Sunday, June 4, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

ክቡር ሚኒስትሩ የድካም ስሜት በተሰማቸው ቀን በጊዜ ከቢሮ ወጥተው በመኖሪያ ቤታቸው በረንዳ ላይ ቡና እያስፈሉና ቀዝቀዝ ያለ የምሽት አየር እየተቀበሉ ከባለቤታቸው ጋር የማውጋት ልማድ ቢኖራቸውም፣ ዛሬ ግን የባለቤታቸው ወግ ደረቅ ሆኖባቸዋል. . . አልፎ አልፎም በነገር ወጋ እያደረጓቸው ነው

[ክቡር ሚኒስትሩ የድካም ስሜት በተሰማቸው ቀን በጊዜ ከቢሮ ወጥተው በመኖሪያ ቤታቸው በረንዳ ላይ ቡና እያስፈሉና ቀዝቀዝ ያለ የምሽት አየር እየተቀበሉ ከባለቤታቸው ጋር የማውጋት ልማድ ቢኖራቸውም፣ ዛሬ ግን የባለቤታቸው ወግ ደረቅ ሆኖባቸዋል. . . አልፎ አልፎም በነገር ወጋ እያደረጓቸው ነው]

  • ዛሬ ምን ሆነሻል ቁጣ ቁጣ እያለሽ ነው?
  •  ምን እሆናለሁ እኔ አንተን ልጠይቅህ እንጂ? 
  • [እያዛጉ]. . . እኔ እንኳን ድካም ቢጤ ተሰምቶኝ ነው፡፡ ዛሬ የጉልበት ሥራውም አልቀረኝ።
  • ምን ገጠመህ?
  • የቢሮ ዕድሳቱ።
  • አዬ. . . እሷን እንኳ ተዋት. . . የእኔን ጥያቄ ለማፈን የፈጠርካት ምክንያት ነች።
  • ምንድን ነው ደግሞ ያንቺ ጥያቄ?
  • ይኸው. . .ጥያቄው እንኳን ምን እንደሆነ ዘንግተኸዋል። ስንት ጊዜ ነው የተጀመረው ቤት ቶሎ ይጠናቀቅ እያልኩ ስጠይቅ የነበረው? አንተ ግን ምክንያት እየፈጠርክ ታልፈዋለህ. . . ዛሬ ደግሞ ጭራሹኑ ዘንግተኸዋል። ተው ስማኝ. . .  ተው የሚመጣው አይታወቅም፡፡
  • እኔም መቼ ሊመጣ ይችላል የሚለው ነው ሥጋት የፈጠረብኝ?
  • ይኸው. . . አሁንም አጠገቤ ያለው በድንህ ነው። ለመሆኑ ማነው የሚመጣው?
  • አለቃ ነው. . .ዋናው አለቃዬ? 
  • እ. . . ለምንድን ነው ታዲያ በድንገት የሚመጣው? 
  • በአሳቻ ቀን ጉብኝት የማድረግ አባዜ ይዟል፡፡ መቼና የት እንደሚመጣ እንኳን አይታወቅም፡፡ ነገ የእኔ ተራ ሆኖ ቢመጣና የቢሮ ዕድሳቱ ገና እየተጀመረ መሆኑን ቢያይ ምን ይለኛል? . . . መቼም እንደ ጠላት ነው የሚቆጥረኝ። 
  • ለምን እንደ ጠላት?
  • ሌሎቹ እንደ ተሾሙ ነው ቢሮ የሚያድሱት. . . እኔ ይኸው ዓመት ሞላኝ. . . ለውጡ አልገባህም ብሎ እንደሚበሳጭ ይሰማኛል. . . ኧረ እንዲያውም ከቦታው ባያነሳኝ ነው?
  • በሌላ ጉዳይ ተጠምጄ ነው . . . ቅድሚያ ትኩረት የሰጠሁት ሥራ ላይ ተጠምጄ ነው ብለህ አታስረዳውም?
  • የማይሆነውን?
  • ለምን አይሆንም? 
  • የቢሮ ዕድሳት ቅድሚያ እንድትሰጡ ተብሎሁሉም ካቢኔ አባላት አቅጣጫ ተስጥቷል።
  • አቅጣጫ ለቢሮ ዕድሳት!?
  • ለውጡ ከቢሮ መጀመር አለበት. . . ቢሮውን ያለወጠ አገር መለወጥ አይችልም በሚል ዕሳቤ ነው፡፡
  • ዕሳቤው ላይ መጠነኛ ማሻሻያ አድርጌ ነው በለዋ?
  • ምን ብዬ?
  • ለውጡ ከቢሮ ይጀመር አይደል የሚለው ዕሳቤው?
  • እህ. . .
  • ለውጡ ከቤት ይጀመር ብለህ አሻሽለዋ?
  • እያፌዝሽ ነው?
  • ኧረ እኔ. . .  ከቢሮ ስትመለስ ቤትህ ነውምትገባው ከሚል ዕሳቤ ነው። 

[ሚኒስትሩ ተበሳጭተው ባለቤታቸውን ጥለው ወደ መኝታ ክፍላቸው ገቡ። አፍታም ሳይቆይ የእጅ ስልካቸው ጠራ። አሜሪካ የሚገኘው የረዥም ጊዜ ወዳጃቸው ነው]

  • እንዴት አሉ ክቡር ሚኒስትር ?
  • ዛሬ ደግሞ ክቡር ሚኒስትር አልከኝ?
  • ስለሚገባዎት ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ማለትህ ነው?
  • ሰሞኑን አይደለማ የተሾሙት . . . የሰሞኑ ተሿሚ ቢሆኑ አልልዎትም ነበር፡፡
  • ለምን?
  • ፓርላማ ቀርቦ ያልተሾመና መሃላ ያልፈጸመን ተሿሚ ክቡር ሚንስትር ማለት አይከብድም? 
  • ከዚህ ቀደም መሃላ ስለፈጸሙ እኮ ነው?
  • ከዚህ ቀደም የፈጸሙት መሃላ ይከተላቸዋል ነው? 
  • ከሚደጋገም አይሻልም? ከሥልጣን ሥልጣን የተሸጋገረን በየጊዜው ማስማል ምን ይጠቅማል? 
  • መሃላ ብቻ አይደለም፡፡ የሕግ ጥሰት የተፈጸመበት ሹመት ነው፡፡
  • እንዴት?
  • ሚኒስትር የመሾም ሥልጣን የፓርላማው እንደሆነ በሕገ መንግሥቱ ተደንግጓል፡፡ ስለዚህ የሕግ ጥሰት ነው። 
  • እሱስ ልክ ነህ፡፡
  • ስለዚህ ሹመቱ እንዳልተደረገ የሚቆጠር፣ የማይፀናና ተፈጻሚነት የሌለው ነው፡፡
  • የድሮ ጨዋታዎችህን አስታወስከኝ [እየሳቁ] ለነገሩ ማን ያውቃል እንደዚያም ሊሆን ይችላል፡፡ 
  • እንዴት ? 
  • መሃላ እንዲፈጽሙ አለመደረጉ ሚስጥራዊ መልዕክት ይኖረው ይሆናላ! 

[ክቡር ሚኒስትሩ ዘወትር እንደሚያደርጉት ከሁሉም ሠራተኛ በፊት ቀድመው ቢሯቸው በጠዋት ገብተዋል። ቢሮ ከገቡ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ጸሐፊያቸው ፋይሎችን ይዛ ወደ ሚኒስትሩ ቢሮ ገባች። ጸሐፊዋ የአፍ መሸፈኛ ማስክም ሆነ የእጅ ጓንት አለማድረጓን የተመለከቱት ሚኒስትሩ በግራ መጋባት እየተመለከቷት. . .]

  •  እንዴ  እዚያው ባለሽበት  ወደዚህ እንዳትቀርቢ፡፡
  • ምነው ክቡር ሚንስትር? 
  • ያመጣሽውን ፋይል ከጠረጴዛዬ ላይ በፍጥንት አንሺ. . . [እንዳትቀርባቸው ከመቀመጫቸው ተነስተው ራቅ አሉ]
  • ምን ሆነሻል ዛሬ የታለ ማስክ ያደረግሽው?  የእጅ ጓንትስ ለምን አላደረግሽም? 
  • አልሰሙም እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምኑን?
  • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማብቃቱን፡፡ 
  • እና አዋጁ እንጂ ቫይረሱ አበቃ?
  • እንደዚያ ማለቴ አይደለም፡፡ ቫይረሱ ከእርስዎ አይመጣብኝም ብዬ ነው፡፡ 
  • አሁን ውጭልኝ!

[ነገሩ ያሳሰባቸው ሚኒስትሩ ጉዳዩ የሚመለከተው ወዳጃቸው ሚኒስትር ዘንድ ደወሉ] 

  • እኔ ምልህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳታችሁ ተገቢ አልመሰለኝም፡፡
  • ለምን? 
  • ሕዝቡ አዋጁ አብቅቷል ብሎ ጥንቃቄውን ትቶታል እኮ፡፡
  • በእርግጥ አሳሳቢ ነው፡፡ ግን አዋጁ ቢኖርም ሕዝቡን በበዓል ወቅት ማስገደድ አይቻልም፡፡
  • እህ. . .
  • የበዓል ወቅት ባይሆንም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስም ነው ያተረፈልን፡፡ 
  • እንዴት አልገባኝም? 
  • ከጅምሩ አዋጁን መቼ ማስፈጸም ቻልን? በደቡብ የተቃውሞ ሠልፍ ብሎ ሕዝቡ ይወጣል በስተ. . .
  • ተወው ገባኝ፡፡
  • ምኑ? 
  • በእንጥልጥል የተውከው ምን እንደሆነ፡፡
  • ምንድነው?
  • የሰሜኑ ምርጫ፡፡
  • ምን ምርጫ አለን ታዲያ?! 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

ኢትዮጵያ በ2023 የሚኖራት የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለ18 ቀናት ግዢ መፈጸሚያ ብቻ እንደሚሆን አይኤምኤፍ ተነበየ

ኢትዮጵያ በ2023 የሚኖራት የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለ0.6 ወር ወይም...

ጦርነቱና ሒደቱ

ሦስት ሳምንታት ያስቆጠረው ሦስተኛው ዙር የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አሁንም...

ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ አበባን ንግድና ዘርፍ ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት በተደረገው ምርጫ አሸነፉ

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት፣...

መንበሩ ካለመወረሱ በስተቀር መፈንቅለ ሲኖዶስ መደረጉን ቤተ ክህነት አስታወቀ

ቅዱስ ሲኖዶስ ከነገ ጀምሮ ውይይት እንደሚጀምር ተነገረ ‹‹እኛ ወታደርም ሆነ...
- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...

ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው ራሚስ ባንክ ዛሬ ሥራ ይጀምራል

በኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ አምሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው ‹‹ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ሕዝባችንን እናሻግራለን›› የሚለውን የቴሌቪዥን ዜና ተመልክተው ለብቻቸው ሲስቁ አገኟቸው]

ስልክ እያወራሽ ነበር እንዴ? ኧረ በጭራሽ... ምነው? ታዲያ ምንድነው ብቻሽን የሚያስቅሽ? አይ... በቴሌቪዥኑ የሚቀርበው ነገር ነዋ። ምንድነው? ድሮ ድሮ ዜና ለመስማት ነበር ቴሌቪዥን የምንከፍተው፡፡ አሁንስ? አሁንማ ቀልዱን ተያይዘውታል... አንተ ግን በደህናህ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ስልካቸው ጠራ። ደዋዩ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ኃላፊ እንደሆኑ ሲነገራቸው የስልኩን መነጋገሪያ ተቀበሉ]

ሃሎ፡፡ እንዴት አሉ ክቡር ሚኒስትር። ደህና ነኝ። አንተስ? አስተዳደሩስ? ሕጋዊ ሰውነታችን ተነጥቆ እንዴት ማስተዳደር እንችላለን ክቡር ሚኒስትር? ለዚህ ጉዳይ እንደደወልክ ገምቻለሁ። ደብዳቤም እኮ ልከናል ክቡር ሚኒስትር፡፡ አዎ። ሁለት ደብዳቤዎች ደርሰውኛል።...

[ክቡር ሚኒስትሩ አየር መንገዱ ወጪ ቆጣቢ የሥራ እንቅስቃሴ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ግኝቱን በሚያሳድግበት ሁኔታ ላይ ከተቋሙ ኃላፊ ጋር እየተወያዩ ነው]

ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ትልቁ ወጪያችን ለነዳጅ ግዥ የሚውለው ነው። ክቡርነትዎ እንደሚገነዘቡት የዩክሬን ጦርነት የዓለም የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ አሻቅቧል። ቢሆንም አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር ውስጥ...