Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትጵያ ንግደ ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ አገኘ፡፡

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2020 በጀት አመት አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ 100 ባንኮች መካከል የ 17ኛ፣ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ 1ኛ ደረጃ በመያዝ አመቱን ማጠናቀቁን አፍሪካ ቢዝነስ እና ዘ አፍሪካ ሪፖርት በጥናታቸው ይፋ አደረጉ፡፡ 

የአፍሪካ ባንኮች በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት በተከሰተው የኢኮኖሚና የንግድ መቀዛቀዝ ሳይበገሩ ከባለፉት አሥር ዓመታት የተሻለ የካፒታል መጠን በማስመዝገብ አመቱን አጠናቀዋል፡፡ ባንኮች አማራጭ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅና በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች አማካኝነት ተደራሽነትን ለማስፋት ያደረጉት ጥረት የኮቪድ ተጽዕኖን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳስቻላቸው የጥናት ሪፖርቶቹ አስነብበዋል፡፡ 

ጥናቶቹ እንዳመለከቱት አፍሪካ ውስጥ የባንኮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም፣ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር እና በባንክ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ በ2004 ዓ.ም በናይጄሪያ 89 ባንኮች በአገልግሎ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ 2019 ዓ.ም የባንኮቹ ቁጥር ወደ 27 መውረዱ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ በኬንያም በተመሳሳይ 10 ባንኮች ሲዋሃዱ 3 ባንኮች ደግሞ ከስራ ውጭ ሆነዋል፡፡

በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካ የሚንቀሳቀሰውና ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ላይ የተሰማራው ታይም ባንክ እ.ኤ.አ በየካቲት 2019 ዓ.ም በቀን እስከ 6000 የባንክ ሂሳቦች መክፈት የቻለ ሲሆን፣ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት እንቅስቃሴዎች በተገቱበት ወቅት ብቻ ከ400 ሺ በላይ የባንክ ሂሳቦችን በመክፈት ከ613 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል፡፡ ይህም በአፍሪካ ብዙ ያልተነካውን የዲጂታል የባንክ አገልግሎት በመጠቀም ባንኮቹ ወረርሽኙ የደቀነውን አደጋ  መቋቋም መቻላቸውንና በገንዘብ ንክኪ ምክንያት ለወረርሽኝ መስፋፋት አመቺ የነበረውን አሰራር ማስቀረት መቻሉን አመላካች ነው፡፡

የኢትጵያ ንግድ ባንክ ከአፍሪካ ቀደምት ባንኮች አንዱ ሲሆን፣ ባለቤትነቱ የሀገር ሀብት ሆኖ በአገር ውስጥ ብቻ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በአፍሪካ ተወዳድሮ 17ኛ ከምስራቅ አፍሪካ ከ267 በላይ ባንኮች በሚገኙበት ምድብ 1ኛ መሆኑ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ባንኩ እየተገበረ ያለው የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ የባንኩን ተደራሸነት፣ የአገልግሎ ጥራትና ቅልጥፍና በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው የሚጠበቅ ሲሆን፣ የአፍሪካ ተፎካካሪነቱን በማጠንከር አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባንክ ለመሆን ላስቀመጠው ራዕይ ስኬትም ትልቅ ስፍራ ይኖረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች