የአሥራ ሦስት ወራት ባለጸጋዋ ኢትዮጵያ፣ አዲሱን ዓመት 2013 ዓ.ም. ዓርብ መስከረም 1 ቀን ተቀብላለች፡፡ በዋዜማው አጋጣሚ አዲስ የተገነባው የሸገር ፓርክ የወዳጅነት አደባባይ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በተገኙበት በልዩ ልዩ መሰናዶዎች ተመርቋል፡፡ ከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንትና ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተከናወነው ሥነ በዓል ላይ ታዳጊዎች ኅብረ ዝማሬን ሲያሰሙ፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የአየር ላይ እና የምድር ወታደራዊ ትርዒቶች አሳይተዋል። ምሽት አራት ሰዓት ላይ ርችት የተተኮሰ ሲሆን አገራዊውን ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓትም ተከናውኗል፡፡ ፎቶዎቹ የዕለቱን ሁነት ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -