Thursday, April 18, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለሁለተኛው ዙር የ40/60 ንግድ ቤቶች ጨረታ በካሬ 151 ሺሕ ብር ከፍተኛና 23 ሺሕ ብር ዝቅተኛ ዋጋ ቀረበ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ደቡብ ግሎባል ባንክ ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ ሆኗል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለሁለተኛ ዙር ለጨረታ አቅርቧቸው ለነበሩ የ40/60 ንግድ ቤቶች፣ በካሬ ሜትር ከፍተኛው ዋጋ 151,000 ብር ሲቀርብ ዝቅተኛው ደግሞ 23,951 ብር ቀረበ፡፡

ኮርፖሬሽኑ በቦሌ እህል ንግድ፣ በቦሌ አያት፣ በቦሌ ቡልቡላ፣ በቦሌ ሎቄ፣ በቦሌ ሕንፃ አቅራቢ፣ በልደታ ሰንጋ ተራ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክራውንና በኮልፌ ቀራኒዮ ሳይቶች በተገነቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር የተገነቡ 149 የንግድ ቤቶችን ለጨረታ አቅርቦ ነበር፡፡

ለወጣው ጨረታ ከፍተኛና ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረቡ 298 ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች፣ ለአንድ ቤት ተወዳድረው ከፍተኛና ዝቅተኛ ዋጋ ማቅረባቸውን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ከፍተኛ ዋጋ 151,000 ብር በማቅረብ በቦሌ እህል ንግድ ሳይት የ40/60 ንግድ ቤትን ያሸነፈው ደቡብ ግሎባል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ሲሆን፣ ተፎካካሪው ብርሃን ባንክ አክሲዮን ማኅበር ካቀረበው 83,460 ብርን በ67,540 ብር በልጦ አሸንፏል፡፡

ሌላው የጨረታ ሒደት የተካሄደው እዚያው ቦሌ እህል ንግድ ሳይት ሲሆን፣ ሁለት ግለሰብ ነጋዴዎች ለአንድ የንግድ ሱቅ ዝቅተኛው ዋጋ አንደኛው ተጫራች 23,950 ብር ሲያቀርብ ሌላው ተጫራች በ51 ብር በመብለጥ በ24,001 ብር አሸናፊ መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ መግለጫ ያስረዳል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች