Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከቱሪዝም ዘርፍ ይጠበቅ የነበረው የ5.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ወደ 2.1 ቢሊዮን ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ከሚጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቱሪስቶች የ5.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚገኝ ቢጠበቅም፣ 541 ሺሕ ጎብኚዎች ብቻ በመምጣታቸውና የኮሮና ወረርሽኝም ባስከተለው ተፅዕኖ ሳቢያ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ብቻ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ መከሰት መላውን ዓለም ተፅዕኖ ውስጥ በመክተቱ በተለይም ለኢትዮጵያ ቱሪስት አመንጪ የነበሩ ዋና ዋና አገሮች ድንሮቻቸውን መዝጋታቸው፣ በኢትዮጵያም በከፊል እንቅስቃሴን የመግታት ዕርምጃ መወሰዱ፣ ከውጭ የሚገቡ ጎብኝዎችና ዜጎችም ጭምር በለይቶ ማቆያ ጣቢዎች እንዲቆዩ መገደዳቸውና ፖለቲካዊ ችግሮች ተዳምረው ከዘርፉ ይጠበቅ የነበረው ገቢ እንዲያሽቆለቁል ማስገደዳቸውን ባለሙያዎች አብራርተዋል፡፡

በተሸኘው በጀት ዓመት የተገኘው ገቢ ከዓምናውም ያነሰ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ካቻምና 2.7 ቢሊዮን ዶላር ያስገኘው የቱሪዝም ዘርፉ፣ በየጊዜው በሚነሱ ግጭቶችና በተደጋጋሚ በሚታወጁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ብሎም ኤምባሲዎች በሚያወጧቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያዎች ሳቢያ ሲታወክ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓመት በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝና በፖለቲካ ግጭቶች ሳቢያ አሁንም ከተፅዕኖ መላቀቅ አልቻለም፡፡

ሐሙስ ነሐሴ 21 ቀን 2012 .ም. በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በቱሪዝም ኢትዮጵያ፣ በክልሎች በሚገኙ የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች እንዲሁም በተለያዩ የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳተፎ ተደርጎበታል የተባለ ጥናት ውጤት በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት ተደርጎበታል ጥናቱ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በዘርፉ ላይ ያስከተለውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳት ይዳስሳል።

በሁሉም ክልሎች የሚገኙ 20 ከተሞችን ያካተተው ይህ ጥናት፣ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችና፣ የቱሪስት መድረሻዎችንና አስጎብኝዎችን አካቷል፡፡ በሠራተኞች ላይ የሚያድርሰውን ሥነ ልቦናዊ ጫና እንዲሁም ከዘርፉ ጋር ተሳስረው የሚንቀሳቀሱ ዘርፎችእየደረባቸው የሚገኘውን  ጉዳት ጥናቱ ቃኝቷል። በተለይም የኮከብ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎችና ከኮከብ ደረጃ በታች ሆቴሎች፣ ዋና ዋና የቱሪስት መዳረሻዎች፣ ባህላዊና ዘመናዊ ሬስቶራንቶች፣ አስጎብኚዎችና በመኪና ኪራይ ሥራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች በጥናቱ ተካተዋል።

ከዚህም ባሻገር 2,637 ቋሚ ሠራተኞች በጥናቱ ተካተዋል። ጥናቱ ሦስት ዋና ዋና አመለካች መነሻዎችን መሠረት በማድረግ የጉዳት ደረጃውን እንደገመገመ ሲጠቀስ፣ በተለይም ከዓምናው አማካይ እንቅስቃሴ አኳያ፣ ከወረርሽኙ መከሰት በፊትና እንዲሁም በወረርሽኙ መከሰት ሳቢያ ያጋጠመውን ችግር ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት አኳያ በማነፃፀር ውጤቶቹን አመላክቷል፡፡ በዚህም ወረርሽኙ ከተከሰተበት ከመጋቢት ጀምሮ በሚያዝያና በግንቦት ወር የተከሰተው ሁኔታ ተነፃፅሮ፣ የቱሪዝም ገቢ ምን ያህል እንደቀነሰ ወይም እንደጨመረ ጥናት ተካሂዷል፡፡

ከሆቴሎች አገልግሎት ውስጥ በቀዳሚነት የገቢ ምንጭ የሆነው የመኝታ አገልግሎት ነው፡፡ ይህ ከዓምናው ጋር ሲነፃፀር የ16 በመቶ ቅናሽ አስመዝግቧል፡፡ ከወረርሽኙ በፊት የነበረው አማካይ የአልጋ ሽያጭ ሽፋን ከወረርሽኙ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ61 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱጥናቱ ያጠቁማል። ይህም ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ በባለ ኮከብ ደረጃ ያልተካተቱ ግን የቱሪስት አገለግሎት ሰጪነትን ደረጃ ካሟሉ ሆቴሎች የ61 በመቶ ቅናሽ ሲያሳ፣ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ግን የ71.5 በመቶ የአልጋ ሽያጭ ቅናሽ ማሳየታቸውን ጥናቱ አመላክቷል። የአዲስ አበባ ሆቴሎች የማስተናገድ አቅም የ60 በመቶ ቅናሽ ሲያሳይ፣ በክልል ከሚገኙት ላይ የ63 በመቶ ቅናሽ መመዝገቡን ጥናቱ አመላክቷል።

የሆቴሎችገቢ ምንጭ የሆነው ሌላው የምግብና የመጠጥ አገልግሎት ነው፡፡ ከወረርሽኙ በፊትና በኋላ የታየው አፈጻጸም በንፅፅር ሲታይ፣ የ67 በመቶ ቅናሽ እንዲሁም ወረርሽኙ ከተከስተበት ከመጋቢት ወዲህ የ63 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ተብራርቷል። ይህ በአሁኑ ወቅት እየተሻሻለ በመጣው እንቅስቃሴ ሳቢያ የታየ መጠነኛ ለውጥ ነው፡፡ ከወረርሽኙ በፊት 90 በመቶ ገቢ የነበረው አንድ ሆቴል፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 62 በመቶ ገቢው መቀነሱን፣ የሽያጭ አፈጻጸሙም ከ30 እስከ 20 በመቶ ብቻ ሊሆን እንደሚችል በሆቴልና ቱሪዝም ሥራዎች ማሠልጠኛ ተቋም የምርመራና የማማከር ሥራ ኃላፊ አቶ ማዘንግያ ሽመልስ አብራርተዋል። እንደ አቶ ማዘንጊያ ከሆነ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ከሠራተኞች ከቅጥር የሚከፈል ታክስን ጨምሮ መሰብሰብ የነበረባቸውን ገቢን ጨምሮ፣ የጂምናዚየምና የስፓ አገልግሎቶች እንቅስቃሴዎች የሚያመነጩት ገቢ በ62 በመቶ ቅናሽ አሳይተዋል መንግሥት ማግኘት የሚገባውን የቅጥር ገቢ ታክስ የ24 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ የሚሰበሰበው የመንግሥት ገቢም የ65 በመቶ ቅናሽ ማስመዝገቡ ተብራርቷል የሠራተኞች ቁጥር መቀነሱን ወይም ሠራተኞች ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅማ ጥቅም ሊቀንሰው እንደሚችል ባለሙያው አብራርቷል።

በሌላ በኩል ከሆቴል አገልግሎት ባሻገር የሬስቶራንት እንቅስቃሴም ከዓምናው አኳያ ሲታይ በተለይም በምግብና በመጠጥ ሽያጭ ረገድ የ17 ጭማሪ ያሳየቱበት የተለየ ክስተት ተስተናግዷል፡፡ በሆቴሎች የታየው መቀዛቅዝ በሬስቶራንቶች በኩል ግን የተወሰነገበያ መሻሻል ማስመዝገቡን ለማሳየት ተሞክሯል።

የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎችን በተመለከተምሰሜን ተራሮች፣ በላሊበላ፣ በጎንደር፣ በሐረር፣ በባሌ፣ በደቡብ ኦሞ እንዲሁም በአርባምንጭ ይታዩ የነበሩ የቱሪዝም እንቅስቃሴዎች ዓምና ከነበራቸው አፈጻጸም፣ በተለይ ከጎቢኚዎች ቁጥር አኳያ ሲታይ የ34 በመቶ ቅናሽ ታይቶባቸዋል። የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ያለውን እንቅስቃሴ በሽታው ከመግባቱ በፊት ከነበረው ጋር በማነፃፀር በቀረበው አኃዝ መሠረት፣ በእነዚህ መዳረሻዎች የ88 በመቶ ገቢ ሊታጣ ችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር 69 በመቶ የቱሪስት መዳረሻ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደተዘጉ ተጠቅሷል። ከእነዚህ የተቀሩት ሥራ ላይ ቢሆኑምምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ እንደሌላቸው ጥናቱ አመላክቷል።ሆቴል መስክም 53 በመቶዎቹ ከሞላ ጎደል አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ሲገለጽ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላችው ሬስቶራንቶች ግን ሙሉ በሙሉ ከሥ ውጭ መሆናቸው ተጠቅሷል። ከዚህ አኳያ ሆቴሎችን በተመከለተ የቀረበው አኃዝ እንደሚያሳየው 66 በመቶ በአዲስ አበባ፣ 73 በመቶ በመቀሌ፣ 70 በመቶ በባህር ዳር፣ 66 በመቶ በጅማ፣ በ75 በመቶ በቢሾፍቱ፣ 50 በመቶ በጎንደር፣ 71 በመቶ በአርባምንጭ፣ 60 በመቶሐረር እንዲሁም 90 በመቶሰመራ የሚገኙ ሆቴሎች በሙሉ አቅማቸው መሥራት እንዳልቻሉ ታይቷል።

ኮሮና ቫይረስ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ካስከተለው መደካምና መቀዛቀዝ በተጨማሪ በሠራተኞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የባለሙያዎቹ ጥናት ይጠቁማል።  ከወረርሽኙ በፊት በአማካይ 1,300 ብር በወር ያገኝ የነበረ አንድ ሠራተኛ፣ ከአገልግሎት ክፍያም 600 ብር ጉርሻ ያገኝ እንደነበር ተጠቅሶ፣ በአሁኑ ወቅት ግን 53 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች 200 ብር በታች ለማግኘት መገደዳቸው ተነግሯል። በተጨማሪ 17 በመቶ የሚሆኑ ሠራተኞች ደመወዛቸው እንደተቀነሳቸው ታውቋል።

የኮሮና ወረርሽኝ ካደረሰው ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ባሻገር ሥነልቦናዊ ጉዳቱም የጎላ እንደመጣ እየተነገረ ነው። መንግሥት ወረርሽኙ መከሰቱ ይፋ ከተደረገበት ወቅት ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ቢያደርግም በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት፣ በተሰጣቸው ተስፋና የድጋፍ መጠን ልክ ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ ተነስቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለቱሪዝም ዘርፉ የአምስት በመቶ ወለድ የሚታሰብበት የሦስት ቢሊዮን ብር የሥራ ማስኬጃ ብድር በመፍቀድ ንግድ ባንኮች እንዲያበድሩ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች