Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናመንግሥት ከአሜሪካ ጋር በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የነበረው አለመግባባት እንዲቀጥል እንደማይፈልግ አስታወቀ

መንግሥት ከአሜሪካ ጋር በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የነበረው አለመግባባት እንዲቀጥል እንደማይፈልግ አስታወቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ መንግሥት በቀጣይ ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው ግንኙነት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወቅት በነበረው አለመግባባት እንዲቀጥል እንደማይፈልግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር) ማክሰኞ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በሚኒስቴሩ ሳምንታዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፣ በቅርቡ ወደ ሥልጣን ከመጡት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት ለመፍጠር እየሠሩ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመናቸው ከመጠናቀቁ ሁለት ወራት በፊት፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በሰጡት አስተያየት ምክንያት በኢትዮጵያ በኩል ከፍተኛ ቁጣ አስነስቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

ፕሬዚዳንቱ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክና ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንያም ናታኒያሁ ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት ግድቡን አስመልክተው፣ ሁኔታው አደገኛ እንደሆነና ‹‹ግብፅ ግድቡን  ልታፈነዳው ትችላለች›› በማለት የሰነዘሩት አስተያየት፣ በአገር ቤትና በውጭ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆችን አስቆጥቶ ነበር፡፡

ከዚህ ባለፈም አሜሪካ ለኢትዮጵያ በዕርዳታ መልክ ልታቀርብ አቅዳ የነበረውን 272 ሚሊዮን ዶላር ከህዳሴ ግድብ አሞላልና አጠቃቀም ጋር በተገናኘ እንዳይለቀቅ ተደርጎ ነበር፡፡

በቅርቡ ወደ ሥልጣን የመጡት የዴሞክራት ፓርቲ ተመራጩ ጆ ባይደን አስተዳደር ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ታስቦ የነበረውን ገንዘብ ከህዳሴ ግድብ ጋር እንዳይያያዝ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል በሚያደርገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ ለቀው እንዲወጡና በክልሉ የተፈጠረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ብሏል፡፡

ቃል አቀባዩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹ከአሜሪካ የሚመጣ ዕርዳታ ከግድቡ ጋር መያያዙ ስህተት እንደነበርና አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ሁለቱን ጉዳዮች መለያየቱን የምናደንቀው ነው፤›› ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል በአሜሪካ የሚገኘው ኤምባሲ የቅርብ ግንኙነት እንዲያደርግና በአገር ቤትም ከአሜሪካን ኤምባሲ ጋር በመነጋገር፣ የዲፕሎማቲክ ግንኙነቱ ለማሻሻል ይሠራል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን በተመለከተ ከ75 በላይ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፉን ለሕዝቡ እያደረሱ እንደሆነ፣ በአንዳንድ ቦታዎች በተለይም የደኅንነት ሥጋት ባለባቸው ግን እንዲገቡ አይፈቀድም ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ስለህዳሴው ግድብ ሲያስረዱ ኢትዮጵያ ሌላ አሸማጋይ ወገን እንደማትፈልግ፣ ‹‹የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካ ይታይ የሚል አቋም ነው ያለን፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

ከኢትዮጵያና ከሱዳን ድንበር ግጭት ጋር በተገናኘ የሱዳን ወታደሮች ከጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በፊት የነበሩበት ቦታ ካልተመለሱ ለመደራደር አይቻልም ብለዋል፡፡

‹‹በድንበሩ ጉዳይ በርካታ ወገኖች እናስታርቃችሁ የሚል ጥሪ እያቀረቡ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ በኩል ሱዳን ወደ ቀድሞ ድንበሯ ስትመለስ ሊያደራድሩን ይችላሉ፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...