Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኮሮና ቫይረስ የተያዙት ቁጥር ከ56 ሺሕ በላይ ሆኗል

በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ቁጥር ከ56 ሺሕ በላይ ሆኗል

ቀን:

የሟቾች ቁጥር እስከ ዓርብ 880 ደርሷል

የጤና ሚኒስቴር ነሐሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. በለቀቀው የኮሮና ወረርሽኝ መረጃ፣ በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 23,712 የላቦራቶሪ ምርመራ 1303 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

 በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 56,516 መድረሱን የገለጹት የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር)፣ በዕለቱ 24 ሰዎች ሕይወት በቫይረሱ ምክንያት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 880 መድረሱን ገልጸዋል።

እስከ ነሐሴ 29 ቀን ድረስ ለ994,303 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፣ እስከ ዓርብ ቫይረሱ ያለባቸውናክምና እየተከታተሉ የሚገኙት ሰዎች ቁጥር 23,022 ነው፡፡ የጤና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚሳየው፣ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 20,612 ሲደርስ፣ 315 ሰዎች በፅኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ናቸው።

 

ኮቪድ-19 በወረርሽነት ዓለምን ካካለለ ስምንት ወር ሆኖታል፡፡ በእነዚህ ወራት ሕዝበ ዓለም ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠበቅ፣ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ እንዳይያዝ የጤና ባለሙያዎችና ዓለም አቀፋዊም ሆነ አገራዊ ተቋማት ማስገንዘቢያዎችን ከመስጠት ችላ ያሉበት ጊዜ አልነበረም፡፡

ኮቪድ-19 የሚተላለፍበት መንገድ አስመልክቶ እስካሁን ያለው አቋም፣ በሽታው ከሕመምተኛው አፍንጫ ወይም አፍ በሚወጣ ጥቂት ፈሳሽ አማካይነት የሚተላለፍ መሆኑ ነው፡፡ ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ሲያስነጥስም ሆነ ሲተነፍስ ወደ ሌሎች ከማስተላለፍ ባለፈ፣ ከሕሙማን የሚወጣ ፈሳሽ ያረፈበትን ቦታ የነኩ ሰዎችም በበሽታው በቀላሉ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ከሰዎች ጋር ያላቸው ቅርርብ ከአንድ ሜትር በላይ መሆን አለበት የተባለውም በሽታው በትንፋሽ ስለሚተላለፍ ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩት ቫይረሱ በአየር ውስጥ ሳይሆን በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች የመተንፈሻ አካላት ከወጡ ፍሳሾች ጋር በሚኖር ንክኪ ብቻ የሚተላለፍ መሆኑን ነው፡፡

ይሁን የቅርብ መረጃዎች የኮሮና ቫይረስ በአየር ላይ የመተላለፍ ዕድሉ ሰፊ መሆኑ እየገለጹ ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት በቫይረሱ የመጋለጥ ወይም ያለመጋለጥ ዙርያ የቀረቡ ጥናቶች ላይ እየመከረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በአየር ላይ ቫይረሱ በመቆየት ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ስለሚችል ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

ተተኳሪ ጉዳዮች

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት አገላለጽ፣ ኮሮና ቫይረስ የተለያዩ የቫይረስ ዓይነቶችን የያዘ የቫይረስ ቤተሰብ ነው፡፡ ይህ ቫይረስ በሰዎችና በእንስሳት ላይ በሽታን ያስከትላል፡፡ በሰዎች ላይ የሚከሰተው ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በመጉዳት ከተራ ጉንፋን እስከ ከፍተኛ የመተንፈሻ አካል ችግር የሚያደርስ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...