Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በኢትዮጵያ የሒሳብ ሙያን የሚደግፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የተመሰከረላቸው የሒሳብና የኦዲት ባለሙያዎች ማኅበር በኢትዮጵያ የዘርፉ ተቆጣጣሪ አካል ከሆነው ከኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ጋር በመተባበር፣ የሒሳብ ሙያ ልማትን የሚደግፍ ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ይፋ አደረገ።

ቅዳሜ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠበት የሒሳብና የኦዲት አያያዝ ተግባር በገንዘብ ሚኒስቴር በሚተዳደር ፈንድ አማካይነት፣ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለትም ተገልጿል፡፡

የተመሰከረላቸው የሒሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ማኅበርና የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት በማጠናከር በጥር ወር 2012 ዓ.ም. የረዥም ጊዜ የአጋርነት ስምምነታቸውን ማደሳቸውን ያስታወሱ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱም በሁለቱ ተቋማት መካከል አስቀድሞ የነበረ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በፕሮጀክቱ ስምምነት መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሒሳብ ሙያን ለማጠናከር እንደ መሠረት ሆኖ ለማገልገል ትልቅ ድርሻ እንዳለው፣ ፕሮጀክቱ የሙያውንና የበርካታ ባለድርሻ አካላትን ፍላጎቶች ለማሟላት የሚያስችል ጠንካራ ስትራቴጂ ዕቅድ የተነደፈለት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ሥራው ይበልጥ ጠንካራ የሆነ፣ ለጉዳዩ የሚመጥንና ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን የሚያሟላ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋትና ዓለም አቀፍ የደረጃ መሥፈርቶችን በማክበር ላይ አተኩሮ መንቀሳቀስን የሚያስችል መሆኑ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡

ተመሰከረላቸው የሒሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ማኅበር የገበያ (አጋርነትና ዕውቅና) ዳይሬክተር ስቴፈን ሺልድስ፣ ‹‹ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ፣ ፕሮጀክቱ ከብሔራዊ ባለሙያዎችና ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር በመተባበር የተጀመረ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማም ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የሒሳብ ሙያ ዘላቂ በሆነ መንገድ በመገንባት፣ የሕዝቡን ጥቅም ማስጠበቅ እንደሆነም ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሒክመት አብደላ፣ ከተመሰከረላቸው የሒሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ማኅበር ጋር መሥራት በሙያው ክፍተኛ ቁጥጥር ለማድረግ፣ እንዲሁም የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ አስፈላጊ የሆኑት ማስፈጸሚያዎች እንዳሉት ጠቁመዋል፡፡

ከታቀዱ የካፒታል ገበያዎችና ኢኮኖሚዎች  ክፍት ከማድረግ ጋር ተያይዞ ሕዝቡና ኢንቨስተሮች የሚወስኗቸው ውሳኔዎች አስተማማኝ የፋይናንስ መግለጫዎችን መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ወ/ሮ ሒክመት አክለዋል፡፡

የተመሰከረላቸው የሒሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ማኅበር ከአርባ ዓመታት በላይ ፕሮጀክቶችንና ራስ አገዝ አጋርነቶችን በማልማት፣ የረዥም ጊዜ ልምድ እንዳለው ይነገራል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች