Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየደኅነት ሥጋት በሳዑዲ ያሉ ኢትዮጵያዊ እስረኞችን ለማምጣት እንቅፋት መሆኑ ተገለጸ

የደኅነት ሥጋት በሳዑዲ ያሉ ኢትዮጵያዊ እስረኞችን ለማምጣት እንቅፋት መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ እየተደረገ ቢሆንም፣ የተቀሩትን ለማስመለስ ለሚደረገው ጥረት የደኅንነት ሥጋትና አንዳንድ ዓለም አቀፍና የመነሻ አገር ሕጎች እንቅፋት እንደሆኑ ተገለጸ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር) ዓርብ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ 955 ዜጎችን በቅርቡ ከሳዑዲ ዓረቢያ ማስመጣት ተችሏል፡፡ አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን አስለቅቆ ለማምጣት በርካታ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል

ይሁንና በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ እንደሚገኙ እንደሚታወቅ፣ ነገር ግን የታሳሪዎችን ማንነት የማረጋገጥ ሥራ ስለሚጠይቅና ይኼም ከደኅንነት ጋር በቀጥታ ስለሚገናኝ እስካሁን ዜጎች በእስር እንደሚገኙ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የመነሻ አገሮች (ሳዑዲ ዓረቢያ) እና በዝርዝር ያልጠቀሷቸው ዓለም አቀፍ አሠራሮች፣ ተጨማሪ ዜጎች እንዳይወጡ ጫና እንደፈጠረ አስታውቀዋል፡፡

አምባሳደሩ ከሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች አንፃር የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የሚያደርጉት ዜጎችን የመርዳት ጥረት ውስንነት እንዳለበት ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ኤምባሲዎች የሚሠሯቸው የመመለስና የመሳሰሉት የእሳት ማጥፋት ሥራዎች ናቸው፣›› በማለት አስተባብለው፣ በዋናነት በአገር ውስጥ ያሉ የተለያዩ ገፊ ምክንያቶች ላይ ትኩረት ሊረግ ይገባል ብለዋል፡፡

እንደ አምባሳደሩ ገለጻ፣ ገፊ ምክንያቶች የሚሏቸው የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች መሆናቸውን፣ ለዚህም የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ ኢትዮጵያውያን አሁንም ድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን እየማቀቁ እንደሚገኙ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ እስከ 130 ሰዎች ጥቂት መፀዳጃ ቤቶችን በጋራ እየተጠቀሙ እንደሚኖሩ በተደጋጋሚ የተገለጸ ሲሆን፣ እስረኞቹ ደመወዛቸውን ተከልክለው ሳለ የሥራ ፈቃድ ስለሌላቸው ለፖሊስ ታላልፈው የተሰጡ እንደሆኑ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ በኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ የሚደረግላቸው ታሳሪዎች፣ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው አናሳ በመሆኑ፣ ተመልሰው ለመሄድ የሚቋምጡ እንደሆነ በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሳይቀር የተነገረ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሳይቀሩ በፓርላማ ይኼ ጉዳይ ተነስቶ ጥያቄ ቀርቦላቸው ተመላሾችን ማምጣት ላይ ማንነትን የመለየት ሥራ በራሱ አስቸጋሪ መሆኑን፣ ሰነድ አልባ ግለሰቦች ኢትዮጵያዊ ነን ስላሉ ብቻ ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ከባድ እንደሆነ በመግለጽ፣ በተደጋጋሚ መንግሥት ወደ አገር ቤት ካመጣቸው በኋላም ተመልሰው የሚሰደዱ እንዳሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ስምንት ጊዜ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ እያመጣቸው ተመልሰው የሄዱ ግለሰቦች ጭምር እንዳሉ ጠቅሰው ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...