Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበእንጦጦ በእንጨት ለቀማ የተሰማሩ እናቶችን ተጠቃሚ የማድረግ ጅማሮ

በእንጦጦ በእንጨት ለቀማ የተሰማሩ እናቶችን ተጠቃሚ የማድረግ ጅማሮ

ቀን:

በተመስገን ተጋፋው

የእንጦጦ ደን ለበርካታ እንጨት ለቅመው ቤተሰባቸውን ለሚያስተዳድሩ እናቶች ባለውለታ ነው፡፡ ዳገት ወጥተውና ቁልቁለት ወርደው ልጅ ማዘል ባልታከተው ጀርባቸው እንጨት ተሸክመው የልጆቻቸውን ጉርስ ችለዋል፡፡ እንደ አቅማቸው ልጆቻቸውን ትምህርት ልከዋል፡፡ ይሁን እንጂ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ከመሆን እንዳልተቀየረ የሁልጊዜ ሸክማቸው ምስክር ነው፡፡

እነዚህ በእንጨት ለቀማ የሚተዳደሩ ሴቶች የእንጦጦ ፓርክ ግንባታ በመጀመሩ ምክንያት ሥጋት መግባታቸው አልቀረም፡፡ ሆኖም በፓርኩ ግንባታ ብሎም በኋላ በሚጀምረው አገልግሎት ምክንያት እንዳይስተጓጎሉ እነሱን የሚያሳትፍ ሥራ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸው ነበር፡፡ እሳቸው እንዳሉትም በአካባቢው በእንጨት ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ ሴቶች ከእንጦጦ ሀብት ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ ይመቻቻል፡፡ 

ይህንንም ተከትሎ በእንጦጦ አካባቢ በእንጨት ለቀማ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ እንዲገቡ ሥልጠና መስጠት ተጀምሯል፡፡

በእንጦጦ አካባቢ ላይ ኑሮአቸውን አድርገው በእንጨት ለቀማ 263 እናቶች የሚሳተፉበት ሥልጠና ወደ ሌላ ሥራ እንዲገቡ እንደሚያስችል የፔትኮ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ምሕረት ተክለማርያም ገልጸዋል፡፡

የሴቶችን የሥራ ጫና ለመቀነስ በዘርፉ ላይ ሥልጠናዎችን በመስጠት የሚኖራቸውን የሙያ ክህሎት በማዳበር ተቋሙና ትልቅ እንደሚሠራም ወ/ሮ ምሕረት ተናግረዋል፡፡

አካባቢን የሚበክሉ የውኃ ፕላስቲኮችን በመሰብሰብና መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ ሥልጠና ከመስጠት ባለፈ በዘርፍ ላይ መሥራት እንደሚገባ ሥራ አስኪያጇ ገልጸው፣ በቀጣይም ለሌሎች እናቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሠሩም አክለዋል፡፡

 የአዲስ አበባ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ አማካሪ ወ/ሮ ይብራለም ወልደአብ እንደገለጹት፣ በእንጨት ለቀማ ላይ የተሰማሩና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶችን  አደራጅቶ ወደ ሥራ ለማስገባት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ባለሀብቶች ከፍተኛ ድርሻ ስላላቸው በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በኢትዮጵያም ከፍተኛ ቁጥር የሚይዙት በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች መሆናቸውን ያስታወሱት ወ/ሮ ይብራለም፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በተጀመሩ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች ውስጥ በማካተት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሥልጠናውን ያዘጋጁት የኮባ ኢምፓክትና የፔትኮ ኢትዮጵያ ድርጅት በእንጨት ለቀማ ላይ ላሉ እናቶች የሥራ ዕድል መፍጠራቸው የሚበረታታ  ነው ብለዋል፡፡

በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተጥለው የሚገኙ የውኃ ፕላስቲኮችን በመልቀም መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያደርጉ ድርጅቶችን በመደገፍ አብረው እየሠሩ እንደሚገኙ የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመልሶ መጠቀም ውህደት ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ፀጋዬ፣ ለነዚህም ድርጅቶች ግብዓቶችን ለማቅረብ በየወረዳው ማኅበራትን በማደራጀት እንቅስቃሴዎች መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

በእንጨት ለቀማ ላይ ለነበሩ እናቶችም ወደ እዚህ ሥራ እንዲገቡ መደረጉ ራሳቸውን ብሎም ቤተሰቦቻቸውን በኑሮ እንዲቀይሩ መንገድ ይከፍታል፡፡

ቆሻሻን መልሶ በመጠቀምና ወደ ገንዘብ በመቀየር እናቶች ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸውና በዚህም የአካባቢ ብክለትን መቀነስ እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...