ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ የብር ኖቶች መቀየራቸውን ይፋ ባደረጉበት መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ሕገወጥ ተግባራትንና ሙስናን፣ ኮንትሮባንድንና የሐሰተኛ ገንዘብ ኅትመት ሥርጭትን ለመከላከል የብር ኖቶች መቀየራቸውን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ማኪያቶ አቅራቢ ነጋዴዎች የአምስት ብር ማኪያቶ ጠጥተው አሥር ብር ጉርሻ የሚሰጡ ሰዎች እየበዙላቸው ሲሄዱ 15 ብር እንደሚያደርጉትም አመልክተዋል፡፡ የዋጋ ግሽበቱን እያመጣ ያለው አላግባብ የታተመውና የተሠራጨው ገንዘብ መሆኑንም ጠቁመው፣ ምርት አቅርቦትን ከማሻሻል በተጨማሪ የብር ኖት ለውጡ ግሽበትን ይቆጣጠራል የሚል እሳቤ መኖሩንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡