Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

‹‹አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስን በዩኒቨርሲቲያችን ማስገባት ከቻልን ትልቁ አብዮት ይሆናል›› ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ፣ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዳንት ናቸው። ተወደው ያደጉት ደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ ሜፀር በምትባል አነስተኛ ቀበሌ ነው። ባደጉባት ሜፀር ቀበሌ ሁሉም የክፍል ደረጃ የያዘ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ምክንያት ትምህርታቸውን የተከታተሉት በከባድ ችግር ነው። ከክፍል ወደ ክፍል ባለፉ ቁጥር በትምህርት ቤት እጥረት ምንያት ከከተማ ከተማ በመቀያየር ትምህርታቸው ተከታተሉ። የደረጃ ተማሪም ነበሩ። በዚህ ሁኔታ የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሺዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በሶሻል አትሮፖሎጂ የማስተርስ ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ውጤት ያዙ። ፒኤችዲያቸውን አሜሪካ ፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ በሶሻል አንትሮፖሎጂ፣ ድረ ዶክትሬታቸውንም ደግሞ ጃፓን ርተው ወደ ገራቸው በመመለስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሻል አትሮፖሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ በመሆን አስተምረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በመሆን አገልግለዋል። በአሁኑ ጊዜ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ናቸው። በጂንካ ዩኒቨርሲቲና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ናርዶስ ፍቃዱ አነጋግራቸዋለች።

ሪፖርተር፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ነው የተቋቋመው? በየትኞቹ መስኮች ትምህርትን ተደራሽደርጋላችሁ?

ፕሮፌሰር ገብሬ፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመው 2010 .. ነው። 2013 .. ለአራተኛ ጊዜ ተማሪዎችን ይቀበላል። የመጀመሪያው ዙር ተማሪዎቻችን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ባይቋረጥ ኖሮ ይመረቁ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲው አራት ኮሌጆችና 14 ዲፓርትመንቶች አሉት። አራቱ ኮሌጆች የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ፣ ማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም የግብርና ሳይንስ ናቸው። የተፈጥሮ ሳይንስና የግብርና ሳይንስ ኮሌጆች እያንዳንዳቸው አራት ዲፓርትመንቶች አሏቸው። የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ እያንዳንዳቸው ሦስት ዲፓርትመንቶች አሏቸው፡፡ 2013 .. አሥር ዲፓርትመንቶችን ለመጨመር ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን። ይህ የዲፓርትመንት ቁጥሩን ወደ 24 ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪም አራት የማስተርስ መርሐ ግብሮችን ለመጨመር ዝግጅት ላይ ነን።

ሪፖርተር፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እንዲመጡ የተደረገበት ምክንያት ምንድነው?

ፕሮፌሰር ገብሬ፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እንድመጣ የተደረገበት አንዱና ትልቁ ምክንያት የዚህ አካባቢ ልጅ ስለሆንኩና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዳንት ለመሆን ብቃት አለው ብለው ስላመኑ ነው። ነገር ግን ጥያቄው ሲቀርብልኝ የቤተሰብ ጉዳይ ስለነበረብኝ በሌላ መንገድ ነበር ለመርዳት የወሰንኩት። ስምምነታችንም የነበረው የቦርድ አባል ሆኜ ለማገልገል ነበር። ነገር ግን ለቦታው ምትመጥን ሰው ነህ በማለትና አሳማኝ ነጥቦችን በማስቀመጥ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብልኝ ለመሞከር ወሰንኩ። ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ በፕሬዳንትነት እያገለገልኩ እገኛለ

ሪፖርተር፡- ዩኒቨርቲው ስንት ተማሪዎችን ይዟል? ለስንት ሰዎችስ የድል ፈጠረ? በቀጣይስ የቅበላ አቅሙን በማሳደግ ዙሪያ ምን አስቧል?

ፕሮፌሰር ገብሬ የተማሪዎች ቁጥር በስት ዙር ቅበላ የክረምትና የቅዳሜ ጨምሮ 4400 ደርሷል። ከድል አንፃር በቋሚነት ከ200 በላይ መምህራንና 700 ያህል የአስተዳደር ራተኞች አሉ። ከዛ ውጪ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመከፈቱ ጀምሮ ከግንባታ በመነሳት በርካታ ማበራት ተጠቃሚ ሆነዋል። ለ2013 ዓ.ም. 3000 ያህል ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅታችንን አጠናቀናል።

ሪፖርተር፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ላማዎች ምንድናቸው? እስካሁንስ ምን ምን ነገሮችን አከናውኗል?

ፕሮፌሰር ገብሬ– ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ስት ዋና ዋና ላማዎች አሉት። የመጀመርያው መማር ማስተማር ሁለተኛው ምርምር የመጨረሻው የማበረሰብ አገልግሎት ነው። በመማር ማስተማሩ ዙርያ መጀመሪያ ዓመት ላይ ማለትም በ2010 ዓ.ም. 1500 ተማሪ ጠብቀን የመጣልን ግን 1099 ተማሪ ነው። ቅበላውን የጀመርነው በጥር ወር ላይ በመሆኑ ተማሪዎች ሌሎች አማራጮችን ወስደዋል። የተቀሩት ተማሪዎችም ዩኒቨርቲው የመጀመርያ ተማሪዎች በመሆናቸው አርባ ምንጭ ድረስ ሄደን ነበር የተቀበልናቸው። የማበረቡም አቀባበል ደማቅ ነበር። በመቀጠልም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምዝገባ ጀምሮ እስከ ምደባ ድረስ ያለውን ደት ቀላል አድርገናል። እንዲሁም የዲጂታል ላይብረሪ ሥርዓት በመጠቀም ኢንተርኔት ማይፈልግ ስልክን ወይም ኮምፒዩተርን በመጠቀም ተማሪዎች በቀላሉ መጽሐፍ የሚያገኙበትን ዕድል አመቻችተናል። ከዚሁ ከመማር ማስተማር ደት ሳንወጣ ለመምህራን ተጨማሪ ልጠናዎችንለተማሪዎችም አጋዥ ትምህርቶችን በመስጠት ተማሪዎችን በመደገፍ የመባረር ምጣኔውን ለመቀነስ ችለናል። የዩኒቨርሲቲያችን ሁለተኛው ላማ ምርምር ነው። በመጀመሪያ ዓመት መንግት ብር ባለመመደቡ ምክንያት ምርምር መራት አልቻልንም ነበር። ነገር ግን በሁለተኛው ዓመት ገንዘብ ማግኘት በመቻላችን ላሳ አምስት ፕሮፖዛል ቀርቦ ላሳው በማለፋቸው ገንዘብ መድበንላቸው ጥናት አድርገው የጥናቱን ውጤት ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርት መልክ ያቀረቡትንም እንዲያሳትሙ እየተሞከረ ነው። ስተኛ ዓመት ላይም እንዲሁ 67 ፕሮፖዛሎች ቀርበው 47 ተመርጦ ጥናታቸውን በጀመሩበት ወቅት ነው በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠው። ሌላው በምርምር ራ የራነው የተለያዩ ኮንፍረንሶችን ማዘጋጀት ነው። ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከሌላው ዩኒቨርሲቲ ለየት ባለ መልኩ ትምህርት መስጠት ሳንጀምር በፊት ነው ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን ማዘጋጀት የጀመርነው። እስካሁንም በብዝ ግጋትና ዓተ ፆታ ላይ ያጠነጠኑ ለም አቀፍ ኮንፍረንሶችንና ስት የገር ውስጥ ኮንፍረንሶችን አዘጋጅተናል።

ስተኛው የዩኒቨርሲቲያችን ላማ የማበረሰብ አገልግሎት ነው። በዚህ ውስጥም በርካታ ሥራዎችን ርተናል። በመጀመርያ ትኩረት ያደረግነው ትምህርት ላይ ነው። ምን ችግር አለ ብለን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጀምረን በጠየቅን ጊዜ የመጽሐፍ እጥረትና የኮምዩተር አለመኖር በመገንዘባችን ችግሩን ለመቅረፍ ከካማራ ኤድዩኬሽን ኢትዮጵያ ጋር በመነጋገር ወደ 700 ኮምዩተሮችን በመግዛትና ኮምዩተሮች ላይ መጻሕፍትን በመጫን ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች ልጠና ሰጥተን አድለናልን። እነዚ ኮምዩተሮች የታደሉት የጂንካ ማረሚያ ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጨምሮ ለላሳ አራት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ለአንድ ሞዴል ማድረግ ለፈለግነው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። ይህም በትንሹም ቢሆን ከሌሎች የኢትዮጵያ ተማሪዎች ጋር ለመወዳደር ያስችላቸዋል ብለን እናስባለን። ሌላው ለስት አቅመ ደካማ እናትና አባቶች ከተማሪው ጋር በመሆንና ገንዘብ በማዋጣት ቤት ርተን ሰጥተናል። ይ በእርግጥ የሚያኩራራ ሥራ ባይሆንም በቀጣይ ግን መነሳሻ የሚሆን ነው ብለን እናምናለን። በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ላይም እንዲሁ እየተሳተፍን እንገኛለን። ለምሳሌ ያህል በተወሰ መልኩ እየተራቆተ የሚገኘውን ከጂንካ ከተማ አጠገብ ባለው የጎሪጎቻ ተራራ ላይ ማበረሰቡን በማሳተፍ ችግኝ በመትከል ጥበቃ እንዲደረግለት አድርገናል። ለመንግራተኞች አቅም ማጎልበቻ የተለያዩ ልጠናዎችን ሰጥተናል። ከዚህ በተጨማሪ የደቡብ ኦሞ ባህል ፌስቲቫልም ጀምረናል። ለዘንድሮ በኮቪድ-19 ምክንያት ሳይሳካ የቀረው የዚህ ፌስቲቫል ላማ በደቡብ ኦሞ ሉ 16 ብሔረሰቦች ቱባ የሙዚቃ፣ የምግብ እንዲሁም የደ ጥበብ ባህል ስላላቸው እሱን ለተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ማስተዋወቅና የገቢ ምንጭ ማምጣት ነው። በዚህም መረት የመጀመርያው ዙር በጥሩ ሁኔታ ተካሄዷል። ሌላው የኮሮና ቫይረስ በገሪቱ ከተከሰተ በኋላ ዩኒቨርሲቲው ከክልሉ ጤና ኢንስቲትዩት ላራቶሪ ጋር በመተባበር ሳኒታይዘር በማምረት በመጀመርያ ዙር ለተወሰነ ማበረሰብ ክፍል በነፃ ካደልን በላ በቀጣይ ያለ ትርፍ በተመጣጣኝ ዋጋ እያመረትን ማከፋፈል ጀምረናል። በዚህም ባለማቆም ወደ አምስት ሚሊዮን ብር በማውጣት የኮሮና ቫይረስ መመርመያ ማሽኖችን በመግዛትና ለሱ የሚሆኑ ግንባታዎችን በማከናወን ምርመራ ለማድረግ እየተዘጋጀን እንገኛለን። ይንና የመሳሰሉት በማበረሰብ ዙርያ ዩኒቨርሲቲው የራቸው ሥራዎች ናቸው።

ሪፖርተር፡- በመላ ኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት ሁለት መታት የፀጥታ ችግር በሰፊው ተስተውሏል። የዚህ ችግር ሰለባዎችም በተቀዳሚነት ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በነዚህ ጊዜያት ምን ይነት ችግሮች አጋጠሙት? እንዴትስ ተወጣው?

ፕሮፌሰር ገብሬ እውነት ነው። ባለፉት ሁለት መታት ማለትም በለውጡ ጊዜ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ችግር ላይ ነበሩ። የእኛ ዩኒቨርሲቲ ሁለቱን ዓመት ያለ ምንም ኮሽታ አሳልፈናል። ሦስተኛ ዓመት ላይ ግን የተወሰኑ ተማሪዎች ተልኮ ተሰቷቸው ተደራጅተው ነበር የመጡት። አስቀድሞ መረጃ ደርሶን ስለነበረ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርገናል። አንድ ቀን ብቻ አርባ የሚጠጉ ተማሪዎች በመመገቢያ ካፌ ውስጥ ምግብ አንስቶ ያለመብላትና ባነሱት ምግብ ላይ ው የመጨመር አድማ በማድረግ ችግር ለማስነሳት ሞክረዋል። በዩኒቨርሲቲያችን ትልቁ የደረሰው ክስተት የምንለው ይህንን ነው። ለነዚህ ተማሪዎች የምክር አገልግሎት ሰጥተናል። ከነዚህም ውስጥ አራ ሁለት ሚጠጉ ተማሪዎች የአንድ የሁለት ዓመት ገዳ እንዲሁም የማስጠንቀቂያ ቅጣት ተወስዶባቸዋል።

ሪፖርተር፡- ኮሮና በኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ከተወሰዱ ርምጃዎች መካከል አንዱ ዩኒቨርሲቲዎችን መዝጋትና ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ማድረግ ነበር። ተማሪዎቻችሁ ወደቤት ከላካችሁ በኋላ ግንኙነታችሁ ምን ይመስላል?

ፕሮፌሰር ገብሬ ተማሪዎች ወደየቤታቸው መሄድ አለባቸው የሚል መመያ እንደተሰጠ ወያው ተማሪዎችን ወደ ቤታቸው ለመላክ ወሰንን። ነገር ግን ቤተሰብ ወያው ብር አስልከው መሄድ ትንሽ አስቸጋሪ ነበር። በጣም ጥቂት ተማሪዎች በግላቸው ሄዱ። ነገር ግን አብዛኛው ተማሪ መሄድ ስላልቻለ ሰማንያ አውቶሶችን በማዘጋጀት ዩኒቨርሲቲው እንዲያደርሳቸው አድርገናል። በአ ወቅት የመጀመግሪ ተማሪዎች በበሽታው ምክንያት ቤታቸው ሲሆኑ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተሟላ ግንኙነት ኖሯቸው ኦንላይን ትምህርት እያገኙ አይደለም። በኦንላይን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት የማስተርስና የፒኤችዲ ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ሪፖርተር፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለቀጣይ ምን አስቧል?

ፕሮፌሰር ገብሬ የመጀመያው ያለንን አጠናክሮና አሻሽሎ መሄድ ነው። ይህም በላይብረሪ፣ በሬጅስትራር እንዲሁም በመማር ማስተማር የምንሰጠውን አገልግሎት አጠናክረንና አዘምነን መሄድ ነው። ሁለተኛው የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ ነው። ለምሳሌ አሜሪካ ካለ አንድ ተቋም ጋር በመተባበር ለአራ አንድ ዩኒቨርሲቲዎች የአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ለማስገባት ቅድ አለ። ከአራ አንዱ ዩኒቨርሲቲዎች መከልም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው። ስለዚህ አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስን በዩኒቨርሲቲያችን ማስገባት ከቻልን በጣም ትልቁ አብዮት ነው ሚሆነው። ከዚህ በተጨማሪም አምስት የሚሆኑ የልህቀት ማከላት አሉ። ሁሉም ላይ ባይሆንም የተወሰኑት ላይ መራት እንፈልጋለን። አካባቢያችን አርብቶ አደር የበዛበት፣ የእንስሳት ሀብት በብዛት ያለበት በመሆኑ እዛ ላይ መራት እንፈልጋለን። ይም በእንስሳት ሀብት ዙርያ ለገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ሌላው እንደ ልህቀት ማከል ማየት የምንፈልገው ዞኑ የአራ ስድስት ብሔረሰቦች ስብስብ እስከሆነ መጠን ሕብረ ብሔራዊነት ላይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የልህቀት ማከል ይሆናሉ ብለን የምናስባቸው አራቱ የስኳር ፋብሪካዎች ናቸው። ሌላው ደግሞ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ኦሞ በመገኘቱና ደቡብ ኦሞ ከኬንያና ከደቡብ ሱዳን ጋር በመጎራበቱ አጉራዊ ቀናዊ ግንኙነትን ማለትም የኢትዮጵያ ዝቦች ከኬንያ ዝቦች ጋር እንዲሁም ከደብ ሱዳን ዝቦች ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት እንዲጎለብት ያደርጋል የሚል እምነት አለን። ይ ሁሉም ዩኒቨርሲቲ የማይታደለው ለኛ በጓሮአችን ያለ ድል ስለሆነ ከዚህ በላይ ልንራ አስበናል።

ተዛማጅ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች ለማግኘት

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

ተዛማጅ ፅሁፎች

ለቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት የቆመው የብርጋዲየር ጄኔራል ለገሠ ፋውንዴሽን

የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት አባላት ለአገራቸው የሕይወት መስዋዕትን ለመክፈል የወደዱ፣ ለአገራቸው ክብር ዘብ የቆሙና ውለታን የዋሉ ናቸው፡፡ እነኚህ የአገር ጌጦች በአገሪቱ በተከሰተው የሥርዓት ለውጥ...

ገደብና አፈጻጸም የሚሹ የአየር ሙቀት መጠንና የካርቦን ልቀት

የአየር ንብረት ቀውሱን ለመቋቋም የዓለም ከተሞች ከንቲባዎችን የሚያስተሳስረው ቡድን (ግሩፕ) ሲ-40 (C-40) ተብሎ ይታወቃል፡፡ ከተቋሙ ድረ ገጽ መገንዘብ እንደሚቻለው፣ አዲስ አበባን ጨምሮ የ40ዎቹ ከተሞች...

ሕፃናትን ከመስማት ችግር የሚታደገው የቅድመ ምርመራ ጅማሮ

‹‹መስማት ለኢትዮጵያ›› በጎ አድራጎት ማኅበር በጨቅላ ሕፃናት ደረጃ የመስማት ችግር እንዳይከሰትና በሕክምናውም ዙሪያ በዘመኑ ሕክምና መሣሪያዎች በመታገዝ ሕክምና ለመስጠት ሚያዝያ 2014 ዓ.ም. የተመሠረተ ነው፡፡...