Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለዓለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ጉባዔ መዳረሻ ተከታታይ ውይይቶች የሚደረጉበት መርሐ ግብር ማስጀመርያ ፊርማ ተፈረመ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በየአራት ዓመቱ የሚከናወነው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ጉባዔ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ እ.ኤ.አ. በጁን 2019 ተቀባይነት መወሰኑን ተከትሎ፣ ለዚሁ ጉባዔ መንደርደሪያ የሚሆኑ የተለያዩ መርሐ ግብሮችን የሚካተቱ ተከታታይ ውይይቶችን ማስጀመርያ መርሐ ግብር፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድና (ዶ/ር) የዓለም አቀፍ የቴሌኮሙዩኒኬሽንስ ኅብረት ሊቀመንበር ሁሊን ዣዎ ባደረጉት የስምምነት ፊርማ ይፋ ተደረገ፡፡

በበይነ መረብ የድምፅና ምሥል ጥሪ (ዙም) በተደረገ ውይይት ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ በርካታ ታዳሚዎች የተገኙበት የማስጀመርያ መርሐ ግብር በተደረገበት ወቅት እንደተገለጸው፣ እነዚህ ተከታታይ ውይይቶች ወጣቶች፣ የዘርፉ ተዋናዮች፣ የፈጠራ ባለሙያዎችና የተለያዩ የዘርፉ ባለሙያዎች ይሳተፉባቸዋል ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የቴሌኮሙዩኒኬሽንስ ኅብረት ሊቀ መንበር ሁሊን ዣዎ ጋር እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2019 ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ የተወሰነው ይኼ ጉባዔ 4,500 ያህል ተሳታፊዎችን ያስተናግዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አህመዲን (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ጉባዔው የዛሬ ዓመት እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 9 እስከ 19 ቀን 2021 በአዲስ አበባ ለመጀመርያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ዝግጅት ለማድረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን፣ የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ያካተተ ብሔራዊ ኮሚቴ መዋቀሩንና በሥሩም ንዑሳን ኮሚቴዎች እንዳሉ አህመዲን (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ ስለጉባዔው ማወቅ ለሚፈልጉም መረጃ የሚሰጥ www.wtdc21.et የሚል አዲስ ድረ ገጽ መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

ሪፖርተር ላቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አህመዲን (ዶ/ር)፣ በአይሲቲ ስትራቴጂ 2025 እንደተመላከተው አሁን መንግሥት እያደረገ ያለው የቴሌኮም ዘርፍን ለግል ባለሀብት ክፍት የማድረግና አዳዲስ አገልግሎት ሰጪዎችን ማስገባት ለዘርፉ በርካታ ጠቀሜታን ይሰጣል ብለው፣ ይኼም ሰፊ ትስስርንና ተደራሽነትን ለመፍጠር እንደሚረዳና ተወዳዳሪነት መብዛቱም ለዘርፉ ዕድገት እንደሚበጅ አስረድተዋል፡፡

ጉባዔው ለኢትዮጵያ ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በተለመከተም ያስረዱት ሚኒስትር ዴኤታው አገሪቱን ለማስተዋወቅ፣ በትኩረት ገበያው ለመሳተፍ፣ የቱሪዝም ዕድል ለመፍጠር፣ እንዲሁም በዘርፉ ኢንቨስትመንት ለመሳብና ተፅዕኖ ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል፡፡ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ሁሊን ዣዎ ይኼንን መሰል ዝግጅት ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ የመጀመርያዋ አፍሪካዊት አገር መሆኗን በመጥቀስና ለዚሁም በማመስገን፣ ይኼ ጉባዔ ስለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጠቀሜታ የዓለምን ሰዎች ለማስተባበርና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የዲጂታል ትስስር የሚኖረውን ሚና አዲስ አጀንዳ አድርጎ በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች