Thursday, April 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኮሚሽኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ ሀብት ያላስመዘገቡ 197 ተቋማትን በሕግ እንደሚጠይቅ...

ኮሚሽኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ ሀብት ያላስመዘገቡ 197 ተቋማትን በሕግ እንደሚጠይቅ አስታወቀ ሀብት ካላስመዘገቡት መካከል ሕግ አስከባሪ ተቋማት ይገኙበታል

ቀን:

የፌዴራል መንግሥት ተቋማት በሥራቸው የሚገኙ ሠራተኞችን ሀብትና ንብረት እስከ ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ መዝግበው እንዲያጠናቅቁ በተሰጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ግዴታቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ 197 የፌዴራል መንግሥት ተቋማት ላይ አስተዳደራዊናጋዊርምጃ እንደሚወስድ፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ‹‹በሕጉ መሠረት እስከ ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ የሠራተኞቻቸውን ሀብትና ንብረት ባላስመዘገቡ ተቋማት ላይ ከጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ያለመንም ቅድመ ሁኔታ አስተዳደራዊና ሕጋዊርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚሽኑ በአጽንኦት ይገልጻል፤›› ሲል፣ ዓርብ ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ማምሻውን ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በላከው መግለጫ ግዴታቸውን አልተወጡም ያላቸውን ተቋማት ማንነት ዘርዝሮ ያቀረበ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስትር ሕፈት ቤትና ዋነኞቹ ሕግ አስከባሪ ተቋማት ማለትም የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ፌዴራል ፖሊስና የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ይገኙበታል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ተቋማቱ የኃላፊዎችንና ሠራተኞችን ሀብትና ንብረታቸውን ማስመዝገብ እንዳለባቸው የሚያውቁ ቢሆንም፣ በቸልተኛነትና ፈቃደኛ ባለመሆን ግዴታቸውን እንዳልተወጡ ገልጿል። እስከ ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሀብትና ንብረት ያላስመዘገቡት ተቋማት ብዛት 197 መሆኑን ያመለከተው መግለጫውከእነዚህም ውስጥ 109 የሚሆኑት የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የፌዴራል የመንግሥት የልማት ድርጅቶችና በፌዴራል መንግሥት የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች መሆናቸውን አስታውቋል።

የተቀሩትን ተቋማት በተመለከተም 60 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት፣ ክፍለ ከተማና ወረዳዎች፣ እንዲሁም 28 የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተቋማትና ቀበሌዎች እንደሆኑም መግለጫው ያመለክታል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...