Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናመንግሥት አምነስቲ ኢንተርናሸናል በኤርትራ ወታደሮች ላይ ያወጣውን ሪፖርት በበቂ መረጃ ያልተደገፈ ሲል...

መንግሥት አምነስቲ ኢንተርናሸናል በኤርትራ ወታደሮች ላይ ያወጣውን ሪፖርት በበቂ መረጃ ያልተደገፈ ሲል አጣጣለው

ቀን:

የኢትዮጵያ መንግሥት አምንስቲ ኢንተርናሽናል በአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ላይ በኤርትራ ወታደሮች ተፈጽሟል ብሎ ያወጣው የጭፍጨፋ፣ ግድያ፣ ዝርፊያና የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት በትክክለኛው ሥነ ዘዴ መንገድ ያልተጠና ነው ሲል አጣጣለው፡፡

አምነስቲ የተባለው የመብት ተቋም ዓርብ የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት በአክሱም ከተማ ከኅዳር 10 እስከ 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ከኤርትራ ወታደሮች ጥቃቱ የተረፉ 44 የዓይን ምስክሮችን በስልክና በአካል አናግሮ እንዳወጣው በገለጸው ሪፖርት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁኃን ዜጎች መጨፍጨፋቸውን፣ ሁለት የጅምላ መቃብሮች በሳተላይት መመልከቱንና የተደረገው ጭፍጨፋ የጦር ወንጀል ሊሆን እንደሚችል አመላክቷል፡፡

የተጠናቀረው ሪፖርት በምሥራቅ ሱዳን በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በአካልና በአክሱም ከተማ ካሉ ሰዎች ጋር በስልክ በተደረገ ጥረት እንደሆነ አምነስቲ አመላክቷል፡፡

- Advertisement -

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓርብ የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ማምሻውን ባወጣው መግለጫ የአምነስቲ ሪፖርት በትክክለኛ የአጠናን ዘዴ ያላለፈና ውስንነት ያለበት ነው በማለት ገልጾታል፡፡

ለአብነትም አምንስቲ በጥናቱ ወቅት አናገርኩት ያለው ቄስ በቦስተን የሚገኝ ግለሰብ እንደሆነና እንደዚህ ዓይነት መረጃዎች ፍትሕን ከማምጣት ይልቅ በሕወሓትና ግብረ አበሮቹ የሚወጣውን የተሳሳተ መረጃና ፕሮፓጋንዳ የሚያጠናክር ነው ሲል ገልጾታል፡፡

በሌላ በኩል በሱዳን የስደተኞች መጠለያ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን የሕወሓት ታጣቂዎች እንደሆኑና አምንስቲ በትግራይ ክልል በመገኘትና ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያ የመንግሥት አካላትን በማነጋገር ተደረገ የተባለውን ነገር ማጣራት ተገቢ ነው በማለት ውጭ ጉዳይ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

የአምነስቲን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለን (ዶ/ር) ጠቅሶ ባወጣው መግለጫው የአምነስቲ ሪፖርት በአትኩሮት እንዲታይና የምርመራ ውጤቱ ኮሚሽኑ በክልሉ እያደረገ ያለውን ምርመራ እንደሚያግዘው ገልጿል፡፡

ለ24 ሰዓታት በዘለቀው ከኅዳር 19 እስከ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በአክሱም ከተማ የኤርትራ ወታደሮች ሆን ብለው በአደባባይ የከተማው ነዋሪ ላይ ተኩስ መክፈታቸውንና ቤት ለቤት እየዞሩ መዝረፋቸውን አስመልክቶ ኮሚሽኑ ጥናት እያካሄደ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት በበኩሉ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትና አጠቃላይ የምርመራ ሥራ ጠቅሶ መንግሥት የማንኛውንም ዓለም አቀፍ የሙያ ድጋፍና ትብብር እንደሚጋብዝና ለምርመራ የሚመጡትንም  እንደሚቀበል ገልጿል፡፡

ዓርብ አመሻሹ ላይ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አምንስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት የተሳሳተ መረጃና በሪፖርቱ በተለይም በሱዳን አናገርናቸው ብለው የጠቀሷቸው ሰዎች በማይካድራ ጭፍጨፋ ላይ የተሳተፉ የሚሊሻ አባላት እንደሆኑና ሪፖርቱ የሙያ ሥነ ምግባርን ያልተከተለ ነው በማለት አጣጥሎታል፡፡

በተጨማሪም ከኤርትራ መንግሥት ስለጉዳዩ ምንም ማብራሪያ እንዳልተጠየቀ አክለው ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...