Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ላይ የተደቀነው የፊደል ቀረፃ ችግር

በአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ላይ የተደቀነው የፊደል ቀረፃ ችግር

ቀን:

ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ እ.ኤ.አ. በ1999 ባደረገው ጉባዔ፣ የባህልና ቋንቋ ብዝኃነትን ለማሳደግ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን በየዓመቱ የካቲት 14 (ፌብሯሪ 21) ቀን እንዲከበር በወሰነው መሠረት በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ እያከበረች የምትገኘው ኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰመራ ከተማ ‹‹የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ለትምህርትና ማኅበራዊ ተግባቦት መጠቀምን በማረጋገጥ ልሳነ ብዝኃነትን ማበረታታት!›› በሚል መሪ አክብራለች፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ፣ ቋንቋዎችና  ባህሎች አካዴሚ የሥነ ልሳን ተመራማሪ ተሾመ የኋላሸት (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ በአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ትምህርት የሚሰጥባቸው በርካታ ቋንቋዎች ይገኛሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አንዳንዶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጣቸው ትምህርት የሚያበቃ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ብቻ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይማራሉ፡፡ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መሰጠቱ ጠቀሜታው ከፍ ያለ፣ ተማሪዎችም መሠረታዊ ዕውቀት እንዲኖራቸውና የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዙ ያግዛል፡፡

በኢትዮጵያ የአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር ማስተማር ሒደት ሲታይ የፊደል ቀረፃ ላይ ችግሮች እንዳሉ የሚናገሩት ተሾመ (ዶ/ር)፣ በተወላጅ ‹‹ፊደል ይቀረፅ›› ሲባል በሙያው ብቁ ባልሆኑ ሰዎች ጭምር እየተቀረፀ በመሆኑ ትልቅ ፈተና መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ትልቁ ችግር ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር ያለመማር ብቻ ሳይሆን፣ የፊደል ቀረፃ በማን ይደረጋል? ምን ያህል ሰዎች ተሳትፈውበታል እንዲሁም ሒደቱ ኅብረተሰቡ ተወያይቶበትና አምኖበት አለመሆኑ ነው፡፡ ይህም በትምህርቱ ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡

የሥነ ልሳን ምሁሩ ተሾመ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉት ጥረቶች በተበታተነና መናበብ በሌበት በመሆኑ በተፈለገው ልክ እየተጓዘ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ፊደሎች በባለሙያ ባለመቀረፃቸው ለምሳሌ ትርፍ ፊደል እየተባለ የፈለጉትን ድምፅ የሚወክሉበት አሠራር ተገቢ አለመሆኑን ይጠቁማሉ፡፡

የመማርያ ጽሑፍ አዘጋጃጀት ላይም በችግርነት የሚነሳው ለጋምቤላ ማኅበረሰብ የአማርኛውን ተረት ወደ አኝዋ ወይም ኑዌር ቋንቋ ተተርጉሞ መቅረቡ ነው፡፡

የአማርኛ ተረትና ምሳሌ እንዳለ ወደ ሌላኛው ከመተርጎም ይልቅ ማኅበረሰቡ ከራሱ ባህል በመሳነት የሚተርከውና የሚናገረውን ማቅረብ እንደሚገባ የሥነ ልሳን ተመራማሪው ያስረዳሉ፡፡ 

የቋንቋ ትምህርት አዘገጃጀትና መሰል ሥራዎች ሲከናወኑ በአንድ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰቡ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ተረትና ምሳሌ ሌሎችም ነገሮች ተጠንተው በብዙ ባለሙያዎች መሠራት እንዳለበት ባለሙያው ያሳስባሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...