በ1982 ዓ.ም. የተመሠረተው አንጋፋው የሐዋሳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማሳደግ፣ በሦስት ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የተቀረጸው የሁለት ቢሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ጳጉሜን 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ ተደርጓል፡፡ የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች ምርቃት በተስተጋባበት መድረክ፣ ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ምቹ የሆኑ የ14 ሼዶች ግንባታ ሥራ የፌዴራልና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ አስጀምረዋል፡፡