Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፋሲል ከነማ ከካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውጪ ሆነ

ፋሲል ከነማ ከካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውጪ ሆነ

ቀን:

ኢትዮጵያን በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በመወከል ከዩኤስ ሞናስተር ጋር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ያከናወነው ፋሲል ከነማ ከውድድር ውጪ ሆኗል፡፡

ቅዳሜ ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የመልስ ጨዋታውን ያደረገው ፋሲል ከነማ 3ለ2 በሆነ ድምር ውጤት ተረቷል፡፡ የመጀመርያውን ጨዋታ ከሜዳው ውጪ አድርጎ 2ለ0 ተሸንፎ ከተመለሰ በኋላ የቱኒዚያውን ክለብ በአዲስ አበባ ስታዲየም አስተናግዶ ውጤቱን ቀይሮ ወደ ቀጣዩ ዙር ያመራል ተብሎ ቢጠበቅም ድል ሳይቀናው ቀርቷል፡፡

በአዲስ አበባው የመልስ ጨዋታ የበላይነት ወስዶ ሁለት ግብ አስቆጥሮ መምራት ቢችልም ተጋባዥ ዩኤስ ሞናስተር በመጠናቀቂያ ሰዓት ላይ ያስቆጠረው ግብ የፋሲሎችን ዕድል አጨልማለች፡፡

በአኅጉራዊ ውድድሮች ላይ የሚያስቆጩ ስህተቶችን በመሥራት አባዜ ውስጥ ያሉት ክለቦች ብቻ ሳይሆኑ ብሔራዊ ቡድኖችም ጭምር ናቸው፡፡ የሚሠሯቸው ስህተቶች ተመሳሳይነት አላቸው፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ከፍተኛ ጫና ሲያደርጉ የቆዩት ሞናስተሮች 68ኛው ደቂቃ አካባቢ ሁለቱ ተጫዋቾች ተጋጭተው ጉዳት በመድረሱ ለአሥር ደቂቃዎች ተቋርጦ ነበር፡፡ ሁለቱም ተጫዋቾች በአምቡላንስ ተወስደው ሕክምና ተደርጎላቸዋል፡፡ ከፍተኛ ውጥረት በነገሠባቸው የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች መደበኛው ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨመረው አምስተኛ ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የተገኘችውን ኳስ በግንባር በመግጨት ወደ ግብ የቀየረው የሞናስቲሮ ፋዲ አፍሮዩ የፋሲሎችን የአኅጉራዊ ውድድር ጉዞ በአጭር አስቀርቷል፡፡

በድምሩ 3ለ2 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ የሆነው ፋሲል ከነማ ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ቢወክልም የመጀመርያዎቹን ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ግን ማለፍ ተስኖታል፡፡

ከጊዜ በኋላ ከአገር ውስጥ የሚከናወኑ ውድድሮች ላይ ዋንጫ አንስተው በአኅጉራዊ ውድድሮች ኢትዮጵያን ሲወክሉ ከመጀመርያ ዙር ማለፍ ምጥ የሆነባቸው የሊጉ ክለቦችን መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንኳን ኢትዮጵያን በካፍ ውድድሮች ላይ የወከሉ ክለቦች ደደቢት፣ መከላከያና ፋሲል ከነማ የመጀመርያውን የማጣሪያ ጨዋታ ማለፍ አልቻሉም፡፡

በተመሳሳይ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ኢትዮጵያን መወከል የቻሉ ክለቦች ውስጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ጅማ አባጅፋር እንዲሁም መቐለ ሰብዓ እንደርታ ይጠቀሳሉ፡፡ ከእነዚህ ክለቦች ውስጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ የምደብ ድልድል ውስጥ መግባት ችሏል፡፡ ሌሎች ከመጀመርያው ዙር ውድድር ማለፍ አልቻሉም፡፡ ይኼም በብሔራዊ ቡድኑ ላይ በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ ጥቃቅን ስህተቶች በክለቦችም ላይ መንፀባረቁ በእግር ኳሱ ላይ በተደጋጋሚ የሚስተዋለውን ክፍተት መድፈን አለመቻሉ ማሳያ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

ዓምና በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት 17ና ሳምንት ላይ የተቋረጠው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮውን ውድድር ቅዳሜ ታኅሣሥ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ይጀምራል፡፡ ፋሲል ከነማ ከካፍ ኮንፌዴሬሽን ሽንፈት በኋላ በፕሪሚየር ሊግ በመጀመርያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስን በአዲስ አበባ ይገጥማል፡፡ ጨዋታውም የመጀመርያ ጊዜ በዲኤስ ቲቪ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ይቅርብኝ!  

ዓይኔ አይይ ይቅርብኝ ማየቴ ካልረዳኝ፣ የመጥፎ ድርጊት ጦር ጨረሩ ከጐዳኝ፡፡ አላውራ...

ለድሀ በእውነት የሚፈርድ

በእውቀቱ ሥዩም አዲስ አበባ ውስጥ እንደ ቦሌ መድኃኔዓለም እሚገርመኝ ሰፈር...

ተፈጥሯዊው መምህር

ችግር ተፈጥሮአዊ መመህር ነው፡፡ ችግር የታላቅ ህይወት በር ነው፡፡...

ቻርልስ ደሞ ያበዛዋል

የመንደር ወሬ የማያመልጣቸው ስኮትላንዳዊው አያ ላዘንበሪ የሰሙትን ወሬ ለቡና...