Saturday, July 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት አሥር አመራሮችን ከኃላፊነት ያነሳበት መንገድ ጥያቄ አስነሳ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት አሥር አመራሮችን ከኃላፊነት ያነሳበት መንገድ ጥያቄ አስነሳ

ቀን:

አመራሮቹ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን መመደባቸው እንደተነገራቸው ተሰምቷል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሥር የተዋቀሩ  ዳይሬክቶሬቶችንና የሥራ ሒደት ክፍሎችን ሲመሩ የነበሩ ኃላፊዎች ድንገት ለስብሳባ ተጠርተው ከኃላፊነታቸው መሳታቸው እንደተነገራቸው የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

ኃላፊዎቹ እንዲነሱ የተደረጉት በፓርቲ ሆነ በመንግሥት ደረጃ፣ በሥራ አፈጻጸም አሊያም በሥነ ምግባር ችግር ሳይገመገሙና ችግር ሳይገኝባቸው መሆኑ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ምንጮች እንዳብራሩት ከሆነ፣ በከተማው አስተዳደር አማካይነት ከሁለት ሳምንት ወዲህ ከማዕከል ጀምሮ በክፍለ ከተማ ብሎም እስከታች በሚገኙ አመራሮችን የማሸጋሸግና የማንሳት ዕርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ፡፡

አመራሮችን የማሸጋሸግና የማንሳት ዕርምጃ ሲካሄድ፣ በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሥር በሚገኙት አመራሮች ላይ የተነሳ የሥራ አፈጻጸም አሊያም የሥነ ምግባር ችግር እንዳልነበር ከተነሱት ኃላፊዎች መካከል ሪፖርተር ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹ ረቡዕ፣ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 ገደማ በከንቲባው ጽሕፈት ቤት በኩል ጥሪ ደርሷቸው መሰናበታቸው እንደተነገራቸው ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡

አመራሮቹ በአብዛኛው ወጣቶችና አማካይ ዕድሜያቸውም ከ34 ዓመት በታች እንደሆነ ገልጸው፣ ወደ ኃላፊነት የመጡትም የለውጥ ኃይሉ አዲስና ወጣት ኃይሎችን ወደ አመራርነት ለማምጣት በተከተለው መስመር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በዚሁ አግባብ በቀድሞው ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) አመራር ወቅት ለኃላፊነት የተመለመሉት እነዚህ ወጣቶች፣ የፖለቲካ አመራር አባላት እንደነበሩ አስታውቀዋል፡፡

በፖለቲካም ሆነ በመንግሥት ሥራ ኃላፊነታቸውን ያጎደሉትና የሥነ ምግባር ጥሰት ታይቶባቸው ቢሆን ኖሮ ከኃላፊነታቸው ተነስተው በየተማሩበት መስክ እንዲሠሩ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እንዲመደቡ የተደረጉበትን አግባብ ይቀበሉት እንደነበር ያስታወቁት ኃላፊው፣ ይሁን እንጂ ተጨባጭ ግምገማ ሳይደረግባቸውና ሪፖርት ሳይቀርብባቸው ያለ ምንም የጽሑፍ ማስረጃ እንዲነሱና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እንዲያመለክቱ መደረጋቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡ ከኃላፊነታቸው በዚህ አግባብ በመነሳታቸው የነበሯቸውን ጥቅማ ጥቅሞች እንዲያጡ፣ የተሰጧቸውን መኪኖችና ሌሎችም መገልገያዎች እንዲመልሱ የተደረጉበትን መንገድ ኮንነዋል፡፡

በመሆኑም ተነሺዎቹ አመራሮች ጉዳዩን ለምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅርበው እንዲታይላቸው ለማድረግ ሊያገኟቸው እንዳልቻሉና አሁንም ከማነጋገር እንደማይቦዝኑ ገልጸዋል፡፡ ከንቲባዋን አነጋግረው ምላሽ ካጡም ከከተማው ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ባሻገር እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ድረስ በመሄድ አቤቱታቸውን ለማሰማነት መዘጋጀታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ስለተነሱት ኃላፊዎች ጉዳይ የከንተባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊውን አቶ ኤፍሬም ግዛውን፣ እስካለፈው ዓርብ ምሽት ማለትም ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣው ወደ ማተሚያ ቤት ከማምራቱ በፊት በስልክ ለማነጋገር የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊዋን አልፊያ ሐጂ ዩሱፍም ከሪፖርተር ተጠይቀው ስለጉዳዩ የሚያውቁት መረጃ እንደሌለና አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጡበት አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...