Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

አዲሱ የሰላም እና አንድነት ሽልማት

በወጣቶች፣ በሰላምና አንድነት እንዲሁም በበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በመሰማራት ይታወቃል፡፡ በተለይ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች ግጭት ወቅት ለተፈናቀሉና ንብረትና ቤታቸውን ላጡ ነዋሪዎች ‹‹ወገን ለወገን›› የሚልምቦላን አዘጋጅቶ በርካቶችን ለመታደግ ችሏል፡፡ በቅርቡም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ዕውቅና አግኝቶ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አገር አቀፍ የሰላምና የአንድነት አምባሳደር ሽልማትን እያሰናዳ የሚገኘው ኢስት አፍሪካ ኢንተርተይመንትና ኢቨንት ነው፡፡ ተቋሙ እያከናወነ ስላለው ተግባርና ስለሰላምና አንድነት አምባሳደር ሽልማትዋና አስኪያጁ አቶ ሞቲ ሞረዳ ጋር ዳዊት ቶሎሳ ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡

ሪፖርተር፡- የድርጅታችሁ ዋና ተግባርና እንቅስቃሴ ምንድነው?

አቶ ሞቲ፡- ድርጅቱ የግል ድርጅት ነው፡፡ የግል ድርጅት የሚገለጽበት የራሱ የሆነ ተግባር አለ፡፡ ይኼም ነግዶ ለማትረፍ እንዲሁም ካተረፈው ትርፍብረተሰቡንና አገሩን ማገልገል ነው፡፡ የእኛ ግን ለየት የሚያደርገው ጥቂት አትርፎ አብዛኛውን በወጣቶች፣ በሰላምና አንድነት ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት ነው፡፡ ስለዚህ የእኛ ዋናላማ ወጣቱና ማኅበረሰቡ ላይ በመሥራትአገሪቷ ሰላምና አንድነትን ማስጠበቅ ነው፡፡ ይኼም ማለት እኛ የበኩላችንን ከተወጣን፣ ሌላውም ከራሱ ተነስቶ የበኩሉን ይወጣል በሚል ነው፡፡ ንግድ ወይም ትርፍ ከሰላም ቀጥሎ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ሰዓት ሰላምና ደኅንነት ነው የሚያስፈልጋት፡፡

ሪፖርተር፡- ስላከናወናችሁት መርሐ ግብሮች ቢገልጹልን፤

አቶ ሞቲ፡- በርካታ መርሐ ግብሮችን አሰናድተናል፡፡ ከዚህ መካከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማታቸውን ተቀብለው ወደ አገር ቤት ሲመለሱ የተለየዩ ተሸከርካሪዎችን በማዘጋጀትና ወጣቱን እንዲሁም ማኅበረሰቡን በመቀስቀስ ደማቅ አቀባበል እንዲደረግላቸው አድርገናል፡፡ ይኼም ዋናው ትኩረቱ የነበረው ወጣቱ ትውልድ ሰው በስኬቱ ሽልማት ሲጎናጸፍ፣ ማድነቅና ዋጋ መስጠትን እንዲማር በማሰብ ነው፡፡ ሌላው የአረንጓዴ አሻራ በተመለከተም እኔ ባቋቋምኩት ቪዥን ብራይት በተሰኘ በጎ አድራጎት ላይ በሚሠራ ተቋም፣ አዲስ አበባ ላይ 5000 በላይ ወጣት በማደራጀት የችግኝ ተከላ በሁሉም ክፍላተ ከተማ ማከናወን ችለናል፡፡

ሌላው 2011 .ም. በኢሬቻ ክብረ በዓል ዋዜማ በሚሌኒየም አዳራሽ ብሔር ብሔረሰቦች የተሳተፉበት ወይዘሪት ፊንፊኔ የተሰኘ የቁንጅና ውድድር አከናውነናል፡፡ በዕለቱም ክበረ በዓሉን ለመታደም የመጡትን ከአንድ ሺሕ በላይ እንግዶች ማደሪያ፣ ምግብና የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ማስተናገድ ችለናል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደ አገራችን ገብቶ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ማንኛውም ስብሰባዎች እንዳይደረጉ ተብሎ በታወጀ በማግስቱ ከሁለት ሺሕ በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ በአሥሩ ክፍላተ ከተማናክልል ከተሞች ውኃ፣ ሳኒታይዘር እንዲሁም ሳሙና ለማኅበረሰቡ ስናቀርብ ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- ድርጅታችሁ ለትርፍ ከሚሠራው በተጨማሪ በዋነኛነት እየሠራ ያለው ምንድነው?

አቶ ሞቲ፡- ድርጅቱ ከሚሠራው 80 በመቶ የሚሆነው ለአገሪቷ ምን ፋይዳ ይኖረዋል የሚለውን በቀዳሚነት ይመለከታል፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረ ፕሮጀክት ላይ አይሠራም፡፡ ከበጎ አድራጎትና ከሰላም ጋር የተገናኙ አዳዲስ ሐሳቦች ላይ ትኩረቱን አድረጎ የሚሠራ ነው፡፡ አገራችን አሁን ካለችበት የሰላም ሁኔታ አንጻር ወጣቶች ምን ይጠበቅባቸዋል የሚለው ላይ በሰፊው እየሠራን እንገኛለን፡፡ ዘንድሮ የሰላምና የአንድነት አምባሳደር ሴቶች ላይ ትኩረትን አድርገን ለመሥራት፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ንድፈ ሐሳብ አውጥተን ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ ምክር ቤቱም ጥያቄያችንን ተቀብሎን ፈቃድ ከሰጠን በኋላሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በትብብር እንድንሠራ ማድረግ ችሏል፡፡ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተመረጡ ምርጥ ሦስት የሰላምና የአንድነት አምባሳደሮች ኅዳር 27 እና 29 ጠቅላይ ሚኒስትሩና ፕሬዚዳንቷ በተገኙበት፣  የሃይማኖት አባቶችና ሚኒስትሮችም በታደሙበት የአንድነት ፓርክ ላይ ዕውቅና ተሰጥቷቸው የሰላም እንዲሠሩ አድርገናል፡፡

ሪፖርተር፡- በአገር አቀፍ ደረጃ የምታከናውኑት ሽልማት ዝግጅታችሁ ምን ይመስላል?

አቶ ሞቲ፡- አገር አቀፉ የሰላምና አንድነት የበጎ ሰው ሽልማቱ ‹‹ጎህ ሰላምና አንድነት የበጎ ሰው ሽልማት›› የሚል ስያሜ ያነገበ ነው፡፡ በጭላንጭል የታየችውን የሰላም ተስፋ እናስፋት የሚል ትርጓሜን ይዟል፡፡ ሽልማቱአገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወን ሲሆን አገሪቷ ባልተረጋጋችበት ወቅት፣ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦችን የሚሸለም ነው፡፡ ሰለዚህ እነዚህ አካላት የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች፣ ግለሰቦች ወይም ታዋቂ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዋናው ግብ ግን እነዚህ አካላት መመስገን ይኖርባቸዋል የሚል ነው፡፡ ከዚህ ተግባርም ወጣቱ ለአገር ሰላምና አንድነት መሥራት እንደሚያሰመሰግን እና እንደሚያሸልም እንዲማር በማሰብ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ለሰላምና አንድነት የሠሩ በርካታ አካላት አሉ፡፡ ሽልማቱ ክርክር ሳይፈጥር ለማከናወን ምን ዓይነት ዝግጅት አድርጋችኋል?

አቶ ሞቲ፡- ውድድሩ ላይ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ሲሆን በሰላም ላይ የሠሩ አካላት እንዲወዳደሩ ይደረጋል፡፡ ውድድሩ በሕዝቡ፣ በመንግሥት አካላት እንዲሁም በሰላም አስተዳደሮች ዕውቅና ይካሄዳል፡፡ የውድድሩ መሥፈርት፣ በሰላም ዙሪያ የሠራ፣ በበጎ አድራጎት የተሰማራ፣ የተጣላ ጎሳን ያስታረቀ፣ እንዲሁም ሕዝቡ የሚያውቀው መሆን ይኖርበታል፡፡ ይኼን ጉዳይ የሚከታተል ኮሚቴ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አዋቅረናል፡፡ ኮሚቴውም ከመንግሥት ጋር በጋራ ሆኖ ግለሰቡ ምን እንደሠራ አጥንቶና ገምግሞ በጽሑፍ ያቀርባል፡፡ዝቡም በጽሑፍ መልዕክትምፁን እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ስለዚህ ከመላ አገሪቷ የተመረጡት ግለሰቦች፣ አሸናፊዎች እርስ በራስ ይወዳደሩና መጋቢት 26 ቀን 2013 ዓ.ም.ሸራተን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት 2013 .ም. የሰላምና አንድነት አምባሳደር በመባል ሙሉ ዕውቅናና ሽልማት ይበረከትላችዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ከሰላምና አንድነት ሽልማቱ ባሻገር ወጣቶቹን ለማሳተፍ ምን የታቀደ ነገር አለ?

አቶ ሞቲ፡- መጋቢት 26 ላይ የሚከናወኑ ሌሎች መርሐ ግብሮችም አሉን፡፡ አንደኛው በሸራተን አዲስ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የኖቤል ሽልማትስተኛመቱን በማስመልከት የሚከበር ነው፡፡ በዕለቱም ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ አንድ ሴት አንድ ወንድ ሆነው ሽልማትና ‹‹የተሻለች አገር ከአንተ እንጠብቃለን›› የሚል አደራ የመስጠት መርሐ ግብር ይከናወናል፡፡

ሌላኛው ሁሉንምብረተሰብ የሚያሳትፍ ‹‹ለሰላም እሮጣለሁ፣ የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ›› በሚል መሪ ቃል መነሻና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ ሁሉም የከተማው ነዋሪ በነፃ የሚታደል ባንዲራ አንግቦ ለሰላም ይሮጣል፡፡ ይኼ ውድድር በየዓመቱ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ተዛማጅ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች ለማግኘት

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

በኦሮሚያ ክልል በስድስት ከተሞች የተዋቀረውን ሸገር ከተማን የማደራጀት ሥራ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ስድስት ከተሞች የተዋቀረው ሸገር ከተማን...

የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ አልባ በማድረግ ታሪክ አይሠራም

በኢተፋ ቀጀላ​​  ከዛሬ ሃምሳ ዓመት ወዲህ ከተፈጠሩት የኦሮሞ ድርጅቶች መካከል ከኢጭአት በስተቀር፣...

ኢትዮጵያ በትክክለኛ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሕገ መንግሥት ማበጀት እንደሚገባት ማሳሰቢያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ለተለያዩ ጥያቄዎችና ሐሳቦች...

 የክልሎች ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በመከላከያ ሠራዊት ተጠባባቂ ኃይል እንዲካተቱ ጥናት እየተደረገ ነው

የክልሎችን ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በአገር መከላከያ ሠራዊት ተጠባባቂ ኃይል...