Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየዘመን መለወጫ ሸመታ በዘመነ ኮሮና

የዘመን መለወጫ ሸመታ በዘመነ ኮሮና

ቀን:

በሔለን ተስፋዬ

ዕንቁጣጣሽ እየመጣች ነው፡፡ አዲሱን ዓመት 2013 ለመቀበል ሁለት ቀኖች የቀሩት ሲሆን፣ ሰሞኑን ኅብረተሰቡ አሮጌውን ዓመት ሸኝቶ አዲሱን በልዩ ልዩ መሰናዶዎች ለመቀበል ሽር ጉድ እያለ ነው፡፡

ይሁን እንጂ አቀባበሉ እንደ ቀደሙት ዓመታት ዋዜማዎች አይደለም፡፡ ለምን ቢሉ ከመንፈቅ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው ዓለም አቀፉ ወረርኝ የኮሮና ቫይረስ ጥላውን አጥልቶበታልና፡፡ ከስድስት ወራት በላይ ባስቆጠረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተመረመረው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከል 60 ሺሕ የሚሆኑት በበሽታው የተያዙ ሲሆን፣ 940 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ይህ በመሆኑ መንግሥታዊ አካላት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ኅብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር በተደጋጋሚ በማሳሰባቸው በምልዓት ባይሆንም መተግበሩ አልቀረም፡፡

ወረርሽኙ እየጨመረ በመምጣቱ የዘመን መለወጫ በዓልን ለመቀበል ከዚህ ቀደም ይደረጉ የነበሩ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ዘንድሮ ለመከናወን አልታደሉም፡፡

ጠንካራው ክረምት እየተገባደደ አዲስ ዘመን የሚደረገውን ጉዞ ለማጀብ ዓምና እና ካቻምና የነበሩት የኤግዚቢሽንና የባዛርና የሙዚቃ መሰናዶዎች በወረርሽኙ ምክንያት አልተዘጋጁም፡፡

ይሁን እንጂ የአዲስ ዓመት ብሥራትን የሚያውጁ ባህላዊ ሙዚቃዎች በአዲስ አበባ ከተማ መሰማታቸው ግን አልቀረም፡፡ የዕንቁጣጣሽ መለያ የሆነችው የኢትዮጵያ ብርቅዬ አበባ ‹‹ዓደይ አበባ›› በፋብሪካ ውጤት በጌጣ ጌጥ መልክ ያቀረቡ በየሕንፃዎቻቸው የለጠፉ ቢኖሩም፣ በአብዛኛው በከተማይቱ የሚታየው ባለቢጫ የሱፍ አበባ እንደ ዓምናው ሁሉ ዘንድሮም ለገበያው ቀርቧል፡፡

ገበያው እንዴት ሰነበተ?

ሪፖርተር በተለያዩ የገበያ አዳራሾች፣ አትክልት ተራዎች ቅኝት እንዳደረገው የምግብ ዘይት ዋጋ በሁሉም በሚባል ደረጃ ቅናሽ ታይቶበታል፡፡ ቀደም ሲል እስከ 390 ብር ይሸጥ የነበረው አምስት ሊትር ዘይት ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ ከተፈቀደ በኋላ በ320 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

ዶሮ ከ350 እስከ 500 ብር፣ የሀበሻ ዕንቁላል እስከ ሰባት ብር የፈረንጅ ከሆነ እስከ ስድስት ብር እየተሸጠ ሲሆን፣ ዓደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ባለው የበግ ተራ ገበያ ዝቅተኛው የበግ ዋጋ 2,000 ብር ከፍተኛው 6,000 ብርና ከዚያ በላይ እየተሸጠ መሆኑን ነጋዴዎች ይናገራሉ፡፡

በአዲሱ ገበያ አካባቢ የተፈጨ በርበሬ በኪሎ 240 እና 250 እየተሸጠ ሲሆን፣ ዛላው በርበሬ ግን ከ180 እስከ 200 ብር ለሸመታ ቀርቧል፡፡ መካከለኛው 350 ብር፣ ለጋው 320 ብር፣ ኮረሪማ በኪሎ 200 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት እስከ 120 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል በሾላ ገበያ የቅቤ ዋጋ ለጋው ከ290 እስከ 310 ብር፣ መካከለኛ ከ300 እስከ 320 ብር፣ የበሰለ ቅቤ ከ260 እስክ 270 ብር እንደሚሸጥ ነጋዴዎቹ ይገልጻሉ፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽሕፈት ቤት አዲስ ዓመትን ተከትሎ የዋጋ ንረት ለመከላከል ለበዓል የሚሆኑ ሸቀጣ ሸቀጦች ማቅረቡን በማኅበራዊ ትሷስር ገጽ አስፍሯል፡፡

በዚህም ጤፍ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ዶሮ፣ ቅቤ፣ ዓይብ፣ ዘይትና ሌሎችም የበዓል ማድመቂያዎች በቅናሽ ዋጋ ማቅረቡን ጠቅሷል፡፡

በዚህም ነጭ ጤፍ በኪሎ 33 ብር፣ ሠርገኛ 37 ብር፣ እንቁላል ከአራት ከሃያ አምስት ሳንቲም እስከ አራት ብር ከሃምሳ ሳንቲም፣ ቅቤ ከ218 ብር እስከ 220 ብር፣ አይብ እስከ 80 ብር እንደሚሸጥ የዋጋ ዝርዝር ተመኑ ያስረዳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...