Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበትግራይ ክልል በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች ምርመራ እንዲፋጠን ተጠየቀ

በትግራይ ክልል በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች ምርመራ እንዲፋጠን ተጠየቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ተጠርጣሪዎች፣ የወንጀል ምርመራቸውን በተቻለ ፍጥነት እንዲጠናቀቅና የሕግ አግባብ በሚፈቅደው መሠረት ሊለቀቁ የሚገባቸው ታሳሪዎች እንዲለዩ አሳሰበ፡፡

ኮሚሽኑ ማክሰኞ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ከተያዙ በኋላ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የቆዩ እንዳሉ፣ በትግራይ ክልል ከመቀሌ ሸሽተው ሲሄዱ በተያዙበት ጊዜ ስድብ፣ ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ተኩስ እንደነበርና የአካል መቁሰል እንደ ደረሰባቸው ከታሳሪዎቹ መረጃ ደርሶኛል ሲል ገልጿል፡፡

በተጨማሪም  ከትግራይ ክልል ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ነፃ ሆኖ የመገመት መብታቸውን በሚጋፋ ሁኔታ በሚዲያ በማቅረብ ‹‹ማንኳሰስ ተፈጽሞብናል›› ማለታቸውን አያይዞ ገልጿል፡፡

- Advertisement -

በዚህም አብዛኞቹ ታሳሪዎች የቀረበባቸው ክስ ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ፣ የተጠረጠሩበት ጉዳይ በተናጠል አለመቅረቡንና የምርመራ ሒደቱም በአፋጣኝ አለመታየቱን አቤቱታ ከታሳሪዎቹ አቤቱታ እንደደረሰው ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የተወሰኑ ታሳሪዎች የራሳቸውና የቤተሰቦቻቸው የባንክ ሒሳብ በመታገዱ፣ ቤተሰቦቻቸው መቸገራቸውን ነግረውኛል ሲል አክሎ ገልጿል፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እና የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በሚገኘው እስር ቤት፣ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. የታሳሪዎች አያያዝ ማየታቸው በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በጉብኝቱ በትግራይ ክልል ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ 21 ታሳሪዎች የሚገኙበትን የእስር ሁኔታ፣ ከታሳሪዎቹና ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ለአብነትም አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ ዓባይ ወልዱ (አምባሳደር)፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባዲ ዘሙ (አምባሳደር)፣ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ሰሎሞን ኪዳኔ (ዶ/ር)፣ ኦዲስዓለም ባሌማ (አምባሳደር)፣ ሜጀር ጄኔራል ይርዳው ገብረ መድኅን፣ ሜጄር ጄኔራል ገብረ መድኅን ፈቃዱ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔርና ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋን እንዳነጋገረ ጠቁሟል፡፡

የኮሚሽኑ የበላይ ኃላፊዎች፣ ታሳሪዎች በጥሩ አካላዊ ደኅንነት ላይ እንደሚገኙ፣ የሚገኙበት አካባቢና ክፍሎች ንፁህና ብዙም ያልተጨናነቁ የተፈጥሮና የኤሌክትሪክ ብርሃን እንዳላቸው እንዳረጋገጡ በመግለጫው ተገልጿል፡፡

ሁሉም ከላይ የተገለጹት ታሳሪዎች ወደ ፌዴራል ፖሊስ እስር ቤት ከመጡ ወዲህ ተገቢ ያልሆነ የእስር አያያዝ አለመኖሩን፣ ፖሊሶችም በተገቢው የሙያ ሥነ ምግባር የሚሠሩ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የሕክምና አገልግሎት ባለው አቅም እያገኙ እንደሆነ፣ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ተገናኝተው አቅርቦት እንደሚቀበሉና ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት መቻላቸውንም ኮሚሽኑ አክሎ ገልጿል፡፡

የተወሰኑ ታሳሪዎች በመከላከያ ሠራዊት አባላት በትግራይ ክልል በበረሃ ውስጥ ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ፣ በሰብዓዊ እንክብካቤ መያዛቸውንና የመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ከድንገተኛ አደጋና ጥቃት እንደ ጠበቋቸው መግለጻቸውን በኮሚሽኑ መግለጫ ተጠቁሟል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...