Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየባየር ሙኒክ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ አሠልጣኞችን ሊያሠለጥኑ ነው

የባየር ሙኒክ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ አሠልጣኞችን ሊያሠለጥኑ ነው

ቀን:

የጀርመን እግር ኳስ ክለብ ባየር ሙኒክ፣ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በገባው የልምድ ልውውጥ ስምምነት መሠረት በባለሙያዎቹ አማካይነት ለአሠልጣኞች ሥልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

ለአሠልጣኞች ተከታታይ ሥልጠናዎችን ለመስጠት ከፌዴሬሽኑ ጋር ሲሠራ የቆየው ክለቡ፣ በተለይ ለወጣት አሠልጣኞች የልምድ ልውውጥና ሥልጠና ለመስጠት ባለሙያዎቹን ወደ ኢትዮጵያ መላኩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ከፌዴሬሽኑ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ በመሆን ለበርካታ ወጣትና ነባር አሠልጣኞች ልምዱን ሲያካፍል የሰነበተው ባየር ሙኒክ ባለሙያዎቹ ከየክልሉ ለተወጣጡ ጀማሪ አሠልጣኞች ለ15 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና እንዲሚሰጥ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት ቀደም ሲል በሁለት ዙር ከየክልሉ ለተወጣጡ የጀማሪ ወጣት አሠልጣኞች በተሰጠው ሥልጠና ተገቢውን ውጤት ላሟሉ እና ወደ ቀጣይ ዙር ላለፉ 30 ወጣት አሠልጣኞች ለተከታታይ አምስት ቀናት ሥልጠናውን በአዲስ አበባ  ስታዲየም ይከታተላሉ፡፡

ሥልጠናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው ለፕሪሚየር ሊግ የሴቶችና የወንዶች ክለቦች አሠልጣኞች መሆኑን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አብራርቷል፡፡

ከዚህም ባሻገር በባየር ወጣቶች ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ከ15 ዓመት በታች ታዳጊዎችን በመመልመልና አሥር ተጫዋቾችን በመለየት በሚያዝያ መጨረሻ በጀርመን ሙኒክ ከተማ ላይ ለሚካሄደው የባየር የታዳጊዎች ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበት ዕድል ይፈጥራልም ተብሏል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ አዳዲስ ወይም ወጣት አሠልጣኞችን መመልከት የቅንጦት ከመሰለ ሰነባብቷል፡፡ በከተማ አስተዳደር ስር የሚተዳደሩ ክለቦችም ሆኑ በካምፓኒ ስር የሚተዳደሩ ክለቦችን ተዘዋውረው በማሠልጠን የሚታወቁት ዘመናት ያሳለፉ አሠልጣኞችን ናቸው፡፡

በአንጻሩ ለወጣቶች ዕድል መስጠት ለክለቦች ጭንቅ ነው፡፡ በፕሪሚየር ሊግ አንድን አሠልጣኝ በተለያዩ ክለቦች መመልከትም የተለመደ ነው፡፡ በተለይ ክለቦች  ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ካደጉ በኋላ ወዲያው ሲያሰናብቱ መመልከት አዲስ አይደለም፡፡

እነዚህ ነባር አሠልጣኞች ‹‹ልምድ ያላቸው›› የሚል ስያሜ ቢሰጣቸውም፣  እግር ኳስ ላይ ይኼ ነው የሚባል ለወጥ ሲያመጡ አይስተዋልም፡፡ ይልቁን ክለቦች በርካታ ረብጣ ገንዘቦችን አፍሰው ከፕሪሚየር ሊግ ሲወርዱ ወይም ለተጫዋቾቻቸው የሚከፍሉት ገንዘብ በማጣት ዕሰጣ ገባ ውስጥ ሲገቡ መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡

በሥልጠናው የሚካፈሉ በርካታ ወጣት አሠልጣኞች ቢኖሩም፣ የማሠልጠን ዕድል ማግኘት እምብዛም ነው፡፡ በሊጉ የሚሳተፉ ክለቦች ከነባርና ከተለመዱ አሠልጣኞች ይልቅ አዳዲስና ወጣት አሠልጣኞች ዕድል መስጠትን መጀመር እንዳለባቸው የበርካቶች አስተያየት ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ2,700 በላይ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገለጸ

ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ የንብረት ጉዳት ደርሷል በአበበ ፍቅር ባለፉት ዘጠኝ...

የአብዮታዊት ኢትዮጵያ የጦር ሜዳ ጀብዱ ኒሻን ተሸላሚው ሻለቃ ባሻ ዓሊ በርኬ (1943-2015)

ከአርባ ስድስት ዓመታት በፊት፣ ኢትዮጵያ ከወራሪው የሶማሊያ ሠራዊት ጋር...

ኢትዮጵያን የአኅጉራዊ የነፃ የንግድ ቀጣና ተሳታፊ ለማድረግ ድርድር እየተደረገ መሆኑ ተነገረ

ኢትዮጵያ ወደ ትግበራ ለማስገባት ዘግይታበታለች ተብሎ የሚነገረውን የአፍሪካ ነፃ...

ኩዌት ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞችን ለመቀበል መዘጋጀቷን አስታወቀች

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኦማን ጋር አዲስ ስምምነት ላይ መድረሱን...