Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ“ምን እስክንሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው?” የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

“ምን እስክንሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው?” የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ቀን:

ከዘጠኝ ወራት በፊት መነሻውን ከቻይና አድርጎ ዓለምን ያካለለው ኮቪድ-19 የተባለው አስከፊ ወረርሽኝ በኢትዮጵያም መገኘቱ በይፋ ከተገለጸበት መጋቢት 2012 ዓ.ም.  እስከ ጳጉሜን መካተቻ ድረስ ከስደስሳ ሁለት ሺሕ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል፡፡ ሕይወታቸውን ያጡ ቁጥርም ወደ አንድ ሺሕ መጠጋቱን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

በተለያዩ የዓለም አኅጉራትም አስከፊው የኮሮና ቫይረስ በሚሊዮን ሰዎችን በሞት እየቀጠፈና በዚያው ልክ ደግሞ ለሕመምና ስቃይ እየዳረገ የሚገኝ ደዌ ሆኗል፡፡

“የኮሮና መከላከያ መንገዶችን በኃላፊነት እንተግብር! ከቁጥር ሳንጎድል በጤና እንሻገር” የሚለው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሰሞኑን ባወጣው የተማፅኖ መግለጫው ላይ እንዳስገነዘበው፣ በዚህ ጊዜ አገሮች በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት ግራ ተጋብተዋል፡፡ የዜጎቻቸውን ሕይወትም ለመታደግ ያልፈነቀሉት ድንጋይና ያልቆፈሩት ጉድጓድ የለም፡፡ ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታም በራቸውን ጥርቅም አድርገው ዘግተዋል፡፡ የዜጎቻቸውን የመንቀሳቀስ መብት ሁሉ ገድበዋል፡፡ አንዱ አገር ከሌላው አገር እንዳይገናኝ የምድርና የአየር ድንበሮችን በመዝጋት የተጀመረው ዕርምጃ በራሳቸው ግዛት ውስጥም ያሉ ክፍለ ሀገራት፣ ዞኖች፣ ሰፈሮች፣ ጎረቤቶች እንዲሁም ቤተሰብ እርስ በእርስ እንኳን በቅጡ የማይገናኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በሽታ በኢኮኖሚ የበለጸጉና በቴክኖሎጂ የመጠቁ አገሮችን ሳይቀር በእጅጉ የፈተነና ብዙዎቹንም የሚይዙትንና የሚጨብጡትን ያሳጣ በሽታ ነው፡፡ በሽታው ሀብታምና ድሃ፣ ዘርና ቀለም፣ ጾታና ዕድሜ ሳይለይ ሁሉንም እንደሰደድ እሳት የሁሉንም ቤት እያንኳኳ ያለ በሽታ ነው፡፡

የአንዳንድ አገሮች ዜጎች የበሽታው አስከፊነት ገብቷቸውና በተግባር ተፈትነው፣ ሕመሙና ስቃዩ ተሰምቷቸው መንግሥታቸው የወሰደውን ዕርምጃ ተቀብለውና አክብረው፣ የመከላከያ መንገዶችን ተግብረው የዜጎቻቸውን ሕይወት ለማትረፍ ሌት ከቀን እየሠሩ ናቸው፡፡

“ምን እስክንሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው?”

የመንግሥት ምላሽና “ጆሮ ዳባ…” ያለው የኅብረተሰብ ክፍል

መንግሥት የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ሕግና ደንብ አውጥቶ ወደ ተግባር ከገባ ወራትን አስቆጥሯል ያለው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጥናት ኢንስቲትዩት፣ ይሁን እንጂ የበሽታው ሥርጭት በእጅጉ እየተስፋፋ፣ የበርካታ ሰዎችንይወት እየቀጠፈ፣ በርካቶች በሕክምና ተቋማት ለቀናትና ለወራት ተኝተው እንዲያሳልፉና ሌሎችን ደግሞ ቤት ውስጥ ሕክምና እና ራስን ለይቶ መቆያ እየተገበሩ ያሉበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡

ቁጥሩ ቀላል የማይባል የኅብረተሰብ ክፍል ደግሞ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ፣ የመከላከያ ዘዴዎችን መተግበር ተስኖትና ምንምይነት የመከላከያ ዘዴዎችን ሳይጠቀም እንዲሁ እንደተለመደው እየኖረ ያለም በመሆኑ ከፍተኛ ዋጋ እንደከፈሉት ሌሎች አገሮች ሆነን ነገሩ ከቁጥጥራችን ውጭ እንዳይሆን ከፍተኛጋት መፍጠሩን በአሳሳቢነቱ ጠቅሶታል፡፡

የአፍና የአፍንጫ ማስክን መጠቀም፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ እጅን በሳሙናና በውኃ አዘውትሮ መታጠብና ሳኒታይዘርን መጠቀም የኮሮና በሽታን ለመከላከል የተቀመጡ ዋና ዋና መንገዶች ናቸው፡፡ ይሁንና መጠንቀቅ ለራስ መሆኑ እየታወቀ አዩኝ አላዩኝ እየተባለ ከፖሊስ ጋር እየተደረገ ያለው የድብብቆሽ ጨዋታ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል ሲልም ጠቁሟል፡፡

በተለይ በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ ይፋ የተደረገው የማኅበረሰብ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ አንድ አካል የሆነውንምክንያት አልሆንም” እናማስክ ኢትዮጵያ”ን አተገባበርን በአንዳንድ አካባቢዎች መሻሻል ቢታይም አሁን ድረስ ማኅበረሰቡ በታሰበው መልኩ ተግበራዊ እያደረገው አይደለም ሲልም አፅንዖት በመስጠትም አጠቃላይ ገጽታውን እንደሚከተለው ያብራራዋል፡፡

“በእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ማስክን በአግባቡ በመጠቀም ያለው ደረጃ ከከተማ ከተማ ከገጠር ገጠር በእጅጉ ይለያያል፡፡ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛን በአግባቡ የሚያደርጉ ሰዎች በቁጥር ጥቂቶች ናቸው፡፡ እጅግ የሚበዛው ሰው ደግሞ ፈጽሞ ማስክ የማይጠቀም ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አለማድረጋቸው አያስደነግጣቸውም፣ ቅፍፍም አይላቸውም፡፡ ይባስ ብለው ማስክ ያደረገውን ሰው ሲጠራጠሩና ሲዘባበቱበት ይታያሉ፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ለይስሙላ ማስክ የሚያደርግና ማስኩን አገጩ ሥር ወትፎ ፖሊስ አየኝ አላየኝ እያለ የሚያደርግ ነው፡፡

 “አንዳንዱ የኮሮና ቫይረስ በኪስ ይገባ ይመስል ለምን ማስክ አታደርግም ሲባል፣ ይኸውና ብሎ ከኪሱ አውጥቶ ያሳያል፡፡ ለምን ማስክ አታደርግም ሲባል ለድብድብ የሚጋበዝም አይጠፋም፡፡

“በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንደሰማነው የኮሮና ወረርሽኝ በሽታ ሥርጭት ከቁጥጥር ውጭ በሆኑባቸው አንዳንድ አገሮች የቤተሰብ አባላትን በሙሉ ለዘር እንኳን ሳያስቀር ፈጅቷቸዋል፡፡ ብዙዎቹ ለበሽታው በነበራቸው የተሳሳተ ግምትና የመከላከያ ዕርምጃዎችን በመተግበር ላይ ባሳዩት ቸልተኝነት ቀስ በቀስ በሽታው ቤታቸው ድረስ ገብቶ እስኪጨርሳቸውና የሕክምና ዕርዳታ ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ በየጎዳናው አስክሬናቸው ወድቆ ለመቅበር ሲቸገሩ ሰምተናል፣ ተመልክተናልም፡፡ በዚህም ሳቢያ ዜጎቻቸው ለከፍተኛ ጭንቀት፣ ፍርሃትና ድብርት ተጋልጠዋል፡፡

“እኛ ከእነዚህ አገሮች ትምህርት ወስደን የመከላከያ ዘዴዎችን በመተግበር ራሳችንን፣ ቤተሰቦቻችንና ማኅበረሰባችንን ጭምር ከበሽታው መከላከል የምንችልበትን ወርቃማ ጊዜ በከንቱ እያሳለፍነው ነው፡፡ በዚህ ምክንያትም የበሽታው ሥርጭት ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ወደ መሆን እንዳይሸጋገር የሚልጋት ፈጥሯል፡፡ ይሁንና አሁንም ጊዜው አልመሸም፡፡ ተገቢውን የመከላከያ መንገዶችን ከተገበርን ከችግሩ የምንወጣበት ዕድል አሁንም በራሳችን እጅ ላይ ስለሆነ ከወዲሁ ልንነቃ ይገባል፡፡

“እጅግ የሚገርመው ነገር ደግሞ በሽታው ጭራሽ የለም የሚል አመለካከት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸው ነው፡፡ በየሠፈሩ በበሽታው ተይዘው በሕመም ሲሰቃዩና ሕይወታቸው ሲያልፍ እየታየ በሽታው የለም እንደማለት ምን የሚያስገርም ነገር ሊኖር ይችላል? እነዚህ ሰዎች ግን በሽታው ስለመኖሩ እንዲያውቁና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ራሳቸውና የቤተሰባቸው አባላት ለበሽታው ተጋልጠው ሲሰቃዩና ሕይወታቸው ሲያልፍ ካላዩ አያምኑም ማለት ነው? ከዚህ በላይስ ምን እስክንሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው?

“እስካሁን በሽታው መቼ እንደሚቆም ማንም መረጃ የለውም፡፡ የበሽታው መድኃኒትም እስካሁን በውል አልታወቀም፡፡ በአሁኑ ወቅት ከፈጣሪ በታች ብቸኛው መንገድ ቢኖር የመከላከያ መንገዶቹን በጥብቅ ዲስፕሊን መተግበርና መተግበር ብቻ ነው፡፡ አዎ ለራሳችን፣ ለቤተሰቦቻችንና ለማኅበረሰባችን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መያዝ ምክንያት ባለመሆን የኮሮና ቫይረስ በሽታን መከላከል ስንችል መሆኑን አውቀን ወደ ተግባር መሸጋገር ይገባናል፡፡

አራቱ የ‹‹መ›› ሕጎች

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...