Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትቀናት የቀሩት የሁለቱ የጎዳና ላይ ፈርጦች ፍጥጫ

ቀናት የቀሩት የሁለቱ የጎዳና ላይ ፈርጦች ፍጥጫ

ቀን:

የሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮን እና የአሥር ሺሕ ሜትር ባለክብረ ወሰን ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ከኬንያዊው ባለክብረ ወሰን ኪፕቾጌ ጋር መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ፉክክር ሊያደርግ 11 ቀናት ይቀሩታል፡፡

የማራቶን ውድድርን ጠንቅቆ የሚያውቀው የ38 ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያትም ከውድድር ደንበኝነቱ መራቁ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

‹‹በወረርሽኙ ምክንያት ብቻዬን መሥራቴ ለእኔ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ መጥፎ የጉዳት ጊዜንም አሳልፌያለሁ፡፡ በእነዚያ ጊዜያት ወደ ጥሩ አቋሜ ለመመለስ ብቻዬን ልምምድ ሳደርግ ቆይቼያለሁ፤›› በማለት ለኔሽን ስፖርት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ቀነኒሳ የራሱ የመሮጫ መም (ትራክ) በሱሉልታ ያለው፣ በሆቴል ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራ በመሆኑ ከተፎካካሪው ኪፕቾጌ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይኼም ሁለቱም የማራቶን ድምቀቶች በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ላይ መሰማራታቸው ሁለቱም ያለባቸውን ጫና ያሳያል፡፡

ሁለቱ አትሌቶች በሁለት ሰኮንዶች ብቻ የሚለያዩ በመሆኑ የመስከረም 24ቱን ፉክክር ተጠባቂ ያደርገዋል፡፡

የዓለም ክብረ ወሰን

እ.ኤ.አ. 2018 ኤሊዮድ ኪፕቾጌ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ሁለት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ39 ሴኮንድ በመግባት አስደናቂ ችሎታው ማስመስከር ችሏል፡፡ ልክ ከ12 ወር በኋላ ደግሞ ቀነኒሳ በቀለም 2፡01፡41 በማጠናቀቅ ኃያልነቱን አሳይቷል፡፡ ቀነኒሳ ኪፕቾጌ በሮጠበት ተመሳሳይ የበርሊን ጎዳና ላይ የሮጠ ሲሆን የመጀመርያውን አጋማሽ ርቀት ሲያጋምስ ምቾት እንዳልነበረው በወቅቱ ተገልጿል፡፡ ቀነኒሳ ከአጋማሽ በኋላ የነበረው ፍጥነት ግን በርካቶችን ያስደመመ እንደነበር ባለሙያዎች  ይመሰክራሉ፡፡

በጉጉት የሚጠበቀው የሁለቱ አትሌቶች የለንደን ማራቶን ውድድር ሚያዝያ 2012 ዓ.ም. ለማካሄድ ተወጥኖ የነበረ ቢሆንም በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ መስከረም 24 እንዲዛወር ሆኗል፡፡

አሥራ አንድ ቀናት ለቀሩት የለንደን ማራቶን ቀነኒሳ ለተፎካካሪው ኪፕቾጌ ካለው አድናቆት ባሻገር የኬንያ አትሌቶች ለሩጫው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለኔሽን ስፖርት ሳይገልጽ አላለፈም፡፡

‹‹ለኪፕቾጌ ትልቅ ክብር አለኝ፡፡ ለረዥም ጊዜ ተፎካካሪዎች ነበርን፡፡ እሱ ለአትሌቲክሱ ትልቅ አምባሳደር ነው፡፡ ለዛም አከብረዋለሁ፤›› በማለት ቀነኒሳ አድናቆቱን ይገልጻል፡፡

ጥቂት አትሌቶችን ብቻ የሚያሳትፈው ለንደን ማራቶን ውድድር

ቀነኒሳ እነዚህ ታላላቅና ታዋቂ አትሌቶች ጋር ለመፎካከር መዘጋጀቱ ትልቅ መነቃቃት እንደፈጠረለት ይናገራል፡፡ ኪፕቾጌን ኬንያውያኑ የ2016 የሙምባይ ሻምፒዮን ጌዲዮን ኪፕኬተር፣ የሮተርዳም ማራቶን አሸናፊው ማሪሁስ ኪፒሲርምና የአምስተርዳም ባለድል ቪንሰንት ኪቹምባ ያጅቡታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያውያኑ ሙስነት ገረመው፣ ሙሌ ዋሲሁን፣ ታምራት ቶላ፣ ሲሳይ ለማ እና ሹራ ኪታታ ከቀነኒሳ ጎን የሚሰለፉ አትሌቶች ናቸው፡፡ ቀነኒሳ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ፈታኝ የልምምድ ጊዜ እያሳለፈ ቢሆንም የተሻሉ አማራጮችን በመጠቀም ማለትም ጂምናዚየምና ብስክሌትን እንደ አማራጭ እየተጠቀመ መሆኑን ሲገልጽ ውድድሩ ከሚያዝያ ወደ መስከረም መቀየሩ ግን ትንሽ ሥጋት እንዳሳደረበት አልሸሸገም፡፡ ከዚህም ባሻገር በዘንድሮ የማራቶን ውድድር ተመልካቾች አለመኖራቸው የውድድሩን ውበት እንደሚያሳጣም ያስረዳል፡፡

‹‹በእውነቱ ተመልካቾች በየመዳረሻው ድጋፋቸውን በጭብጨባ ቢያሳዩን ለእኛ ልዩ ድጋፍ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ግን ድጋፋቸው በቴሌቪዥን መስኮት እንደማይለየን ተስፋ አደርጋለሁ፤›› በማለት ቀነኒሳ አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡ እንደ ቀነኒሳ አስተያየት ከሆነ ስለሚያጠናቅቁበት ሰዓት እርግጠኛ ሆኖ መናገር ባይችልም ውድድሩ ግን ጥሩ እንደሚሆን ይገምታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...