስንነት አኳያ በርካታ ችግሮች እንደተከሰቱ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ጥናቶችን ዋቢ አድርገው እንዳብራሩት፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ ባለው የተዛቡ አመለካከቶች እንዲሁም በቤተሰብና በትምህርት ቤት ማኅበረሰብ ውስጥ ግልጽ ውይይት አለመኖርና በሌሎች በርካታ ተያያዥ ችግሮች ሳቢያ የሚፈጠረው መገለልና ኃፍረት በልጃገረዶች ጤናና ሥነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው፡፡

የሴቶች ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ፣ ሴቶች የወር አበባቸውን ምቹ በሆነ ሁኔታ ማስተናገድ ካለመቻል፣ እንዲሁም በጓደኞቻቸውና በትምህርት ቤት ማኅበረሰብ የሚደርስባቸውን መገለል ሽሽት ከትምህርት ገበታቸው እንደሚቀሩ፣ አልፎም እንደሚያቋርጡ፣ በዚህም ምርታማነትና ተወዳዳሪነታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚኖረው ችግሩን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በኅብረት እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በበኩላቸው የንፅህና መጠበቂያዎችና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ወደ ትምህርት ቤቶች የማዳረስና የማስፋት ሥራዎች እንደሚሠሩና ይህ ዓይነቱም ሥራ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የሥነ ልቦና ችግር ከትምህርት ገበታቸው የመቅረት አደጋን በመጠኑም ቢሆን ሊያቀል ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የወር አበባ መጠበቂያ አምራች ድርጅቶች አነስተኛ በመሆናቸው፣ ምርቶቹን በአገር ውስጥ ለማቅረብና አምራቾችን ለማበረታታት የቀረጥና ታክስ ማሻሻያዎችን በማድረግ ምርቱን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ያመለከቱት ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሀስሚን ወሀብረቢ ናቸው፡፡

የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት የፕሮግራሞች ዳይሬክተር ወ/ሮ ብሌን ወርቁ የሴቶች ንጽህና አጠባበቅን አስመልክቶ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የወር አበባ ቀን በየዓመቱ በግንቦት ወር በተለያዩ መሪ ቃሎች፣ በማኅበረሰብ ዘንድ ያሉ የተዛቡ አመለካከቶችን በሚቀይሩና ግንዛቤን በሚያሳድጉ ሥራዎች እንደሚከበር በጤና ሚኒስቴር የሀይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢክራም ሬድዋን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...