Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊለአትክልት ምግቦች ያለው ትኩረት ማነስ የሕፃናትና እናቶች ጤና ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑ...

ለአትክልት ምግቦች ያለው ትኩረት ማነስ የሕፃናትና እናቶች ጤና ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በኢትዮጵያ ለአትክልት ምግቦች ከመንግሥት በኩል ያለው የትኩረት ማነስ ከአመጋገብ ባህል ጋር ተዳምሮ እናቶችና ሕፃናት ማግኘት ያለባቸውን በቂ ንጥረ ነገር እያገኙ እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡

ምንም እንኳ የዓለም ጤና ድርጅት አንድ ሰው በቀን 400 ግራም አትክልት መመገብ እንዳለበት ቢገልጽም፣ በኢትዮጵያ ያለው የአትክልት አመጋገብ በቀን ከ20  እስከ 50 ግራም እንደማይበልጥ የተናገሩት የወርልድ ቬጅቴብል ሴንተር የኬንያ ዳይሬክተር  አልፕ ሩትሃርት (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ያለው በጣም ዝቅተኛ የሆነ የአትክልት አመጋገብና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት፣ እናቶችና ሕፃናት ማግኘት ያለባቸውን የካልሲየም፣ ቫይታሚን ኤ፣ ፎሊክ አሲድና አይረን ሜኔራል ባለማግኘታቸው በሕፃናት ጤናና ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

ባልተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ምክንያት ወደ 38 በመቶ የሚሆኑ ሕፃናት ዕድገታቸው አዝጋሚ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የግብዓትና ምርት አገልግሎት ዘርፍ አማካሪ አቶ ደረጀ አሳምነው በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ ሥጋን መመገብ እንደ ሀብት፣ ክብር እና የዝና መለኪያ በማድረግ ከአትክልት ይልቅ ወደ ሥጋ መመገብ የሚደረገው ዝንባሌ መስተካከል አለበት ይላሉ፡፡

ነገር ግን የአትክልት አቅርቦቱ በተገቢው መጠን እንዳልቀረበና ለዘርፉ የሚሰጠው ትኩረት ማነስ የኅብረተሰቡን የአትክልት አመጋገብ ባህል ዝቅተኛ እንዳደረገው አቶ ደረጀ አክለው ገልጸዋል፡፡

አቶ ደረጀ ይህን ያሉት ወርልድ ቬጅቴብል ሴንተር የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሊተገበር የሚችል የአምስት ዓመት ‹‹ቬጅ ፎር ፕላት ኤንድ  ፒፕል›› የተባለ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ይፋ ሲደረግ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ መቀመጫውን ስዊድን ባደረገው የፈርኒቸር አምራች አይኬኢኤ (IKEA) የተባለ ድርጅት በተገኘ ስድስት ሚሊዮን ዩሮ የተደገፈ ሲሆን፣ በኢትዮጵያና ኬንያ በኔዘርላንዱ ኤስኤንቪ ድርጅትና ወርልድ ቬጅቴብል ሴንተር የሚተገበር መሆኑ ተነግሯል፡፡

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ አጎራባች ወረዳዎች የሚገኙ አርሶ አደሮችንና ሴቶችን አትክልትን በተፈጥሮ መንገድ ማምረት እንዲችሉ የሚያግዝ ሥልጠና ከመስጠት ባለፈ የምርት አቅርቦትና ክትትል በማድረግ በኢትዮጵያ ከ5,000 በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...