Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቅድመ መደበኛ መምህራንን የሚያሠለጥን የልቀት ማዕከል ሊቋቋም ነው

የቅድመ መደበኛ መምህራንን የሚያሠለጥን የልቀት ማዕከል ሊቋቋም ነው

ቀን:

በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ ብቁ መምህራንን ለማፍራት የሚያስችል የልቀት ማዕከል (ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ) ለማቋቋም፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ገለጹ፡፡

የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ፕሮግራም ፖሊሲን አስመልክቶ አስተባባሪው አቶ ጃንጥራር ዓባይ መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደገለጹት፣ በከተማ ደረጃ የሚቋቋመው ይህ የልቀት ማዕከል የሚገነባው በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ አማካይነት ነው፡፡

ለዚህም አገልግሎት የሚውል ትምህርት ቤት እንደተለየ፣ እስካሁን ድረስ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህራን የተወጣጡት ከፍ ብሎ ከተጠቀሰው ማዕከል ሳይሆን ከመደበኛ መምህራን እንደሆነ ነው አቶ ጃንጥራር የተናገሩት፡፡

የፕሮግራሙ ዓላማ ከዜሮ እስከ ስድስት ዓመት የሆናቸው ሕፃናት በአስተሳሰብ የበለፀጉ ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ የታሰበና የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፣ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ፕሮግራም ተግባራዊ የሚሆነው በጉዳዩ ላይ ዕውቀትና የሀብት ድጋፍ ከሚያደርጉ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀደም ብሎ ሲሠራበት እንደቆየ፣ ነገር ግን የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዳልነበረው፣ አሁን ግን ጤና ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፖሊሲ እንዳዘጋጀ ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ብቁ የሆነ ካሪኩለም ቀርፃ የሚከናወን መሆኑን፣ ካሪኩለሙን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ግብዓት የማሟላት፣ መምህራን የመመደብና የማዘጋጀት ሥራ በቀጣይ እንደሚከናወን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

እንደ አቶ ጃንጥራር ማብራሪያ ፕሮግራሙ በትምህርት ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን፣ በትምህርትና ከትምህርት ውጭ ለሚገኙ ሕፃናት የአልሚ ምግብ፣ አገልግሎት የማቅረብ፣ እንዲሁም የመጫወቻና የመዝናኛ ሥፍራዎችን በመንግሥትና በማኅበረሰቡ ትብብር የማሟላት ሥራን ያካትታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...