Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ልማት ድርጅቶች ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰቡ

ተዛማጅ ፅሁፎች

– ከ21 ድርጅቶች ስኳር ኮርፖሬሽን ብቻ ከስሯል

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የሚቆጣጠራቸው 21 ድርጅቶች 300.5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገኘታቸውን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረ መስቀል አስታወቁ።

አቶ በየነ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፣ በ2012 ዓ.ም ከተገኘው 300 ቢሊዮን ብር ገቢ፣ 55.5 ቢሊዮን ብር ከታክስ በፊት ትርፍ ማስገባት ተችሏል።ለኤጀንሲው ተጠሪ ከሆኑና የትርፍ ድርሻ ከሚጠበቅባቸው ድርጅቶች 13 ቢሊዮን ብር ገቢ መደረጉ ተገልጿል። ከድርጅቶቹ መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 8 ቢሊዮን ብር፣ ኢትዮ ቴሌኮም 4.5 ቢሊዮን ብር ለመንግሥት የትርፍ ድርሻ ክፍያ የፈጸሙ ናቸው።

በውጭ ዕዳ ክፍያ ረገድ፣ 604 ሚሊዮን ዶላር ለውጭ አበዳሪዎች ሲከፈል፣ ግማሹ የኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ ነበር።

ኤጀንሲው ከሚከታተላቸው 21 የልማት ድርጅቶች ዘንድሮ ኪሳራ ያሰመዘገበው ስኳር ኮርፖሬሽን ብቻ እንደደሆነ ታውቋል። ይህም በርካታ ፋብሪካዎቹ በግንባታ ላይ የሚገኙና ውዝፍ ዕዳ ከመያዙ ጋር ተያይዟል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች