Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለስኬት የበቁት ኢንተርፕራይዞች

ለስኬት የበቁት ኢንተርፕራይዞች

ቀን:

‹‹የታፈረች፣ የምትደመጥና ተፅዕኖ ፈጣሪ አገር ዕውን ይደረግ ከተባለ ዋነኛው መንስዔ በኢኮኖሚ መጠናከር፣ የማይናወጥና የማይንበረከክ አቅም መገንባት በእጅጉ ያስፈልጋል፤›› ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት ለስኬት ለበቁ ኢንተርፕራይዞች በታላቁ ቤተ መንግሥት ዕውቅና በተሰጠበት አጋጣሚ ነው፡፡

ስኬታማ አገልግሎታቸውን ጨምረው የሥራ ወኔያቸውን ሰንቀው መንግሥት ባመቻቸላቸው ሥርዓትና ድጋፍ ታግዘው ድህነትን ለመሻገርና ለስኬት ለበቁት ኢንተርፕራይዞች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹ጉዞአችን አሁንም ይቀጥላል፡፡ አገራችን አሁንም ሥራ ላይ ናት፡፡ ባለፉት ዓመታት የተጓዝንበት አገራዊ የለውጥ ጉዞ ከብልፅግና ከፍታ ላይ እንዳይወጣ የሚያግደን አንዳችም ኃይል እንደማይኖር አይተናል፡፡ በጅምራችን ያገኘነው ውጤት ለላቀ የሥራ ሥምሪት ስንቅ እንደሚሆነን በማሰብ በአንድነት እንሥራ›› ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢንተርፐራይዞች ካሰቡት ለመድረስ ምንም የሚያግዳቸው ነገር እንደማይኖር እስካሁን የመጡበትም የፅናት ፍኖት ለተሻለ ስኬት ስንቅ እንደሚሆናቸውም ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣ በ11 ከተሞች ብቻ ተወስኖ የነበረውና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችለው የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት በአሁኑ ጊዜ ወደ 83 ማደጉንና በዚህም የተጠቃሚዎች ቁጥር ከ800,000 በላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት 10 ወራት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው፣ ባጠቃላይ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠናክሮ ከቀጠለ በርካታ ወጣቶችን ወደ ሥራ ለማሰማራት እንደሚቻል ዋና ዳይሬክተሩ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በትጋታቸው፣ በታታሪነታቸውና በመልካም ሥራቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 106 ኢንተርፕራይዞች ዕውቅና፣ ድጋፍና የአቅም ግንባታ ከማግኘታቸውም ወደ መካከለኛ ባለሀብትነትም እንደተሸጋገሩ ነው ያመለከቱት፡፡

የኢንተርፕራይዞች ለሽልማት መብቃት ሠርቶ መለወጥንና ወደ ባለሀብትነት ደረጃ ለመሸጋገር የሚያስችል መሆኑን ያመለከቱት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢንጂነር) ተሸላሚዎቹም በዚህ ሳይዘናጉ ከመቼውም ጊዜ በላይ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ቆርጠው መነሳሳት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የአሥር ዓመቱ መሪ ዕቅድም በከተማ ልማት ሰፊ የሥራ ዕድል ማመቻቸት በተቀዳሚነት እንዳስቀመጠ፣ ይህም በከተሞች የሚታየውን የሥራ አጥነትን ችግር ትርጉም ባለው መንገድ እንደሚፈታና ወደ ብልፅግና ማማ እንደሚያሸጋግር ነው የጠቆሙት፡፡

በዳግማዊ ምኒልክ የግብር አዳራሽ በተከናወነው በዚሁ ሥነ ሥርዓት ላይ የአቅም ግንባታ፣ ድጋፍና ዕውቅና የተቸራቸው የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች፣ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና፣ እንዲሁም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት፣ የላቀ ውጤት ያስመገቡ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች፣ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ ደረጃ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ናቸው፡፡

በዚህም መሠረት የተሻለ አፈጻጸም ከተቀዳጁት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት መካከል የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ፣ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ አንደኛ፣ የኦሮሚያ ቴክኒክና ትምህርት ሥልጠና ቢሮ ሁለተኛ፣ የአማራ ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ሦስተኛ ሆነዋል፡፡

ከሞዴል ኢንተርፕራይዞች መካከል ደግሞ የኦሮሚያ፣ የአማራና የአዲስ አበባ ብድርና ቁጠባ ተቋማት እንደየቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ወጥተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...