Thursday, April 18, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በሦስት ወራት ከወጪ ንግድ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

አየር መንገድን በከፊል የመሸጥ ውሳኔ እንዲዘገይ ተደርጓል

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የሦስት ወራት ኢኮኖሚያዊ አፈጻጸሞችን በማስመልከት በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፣ በሦስት ወራት ከወጪ ንግድ 499.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታወቁ።

የ2012 ዓ.ም. ዋነኛ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን አስታከው በዘንድሮ የመጀመያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችን ያስታወቁት አቶ አህመድ፣ ከወጪ ንግድ ባሻገር ከታክስና ከሌሎች ምንጮች 80.8 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥ 61 ቢሊዮን ብር ከታክስ ሲሰበሰብ፣ 13 ቢሊዮን ብር ታክስ ካልሆኑ ምንጮች የተገኘ መሆኑን፣ እንዲሁም ዕርዳታና ብድር ቀሪውን የገቢ መጠን መሸፈናቸውን አክለዋል

በወጪ ረገድ 97.7 ቢሊዮን ብር ለክልሎች የሚውለውን የበጀት ድጋፍ ጨምሮ ለፌደራል ባለበጀት ተቋማት ወጪ መደረጉን፣ ይህ ወጪ ከጠቅላላ ለዓመቱ ከተያዘው 22.9 በመቶ እንደሆነ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። ለክልሎች በሚለቀቀው በጀት ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልልን በተመለከተ ጥያቄ ቀርቦላቸው፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት በወሰነው መሠረት እንደሚጸም ገልጸዋል። የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ባካደው ምርጫ ምክንያት ሕገወጥ በመባሉ፣ ሕዝባዊ ተቋማት በሆኑት የከተማና የወረዳ አስተዳደሮች በኩል የሕዝቡ በጀት ተግባር ላይ ይውላል ተብሏል። ‹‹የክልሉ መንግሥት በጀት አይተላለፍለትም፤›› ያሉት አቶ አህመድ አፈጻጸሙ እንዴት እንደሚሆን በዝርዝር እየታየ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ከውጭ በብድርና ዳታ ቃል የተገባ 474.6 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ከዚህ ቀደም ቃል ከተባው ውስጥም 465.6 ሚሊዮን ዶላር በሩብ ዓመቱ መለቀቁን ገልጸዋል። የጀርመን መንግሥት 117 ሚሊዮን ዶላር፣ የጃፓን መንግሥት 13 ሚሊዮን ዶላር መጠታቸውን፣ ለኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ የሚውል 131 ሚሊዮን ዶላር ልዩ ድጋፍ መገኘቱ ተጠቅሷል። መንግሥት የኮሮና ተዕኖን ለመቋቋም ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልገው በማሳወቅ ለዓለም ቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

መንግሥት እያካደው ለው የፕራይቬታይዜሽን ሒደት ስለኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳይ ተጠይቀው እንዳስታወቁት፣ አየር መንገዱን በከፊል ወደ ግል የማዛወሩ ውሳኔ ተፈጻሚነት እንዲዘገይ ተወስኗል። አየር መንገዱ የሚገኝበት የተወዳዳሪነት አቅምና ብቃት፣ የኮሮና ተዕኖን በመቋቋም ያስመዘገበው ውጤት፣ ሠራተኞቹን ሳይበትን በካርጎ ትራንስፖርት ያካካሰበት የተቀዛቀዘው የመንገደኞች ትራንስፖርት ውጤታማነቱንና ጠንካራ አመራሩን ያረጋገጡ ማሳያዎች ተደርገዋል። በመሆኑም መንግሥት አስቀድሞ አየር መንገዱን በከፊል ወደ ግል ለማዛወር ያሳለፈውን ውሳኔ ለወደፊቱ በይደር አቆይቶታል ብለዋል በሌሎች የየብስ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መስኮች የግሉ ዘርፍ በተወሰኑት ላይ እንዲገባ ይደረጋል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በደረቅ ወደብ መስክ መሳተፉ አንዱ እንደሆነ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅትንም በከፊል ከመሸጥ ይልቅ ተቋሙ ከሚሰጣቸው አገልገሎቶች የተወሰኑትን እየተጋሩ የሚሠሩበት አካሄድ ተመራጭ መሆኑን አብራርተዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች