ነባር የብር ኖቶች ሊቀየሩ ነው
- አዲስ ባለ 200 ብር ኖት ይጨመራል
ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይፋ አድርጓል።
አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ ጨምሮ እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ ይረዳሉ ተብሏል።
በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱት መለያዎች ገንዘብ አመሳስሎ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችን ለማስቀረት ያግዛሉ።