Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

መንግሥት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት እንደሚያቆም አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

– ሰመራ ፓርክ ብቻ በመንግሥት ይገነባል

መንግሥት የኢንዱስትሪ  ፓርኮች ግንባታ ሙሉ ለሙሉ እንደሚወጣ  የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።  
የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሯ ሌሊሴ ነሜ የሦስት ወራት የተቋሙን አፈጻጸም በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ወቅት እንዳስታወቁት፣ ከእንግዲህ በመንግሥት የሚገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ከመገንባት በመውጣት ለግሉ ዘርፍ እንደሚተው አስታውቀዋል።   
በአሁኑ ወቅት በመንግሥት ግንባታው የሚካሄደው የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ እንደሆነም ጠቅሰዋል።  
ከዚህ በፊት በነበሩ የመንግሥት ዕቅዶች መሠረት የግሉንም ጨምሮ 30 የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚገነቡ አስፍረው ነበር።  
በሌላ በኩል በቅርቡ የተመረቀውን የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ ለሆንግ ኮንግ ኩባንያ መከራየቱን ኮሚሽነሯ ገልፀዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች