Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየባህል ሕክምና ትምህርትን በትምህርት ተቋማት

የባህል ሕክምና ትምህርትን በትምህርት ተቋማት

ቀን:

በሔለን ተስፋዬ

ዘመናዊ ሕክምና በፊትዋነኛነት ተደራሽ የነበረው ባህላዊ ሕክምና ነው፡፡ ዘመናዊው ሕክምና ቢመጣም ባህላዊ ሕክምናም መሳ ለመሳ እየሄደ መሆኑ ይታያል፡፡ በአንዳንድ አገሮች አማራጭ በሌሎች ደግሞደጋፊ የሕክምና ዘርፍነት ተቀምጧል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት (ዓጤድ) ዕይታ ባህላዊ ሕክምና የተለያዩ ባህሎችን፣ እምነቶችንና ንድፈ ሐሳቦችን መሠረት ያደረጉ ጤናን ለመጠበቅ፣ በሽታን ለመከላከል፣ አካላዊ ወይም አዕምሯዊ ሕመምን ለማከም የሚውሉ ብዙ ነገሮችን ያካትታል፡፡

... 2006 ላይ በኢትዮጵያ ጆርናል ኦፍ ሔልዝ ዴቨሎፕመንት ላይ የወጣ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ 80 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ዛሬም በመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት የሚያገኙት በባህላዊ ሕክምና ነው፡፡

ብዙኃን ኢትዮጵያውያን የባህል ሕክምናን መጠቀማቸውን  ግምት ውስጥ በማስገባት በዘመናዊ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት በትምህርት መታገዝ እንዳለበት ዩቶፕያ አገር በቀል የባህል ሕክምና አዋቂዎች የሙያ ማኅበር በቅርቡ አሳስቧል፡፡

እንደ ማኅበሩ እምነትና አቋም፣ የባህል ሕክምና እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ከመጀመርያ ደረጃ ትምህርት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሰጠት አለበት፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም ዋለልኝ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በየጊዜው ኢትዮጵያ ያጋጥሟት በነበሩ ወረርሽኝና ሌሎች ተዛማች በሽታዎች ኅብረተሰቡ እንዳይጠቃ የባህል መድኃኒት አዋቂዎች ቅጠል በጥሰውና ሥር ምስው ለችግሮች መፍትሔ ይሰጡ ነበር፡፡ አሁን ላይ እየተመናመነ የመጣውን የዕውቀት ሽግግር እንዲያንሰራራ  በትምህርት ሥርዓት ውስጥ መካተት አለበት፡፡

ማኅበሩ ባህላዊ የሕክምና ከዘመናዊ ትምህርት ጋር በማጣመር ለማኅበረሰቡ የተሻለ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ከሚመለከታቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር ሕክምናውን ለማዘመን እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን የባህል ሐኪሞች የሚዲያ ባለሙያዎች በጥምረት እየሠራ ይገኛል፡፡

እንደ አቶ አብርሃም አገላለጽ፣ ማኅበሩ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘ ሲሆን ሙያተኞች ኃላፊነታቸው በአግባቡ እንዲወጡ የሙያ ማኅበሩ አጫጭር ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት በጥናት ላይ የተመሠረተ የባህል ሕክምና ለኅብረተሰቡ እንዲደርስ ማድረግ ከተሰጠው ተልዕኮ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ቻይናና ኮርያን ጨምሮ በርካታ አገሮች ያላቸውን አገር በቀል ዕውቀቶች በማዘመን ከአገራቸው አልፎ ለዓለም አበርክተዋል ያሉት የማኅበሩ የበላይ ጠባቂ የሚዲያ ባለሙያው አቶ ጥበቡ በለጠ፣ ኢትዮጵያም ከእነዚህ አገሮች የማይተናነስ ዕውቀቶች ቢኖራትም ረዥም ዓመታትን ያስቆረው አገር በቀል ዕውቀት በአብዛኛው ባለመዘመኑ ትኩረት ተነፍጎት በመቆየቱ ተዘንግቷል፡፡

በአገር በቀል የሕክምና ዕውቀት ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ ወደ ዘመናዊነት ለማምጣት ትልቅ ዓላማን አንግቦ የተነሳ ማኅበር መሆኑንም የበላይ ጠባቂው አስረድተዋል፡፡

ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መድኃኒት አለን የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ጊዜ ሳይወስድ ዕድል በመስጠት በምርምር ጥናት በማዘመን ወደ ተግባር እንዲገቡ ማገዝ ያስፈልጋል ያሉት የበላይ ጠባቂው፣ የባህል ሕክምና በዘመናዊ ትምህርት አለማዘመን ኢትዮጵያ ትልቁ የሳተችው ነገር ነው ያሉ ሲሆን፣ አሁንም ችግሩን ለመቅረፍ ሁሉም ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል ብለዋል፡፡ በአገር በቀል ዕውቀቶች ዙርያ የጤና፣ የትምህርት፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴሮች  ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባዔዎች እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የባህል ሕክምና ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ እህተ ማርያም ሻምበል በበኩላቸው እንደገለጹት፣ ባህላዊ ሕክምናን በጥናትና ምርምር ለማሳደግ የጤና ፍኖተ ካርታን ጨምሮ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት የባህል ሕክምናን ለማዘመን እየተሠራ ነው፡፡ በ2013 ዓ.ም. የባህል ሕክምናን ለማዘመንና ለመደገፍ የሥልጠና ግብዓት እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

አስተባባሪዋ አያይዘውም የባህል ሕክምና ዕውቀትን ለጤና ባለሙያዎች ከማሳወቅ ባለፈ ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ እንዲካተት በባህል ሕክምና ስም ያሉ ማኅበራት መቀናጀት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

1980ዎቹ ጀምሮ ባደጉም ሆነ በማደግ ላይ በሚገኙ አገሮች የባህላዊ ሕክምና ይበልጥ እየተስፋፋ በመሄዱና ዘመናትን ተሻግሮ ዛሬም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ባህላዊ ሕክምና የኅብረተሰብ ጤናን በመጠበቅ ረገድ ሚናው ይጠናከር ዘንድ የዓለም የጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. ከ2014 እስከ 2023 የሚተገበር የባህላዊ ሕክምና ስትራቴጂን ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ስትራቴጂውም የባህላዊ ሕክምና ሚናን የሚያጠናክሩ ፖሊሲዎችና ዕቅዶች በአባል አገሮች እንዲወጡና እንዲተገበሩ ያስችላል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...