Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለተሰንበት ግደይ የዓለምን የ5,000 ሜትር ክብረ ወሰን በስፔን ሰበረች

ለተሰንበት ግደይ የዓለምን የ5,000 ሜትር ክብረ ወሰን በስፔን ሰበረች

ቀን:

ከዓምናው የዓለም ሻምፒዮና 10,000 ሜትር ሁለተኝነቷ በኋላ፣  ለተሰንበት ግደይ 5,000 ሜትር የመም (ትራክ) ላይ ሩጫ የምንጊዜውም እጅግ ፈጣኗ ሴት ሆናለች። ኢትዮጵያዊቷ ለሰንበት፣ ረቡዕ ጥቅምት 27 ቀን 2013 .. ባደረገችው አስደናቂ ሩጫ 12 ዓመታት በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን በስፔን ቫሌንሽያ ከተማ፣ 14:06.62  በመሮጥ ነው የዓለምን ክብረወሰን መስበር የቻለችው። ይህ ድንቅ ክንዋኔዋ ነው በጥሩነሽ ዲባባ 2008 14:11.15 ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ለመስበር የበቃችው።

ኦሊምፒክ ቻነልና ራነርስ ወርልድ እንደዘገቡት የመጨረሻዎቹን አምስት ዙሮች ብቻዋን የሮጠችው ለተሰንበት፣ ከውድድሩ ፍጻሜ በኋላ ይህ የረዥም ጊዜ ሕልሜ ነው፤ በውድድሩም በጣም ተደስቻለሁ!ብላለች። ይህ በጣም ግሩም ነው፡፡ ከዚህ በፊት ጥሩነሽ ዲባባ ሰበረች፤ አሁን ደግሞ እኔ፡፡” ስትልም አክላለች። የ5,000 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር የኢትዮጵያውያን ሯጮች የፈጣን ሯጭነት ውርስን 22 ዓመቷ ለተሰንበት አስቀጥላለች።

ሌላው የምሽቱ ተጨማሪ  የክብረ ወሰን አስደናቂ ክስተት በቀነኒሳ በቀለ 26:17.53  15 ዓመታት ተይዞ የነበረው 10,000 ሜትር ሪከርድን ዑጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕቴጊ 26:11.02 በመፈጸም መስበሩ ነው። ባለፈው ነሐሴ በተደረገው ዳይመንድ ሊግ በ5000 ሜትርም የቀነኒሳን የዓለም ሪከርድ መስበሩም ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...