Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየትምህርት ሚኒስቴር ድፍን ያለ ‹‹ተማሪዎች ይመዝገቡ›› ውሳኔ  ወላጆችን ግራ አጋብቷል

የትምህርት ሚኒስቴር ድፍን ያለ ‹‹ተማሪዎች ይመዝገቡ›› ውሳኔ  ወላጆችን ግራ አጋብቷል

ቀን:

ትምህርት ሚኒስቴር የቀጣይ ዓመት የትምህርት ምዝገባ እንዲካሄድ ያስቀመጠው አቅጣጫ ግልጽ ባለመሆኑ ወላጆች ግራ መጋባታቸውን ገለጹ፡፡ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመግባቱ ምክንያት በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው የገጽ ለገጽ ትምህርት፣ በ2013 ዓ.ም. በምን መልኩ እንደሚከፈት ግልጽ ያላደረገው ትምህርት ሚኒስቴር፣ በደፈናው ለቀጣዩ ዓመት የትምህርት ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲካሄድ መወሰኑ ብዥታን ፈጥሮብናል ብለዋል፡፡

ወረርሽኙ ሲገባ ትምህርት ፈጽሞ እንዳይቋረጥ በቴሌግራምና በተለያዩ ዘዴዎች ተማሪዎች ትምህርት እንዲቀጥሉ፣ የግል ትምህርት ቤቶች ደግሞ የተማሪ ክፍያን ቀድሞ ሲጠይቁ ከነበረው ከ50 በመቶ እስከ 75 በመቶ ብቻ እንዲያስከፍሉ፣ መክፈል ለማይችሉ ወላጆች በምክክር እገዛ እንዲያደርጉ መመርያ አውጥቶ የነበረ ሲሆን፣ የአሁኑን የምዝገባ ውሳኔ ሲያሳልፍ ስለዚህ ጉዳይ ባለማንሳቱ ከምዝገባ በተጨማሪ የመስከረምን ወይም የመጀመርያውን ሦስት ወራት ክፍያ እንዴት እንደሚያከናውኑ ግራ እንደተጋቡም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የመመዝገቢያና የመጀመርያውን ሦስት ወራት ሙሉ ክፍያ አንዳንዶች ደግሞ የምዝገባና የመስከረምን ወር ብቻ ሙሉ እንዲከፈል እየጠየቁ መሆኑንም ሪፖርተር ከአንዳንድ ወላጆች ባገኘው መረጃ ተገንዝቧል፡፡

- Advertisement -

የሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ በሚኒስቴሩ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ በለጠፉት መግለጫ፣ ምዝገባ ሲካሄድ ቫይረሱን ለመከላከል በዓለም ጤና ድርጅትና በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡ መከላከያዎችን መተግበር እንደሚገባ ቢገልጹም፣ ተማሪዎች በትምህርት ቤት የገጽ ለገጽ ትምህርት የሚጀምሩ ከሆነ አካላዊ ርቀትን እንዴት መተግበር እንደሚቻል አላብራሩም፡፡

በመግለጫቸው በደፈናው አካላዊ ርቀትን ጠብቆ ከማስተማር፣ የንፅህና መጠበቂያዎችን ከማዘጋጀትና መሰል የኮሮና መከላከል ተግባራትን ተግባራዊ ለማድረግ  ቀድመው ዝግጅት የሚደረግባቸው ተግባራት እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ ከጀመሩ አካላዊ ርቀትን መጠበቅና ንክኪን ማስቀረት የማይቻል መሆኑን የሚገልጹት ወላጆች፣ በመማሪያ ቁሳቁስ ልውውጥ ወቅት፣ በላቦራቶሪ እንዲሁም በጨዋታ ሰዓት ተማሪዎችን ተቆጣጥሮ ከንክኪ ማስቀረት ይቻላል የሚለው እንደማያዋጣም ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ወላጆች ግልጽ አይደሉም ብለው ያነሷቸው ሐሳቦች ላይ መልስ ለማግኘት ለወ/ሮ ሐረጓ በተደጋጋሚ ደውለን መልስ ለማግኘት አልቻልንም፡፡ ሆኖም በመግለጫው ትምህርት በምን ዓይነት መልኩ መጀመር እንዳለበት የተለያዩ አማራጮችን ለማመላከት ውይይት እየተደረገበትና ሲጠናቀቅም ይፋ እንደሚሆን አስቀምጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...