Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየባህላዊ ምግቦችን ለማዘመን እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

የባህላዊ ምግቦችን ለማዘመን እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በተመስገን ተጋፋው

የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች ለማዘመንና ለማሳደግ የኢትዮጵያ የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች ማኅበርና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ፡፡  

ስምምነቱ ሐሙስ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም.  ሲደረግ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኮርፖሬት የሰው ሀብት አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዋሲሁን አስረስ እንደገለጹት፣ አገር በቀል የሆኑ የምግብ ባለሙያዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች በማዘመንና በማሳደግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

- Advertisement -

የምግብ ክፍል ዝግጅቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እንዲል በአየር መንገዱ ስር በሚገኙት ፍላይት ኬተሪንግና ካፍቴሪያዎች ላይ በቂ ሥልጠና በመስጠት ተደራሽ ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጅት መጀመራቸውን አቶ ዋሲሁን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ዙሪያ ላይ ከሚሠሩ አገሮች ጋር የልምድ ልውውጥ በመፈጸም የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ለማሳዳግ የሁለትዮሽ ስምምነቱ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረው፣ ይህም ለብዙ የምግብ ባለሙያዎች የሥራ ዕድልን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የምግብ ዝግጅት ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ሔኖክ ዘሪሁን፣ በኢትዮጵያ ያሉትን ባህላዊ ምግቦች ጠብቆ ለማሳደግ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ባህላዊ ምግቦችን በስፋት በማስተዋወቅ ረገድ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት አክለዋል፡፡

የምግብ ዝግጅት ሙያተኞችም በምግብ ዙሪያ በቂ ክህሎትን እንዲያዳብሩ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠትና ከተለያዩ አገሮች ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ በማድረግ ተፎካካሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር እየሠሩ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ባህላዊ ምግቦችን በማቅረብና ለተለያዩ አገሮች በመሸጥ የቱሪዝም ዕድገቱን ለማሳደግ እየተሠራ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንቱ ገልጸው፣ በኢትዮጵያም ምን ያህል የምግብ ግብዓቶች እንዳሉ፣ የምግብ አበሳሰል ሒደቱ እንዴት መሆን እንዳለበት ጥናት ማድረጋቸውን ይኼም ደረጃቸውን የጠበቁ የምግብ አቅርቦቶች እንዲኖር ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ወደፊትም በዘርፉ ላይ አንድ ዕርምጃ ዕድገት እንዲኖረው እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡  

ማኅበሩም ጥራት ያለው የምግብ አቅርቦት እንዲኖርም የምግብ ባለሙያዎችን በማሠልጠን ዘርፍ ላቅ ያለ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሆነ አቶ ሔኖክ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...