Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹በክርክር እና በውይይት የማሸነፊያ ስልቶች››

‹‹በክርክር እና በውይይት የማሸነፊያ ስልቶች››

ቀን:

ሰሞኑን ለአንባቢያን የቀረበው የአቶ ሲሳይ አለፌ ተሰማ መጽሐፍ፣ ‹‹በክርክር እና በውይይት የማሸነፊያ ስልቶች›› ይሰኛል፡፡ ክርክርን በተለያዩ ዓውዶች ማሸነፍ የሚቻለው በሐሳብ ልዕልዕና በጥበባዊ አቀራረብ ብቻ ነው! የሚለው ደራሲው እንደሚገልጹት፣ ክርክር እና ውይይት – በቤተሰብ፣ በጓደኛሞች፣ በተለያዩ ቡድኖች፣ ለአጭር ወይም ለረዥም ጊዜ ለተለያየ ዓላማ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሊካሄድ ይችላል፡፡ ክርክርን ማሸነፍ የሚቻለው በጉልበት ሳይሆን በብልኃት ነው፡፡

‹‹መጽሐፉ በክርክር እና በውይይት ወቅት ማድረግ ስለአለብዎና ስለሌለብዎት አቀራረብ አቅጣጫ ያሳይዎታል፣ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያፈልቁ ይረዳዎታል፣ ምሳሌ ይጠቀስልዎታል፤›› ሲልም ያክላል፡፡ መጽሐፉ በማኅበራዊ፣ በምጣኔ ሀብታዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚከራከሩና የሚወያዩ ሁሉ ግባቸውን ለማሳካት የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው የሚሉት የመጽሐፉ አዘጋጅ፣ በግለሰቦችና በትምህርት ተቋማት፣ በተለያዩ ድርጅቶችም ዘወትር ሊኖር የሚገባው መመርያ ነው ይላሉ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ለሚያጋጥሙ የሐሳብ ፍጭቶች በዕውቀትና በአቀራረብ ጥበብ ላይ የተመሠረተ ክርክር ምንጊዜም አሸናፊ መሆኑንም ያስገነዝባሉ፡፡

በአሥራ ስድስት ምዕራፎች የተደራጀው መጽሐፉ በ180 ብር ለሸመታ ቀርቧል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...