Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊብልጫ ላላቸው 300 ተመራቂዎች የአመራርነት ሥልጠና ሊሰጥ ነው

ብልጫ ላላቸው 300 ተመራቂዎች የአመራርነት ሥልጠና ሊሰጥ ነው

ቀን:

የተሻለ ውጤት ላላቸው 300 ተመራቂዎች በአምስት ዓመታት ውስጥ የአመራርነት ክህሎት ሥልጠና እንደሚሰጥ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ተመራቂ ተማሪዎች በሠለጠኑበት የትምህርት ዘርፍ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱና በሙያው መሠረታዊ ዕውቀት እንዲያገኙ፣ በሥራ ላይ ስምሪት ወቅት ውጤታማ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ለማድረግና ክህሎታቸው ከፍ እንዲል ለማስቻል የወጣቶች አፓረንትሺፕና ኢንተርንሺፕ (የሥራ ላይ ሥልጠና እና ልምምድ) ፕሮግራም በአገር አቀፍ ደረጃ ማስጀመሩንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ሠልጣኞች በአንድ ዓመት ውስጥ የሚያጠናቁት የአመራርነት ክህሎት ሥልጠናም ከሁሉም ክልሎች ተማሪዎችን በመመልመል ይጀመራል ተብሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሥልጠናውን ለማስጀመርም ሚኒስቴሩ፣ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና ከሴንተር ፎር አፍሪካ ሊደርሽፕ ስተዲስ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ 60 ተመራቂዎች በመጀመርያው ዙር የአመራርነትና የአገልጋይነት ሥልጠና በተግባር እንዲያገኙ እንደሚደረግ የሴቶች የሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ፈሊሰን አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡

ሠልጣኞች ስድስት ሺሕ ብር ወርኃዊ ክፍያ የሚያገኙ ሲሆን፣ ሥልጠናውን ጨምሮ ሌሎች ወጪዎችን ሴንተር ፎር አፍሪካ ሊደርሺፕ ስተዲስ ከአጋር አካላት ጋር እንደሚሸፍን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የሥራ ላይ ሥልጠና እና ተለማማጅነት የሚተገበረው መደበኛ ሥራ ከመጀመራቸው አስቀድሞ ዕውቀትና ክህሎትን እንዲያዳብሩ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የሥልጠናው ዓላማም ክህሎት ያላቸው፣ በሥራ ሥነ ምግባር የታነፁ፣ የሥራ ተነሳሽነት የተላበሱና ከአዳዲስ አሠራሮች ጋር ተዋህደው በተመደቡበት ተቋም ሥራቸውን በብቃት እንዲወጡ ማድረግ መሆኑንም አቶ ቴዎድሮስ አብራርተዋል፡፡    

የአመራርነት ክህሎት ሥልጠና ሲጠናከር፣ በግልና በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተቀጥሮ ከመሥራት ባለፈም በራሳቸው ለመሥራት ያስችላል፡፡

የሥራ ላይ ልምምዱ በራስ መተማመንንና ውጤታማነትን እንዲሁም በተቋማትና በአሠሪዎች ዘንድ አመኔታን እንዲያገኙና ከባልደረቦቻቸው ጋር ተጣጥመው እንዲሠሩ ያስችላል፡፡ የሥራ ፍላጎታቸውን ከመጨመር ባሻገርም የሥራ ላይ እና የእርስ በርስ ግንኙነትና የቡድን ሥራን ያሳድጋል፡፡

የወጣቶችን አቅም በማሳደግም ችግሮችን በራስ የመፍታት ችሎታን ማጎልበት፣ የማኅበረሰቡን ባህልና ዕሴቶች በቀላሉ እንዲረዱና የሙያ ትስስርን በመፍጠር የዕውቀት አድማሳቸውን ያሰፋል፡፡

ተመራቂ ወጣቶች ዕድሉን በሚገባ እንዲጠቀሙና በተመደቡበት ዘርፍ በትጋት እንዲሠሩ፣ ከዚሁ ጎን ለጎን ተቋማት በሥራ ልምምድ ላይ ለሚገኙ ወጣቶች ተገቢውን የቅርብ ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...