Tuesday, March 28, 2023

ሱዳን ከህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር በተገናኘ ቀረኝ የምትለው አጀንዳ እንደሌላት ተገለጸ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

ከህዳሴ  ግድብ  የሦስትዮሽ ድርድር ጋር በተገናኘ  ሱዳን  ለግብፅ  ከምትፈጽመው  የተልዕኮ  ሚና  በስተቀር፣  ቀረኝ  የምትለው  አጀንዳ  እንደሌላት   የውጭ ጉዳይ  ሚኒስቴር  አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ  (አምባሳደር)  በሳምንታዊ  ጋዜጣዊ  መግለጫቸው፣  በሱዳን  በኩል  ሲነሳ  የነበረው  ኢትዮጵያ  በግንባር  ቀደምትነትና በኃላፊነት  ለምትገነባው ግድብ  ለሚኖረው የደኅንነት  ሥጋት  መረጃዎችን  ለማቅረብና  የግድቡን  ሁኔታ  በቅርብ  እንዲመለከቱ  ሁኔታዎች  እንደሚመቻችላቸው ለሱዳንም ለግብፅም ተነግሯቸዋል  ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በመጫወቻ  ሜዳ  ላይ  ያለው  ኳስ  ግድቡ  ሆኖ  እያለ  ሱዳን  በኢትዮጵያ  ላይ የፈጸመችው   ድንበር  አልፎ  የመግባት  እንቅስቃሴ   ከኋላ  ሆና የምትገፋፋውን  ግብፅ  አጀንዳ  ለማስፈጸም መሆኑን፣  የሚሰማውን  ሁካታ  ሁሉ  ላለማስተናገድ  ኢትዮጵያ  ሁሉንም  ነገር  በውይይት  እንፍታ  እያለች እየጠየቀች እንደሆነ ቃል  አቀባዩ  ተናግረዋል።

ከዓለም አቀፉ  ማኅበረሰብ   በተለይም  አንዳንዱ  ወገን  ኢትዮጵያ  በውስጥ  የሕግ  የበላይነትን  ለማስከበር  የምታደርገውን  ጥረት  ሲያብጠለጥል  ውሎ እያደረ፣  በሌላ  በኩል  የኢትዮጵያ  መሬት  ሲወረር  ዝም  እንዳለና  ይህም  ትክክል  እንዳልሆነ  መንግሥት እየተናገረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሱዳን በውክልና  የምታደርገውን  እንቅስቃሴ  ምክንያት  ላለመስጠት  ስትል  ብቻ  ከኋላ  በሚገፋት  ኃይል  ከኢትዮጵያ  መጋጨቷን፣ በዚህም ከድንበር ጋር ተያይዞ  ኢትዮጵያ  እያሳየችው  ያለው  አቋም  የፍርኃት  ወይም  ያለማወቅ  ሳይሆን  አዋጭ  ባለመሆኑ  ነው  ሲሉ ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ   ኢትዮጵያ  ግድቡን  ከመሙላት  የሚያስቆማት ኃይል ምንም  ነገር  እንደሌለ፣  መሙላት  በፈለገችበት  ጊዜ  ወቅቱን  ጠብቃ  እንደምትሞላ  አስታውቀዋል፡፡

ግብፆች  በተደጋጋሚ  ከሚያነሱት  የአራትዮሽ  ድርድር  ኢትዮጵያ  ለምን  አፈገፈገች?  ግብፆችስ  ለምን  ፈለጉት?  ለሚለው  የሪፖርተር  ጥያቄ  ቃል  አቀባዩ ሲመልሱ፣  ኢትዮጵያ  ለአራትዮሽ  ድርድር  ችግር  እንደሌለባትና ምንም  እንደማይጎዳት፣  ነገር  ግን  ለምሥረታው  ትልቅ  አስተዋጽኦ  ላበረከተችለት  አኅጉራዊ ድርጅት  የአፍሪካ  ኅብረት   አክብሮት  አላት  ሲሉ ምክንያቱን  ገልጸዋል።

ከዚህ  ባለፈ  በአፍሪካ  ኅብረት  እየተካሄደ   ያለው  ድርድር  ውጤታማ እንደሆነ፣  በተለይም  በቴክኒክና በሕጋዊ  ጉዳዮች  ላይ  ከሞላ  ጎደል  መልካም የሚባል ውጤት  እንደመጣ  ተናግረዋል፡፡  

ከግብፅ  በኩል  መስማማት  ያልተቻለባቸውና  በዋናነት  ችግር  የፈጠረው  ጉዳይ፣   ኢትዮጵያ  የግድቡን  ሙሌት  በተመለከተ ዝግጁ ብትሆንም  ከግብፅ  በኩል ፍላጎት  አለመኖሩን  እንደሆነ  አመላክተዋል፡፡

‹‹የግብፅ  የምንጊዜም  አቋም  አስገዳጅ  በሆነ  ሕግ  ንብረትነቱ  የኢትዮጵያ  የሆነውን  ሀብት  ውሰዱት  ብለን  እንድንፈርም  የሚያደርግ፣  የኢትዮጵያን  የወደፊት  የተፋሰሱን  አጠቃቀም  ጭምር  የሚዘጋና  የመጪውን  የኢትዮጵያ  ትውልድ የሚጎዳ   አካሄድ  ውስጥ  እንድንገባ  የሚፈቅድ  አሠራር  እንድንፈቅድ ፍላጎቷ፤›› ነው ብለዋል፡፡

ነገር  ግን  የአራትዮሽ  ድርድሩን  የኢትዮጵያ  መንግሥት  አለመቀበሉ  ፍርኃት  ወይም  ንቀት   አለመሆኑን፣  ከግብፅ  በኩል  የሚታየው  ዋነኛ  ፍላጎት  ከእውነታ የራቀና  ድርድሩን  ወደ  አራትዮሽ  በመውሰድ  ዓለም አቀፍ  ሥጋት  ለማስመሰል  እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ግብፆች እስካሁን  በተካሄዱት  ድርድሮች  ዘጠኝ  ጊዜ  ሲገቡና  ሲወጡ  አንድም  ጊዜ   ሀቀኛ  ሆነው  እንዳልቀረቡ፣   ለማስመሰል  ብቻ   ምክንያት  እየፈጠሩ ሲወጡና ሲገቡ እንደነበር ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -