Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊአስተዳደሩ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ዕድር ቤቶቻቸውንና መኖሪያቸውን ማፍረሱ ነዋሪዎች አስቆጣ

አስተዳደሩ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ዕድር ቤቶቻቸውንና መኖሪያቸውን ማፍረሱ ነዋሪዎች አስቆጣ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ጨፌ ዓድዋ ፓርክ ተብሎ በሚታወቀው ሥፍራ፣ ከ28 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ ሁለት ዕድር ቤቶችን ጨምሮ በርካታ መኖሪያ ቤቶችን ያለ ምንም የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዳፈረሱባቸው ነዋሪዎች  ገለጹ፡፡

አካባቢው ለካንሰር ሕክምና ማዕከል ግንባታና ለልማት ይፈለጋል ትነሳላችሁ የሚል የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም፣ ለተነሺዎቹ ምንም ዓይነት ምትክ ቦታ ሳይሰጥ አንዳንዶቹም የፍርድ ቤት ዕግድ ደብዳቤ ይዘው ሳለ፣ በአቋራጭ የከተማ አስተዳደሩ ቤቶቹን ማፍረሱ ዱብ ዕዳ እንደሆነባቸው፣ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዕድር አባል ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ከ368 በላይ አባዎራዎችን የያዙ የተባበሩት መድኃኔዓለምና ቦሌ ደብረ ጽጌ የተባሉ ዕድር ቤቶችን ጭምር ያፈረሰው የከተማው አስተዳደር፣ ምትክ ቦታ ይሰጣችኋል ማለቱን፣ አንዳንድ ነዋሪዎች ደግሞ ከ30 ዓመታት በላይ በቦታው ላይ እንደቆዩ አክለው ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

‹‹ካርታ ይሰጣችኋል ጠብቁ ተብለን ሳለ የከተማ አስተዳደሩ ለ30 ዓመታት ያህል የኖርንበት ቤት ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በሁለት ቀናት ውስጥ ለቃችሁ ውጡ ብሎ በማፍረሱ፣ ወዴትም ሄደን እንድንጮህ ዕድል አልሰጠንም፤›› ሲሉ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ አንድ በዕድሜ ገፋ ያሉ ነዋሪ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለሚዲያ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ቦታው በዋነኝነት የጤና ተቋማት እንዲገነቡበት ታስቦ የተደረገ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የሚገነባው የጤና ተቋም ‹‹ለኢትዮጵያ ልዩ ተቋም ነው፣ የሕይወት ጉዳይ ነው፤›› በማለት ተናግረው ነበር፡፡

‹‹በተጨማሪም ለግንባታው ያማከለ ቦታ ወሳኝ ከመሆኑ ባሻገር፣ ኢትዮጵያን በአዲስ አበባ ደረጃ የምትገለጽ ዋና ከተማ ማድረግ አለብን፤›› ብለዋል፡፡

ሪፖርተር በዓድዋ ፓርክ አካባቢ ተገኝቶ እንዳረጋገጠው ቤቶቹ ሙሉ በሙሉ የፈረሱ ሲሆን፣ ከከተማ አስተዳደሩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...