የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ልዩ መገለጫ የሆነችው ትንሿና አሥራ ሦስተኛዋ ወር ጳጉሜን ዛሬ ጳጉሜን 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ብታለች፡፡ ወደ አዲስ ዓመት 2013 ለመዝለቅም መሸጋገርያ ንዑስ ወር ናት፡፡ ለአዲስ ዘመን ማብሰርያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ አበባዎች የሚቆረጡበት በተለይም እንግጫ ነቀላ የሚከናወነው በጳጉሜን ወር ውስጥ ነው፡፡ ትውፊታዊ ሥርዓት ከሚፈጸምባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው ምሥራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶች በተለይም ልጃገረዶች የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎችን በመጫወት ያደምቁታል፡፡ ልጃገረዶች የቆረጡትን እንግጫ፣ ሶሪትና ዓደይ አበባ እንኳን አደረሳችሁ በማለት በየቤቱ በመሄድ ለአባቶች የቆረጡትን እንግጫ በዕንቁጣጣሽ ዕለት ያበረክታሉ፡፡ ፎቶዎቹ ከዚህ ቀደም በምሥራቅ ጎጃም ዞን የአዲስ ዓመት መቀበያ የእንገጫ ነቀላ ክብረ በዓል በተከበረበት ጊዜ የተገኙ ናቸው፡፡