Friday, June 21, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ ሌላ ሚኒስትር ስልክ ደወለላቸው

[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሯቸው ገባ]

 • ምንድነው?
 • ምኑ?
 • የሰማነው ነዋ፡፡
 • ምን ሰማህ?
 • መነሳትዎን ነዋ፡፡
 • ከምን?
 • ከሥልጣን ነዋ፡፡
 • ማን ነው ያነሳኝ?
 • ይኸው ዜና ላይ ነው የሰማሁት፡፡
 • ተረጋጋ እንጂ፡፡
 • እንዴት ነው የምረጋጋው ክቡር ሚኒስትር?
 • አልተነሳሁም፡፡
 • የውሸት ነው ዜናው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ላይ ነው ያነበብከው?
 • ፌስቡክ ላይ ነዋ፡፡
 • እሱ እኮ ፌክቡክ ነው የሚባለው ተብሏል፡፡
 • ኧረ ገላገሉኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ለምን?
 • ልቤን ልተፋት ነበር እኮ፡፡
 • ምን ሆነህ?
 • የመነሳትዎን ዜና ስሰማ ነዋ፡፡
 • ለምን?
 • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምነው?
 • እኔ ምን ይውጠኛል?
 • አልገባኝም?
 • በእርስዎ እኮ ነው ያለሁት፡፡
 • እሱማ አውቃለሁ፡፡
 • በዚያ ላይ ስንት ፕሮጀክት ነው እጃችን ላይ ያለው፡፡
 • የምን ፕሮጀክት?
 • ማለቴ በውጭ የምንሠራቸው፡፡
 • እሱማ ልክ ነህ፡፡
 • ይኸው ስልኬ አላቋርጥ አለ እኮ፡፡
 • ማለት?
 • አሁን አጥፍቼው ነው፡፡
 • ለምን?
 • ሰው ሁሉ እየደወለብኝ ነዋ፡፡
 • ምን ብሎ?
 • ምንድነው የምንሰማው ወሬ እያለ ነዋ?
 • ይኼን ያህል?
 • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምነው?
 • በእርስዎ እኮ እንጀራ ያልወጣለት የለም፡፡
 • እንዴት?
 • ለበርካቶች የሥራ ዕድል ፈጥረው ነበራ፡፡
 • መቼም ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው ይላሉ፡፡
 • እንዴት?
 • ደግሞ ለማን የሥራ ዕድል ፈጠርኩ?
 • ለበርካቶች አልኩዎት እኮ፡፡
 • በግልጽ ንገረኛ?
 • ቢያንስ ወሳኝ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል፡፡
 • እኮ ለማን?
 • ለደላሎች!

[ለክቡር ሚኒስትሩ ደላላ ወዳጃቸው ስልክ ደወለላቸው]

 • ምንድነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምኑ?
 • ይኼን አላምንም፡፡
 • ምኑን ነው የማታምነው?
 • የሚሰማውን ወሬ ነዋ፡፡
 • ምን ሰማህ?
 • ከቦታዎት ተነሱ የሚለውን ነዋ፡፡
 • ተሾሙ ማለትህ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እየቀለድኩ አይደለም፡፡
 • እኔስ መቼ ቀለድኩ?
 • ክቡር ሚኒስትር ተው፡፡
 • ምኑን?
 • ይኼን ቀልድ?
 • የምን ቀልድ?
 • ያውቃሉ አይደል እንዴ?
 • ምኑን?
 • ከስንቱ እንደተቀበልኩ ነዋ፡፡
 • ምንድነው የተቀበልከው?
 • ቀብድ ነዋ፡፡
 • የምን ቀብድ ነው?
 • እርስዎን ለማገናኘት ነዋ፡፡
 • ምን ችግር አለው ታዲያ?
 • እንዴት የለውም ክቡር ሚኒስትር?
 • ታገናኛቸዋለህ ብዬ ነዋ፡፡
 • ተነሱ አይደል እንዴ?
 • ሌላ ቦታ ተሹሜያለሁ፡፡
 • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምነው?
 • ከቦታው ከተነሱ ምን ያደርጉልኛል?
 • ተው እንጂ ወዳጄ፡፡
 • ምኑን ልተው?
 • ቢያንስ አብረን ስለሠራናቸው ሥራዎች ብለህ ሞራሌን ጠብቅልኝ፡፡
 • የምን ሞራል?
 • ከቦታው ከተነሱ ምን ያደርጉልኛል ትላለህ እንዴ?
 • እውነቴን ነዋ፡፡
 • ማለት?
 • በሕይወቴ ነው የመጡብኝ፡፡
 • እንዴት?
 • ማን ይለቀኛል ብለው ነው?
 • አልገባኝም?
 • ባለሀብቶቹ ከአሁኑ እያስፈራሩኝ ነው፡፡
 • ምን ብለው?
 • ገንዘባችንን በላህ ብለው ነው፡፡
 • ለምን?
 • እርስዎን ለማገናኘት ቀብድ በልቻለሁ፡፡
 • እንግዲያው አንድ ነገር አድርግ?
 • ምን?
 • መልስ፡፡
 • ምኑን?
 • ቀብዱን!

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ባለሀብት ስልክ ደወለላቸው]

 • ምንድነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምኑ?
 • የሚሰማው ወሬ?
 • የቱ ወሬ?
 • ስለእርስዎ የሚወራው፡፡
 • ምን ተወራ?
 • ከቦታዎት ተነሱ የሚባለው ነዋ፡፡
 • ሌላ ቦታ ልሾም እኮ ነው፡፡
 • ወዴት ወዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምነው?
 • እየቀለዱ መሆን አለበት?
 • የምን ቀልድ ነው?
 • ብዙ ነገር ተነጋግረን ነበር፡፡
 • እሱማ አውቃለሁ፡፡
 • ታዲያ ዝም ብሎ መታጠፍ አለ እንዴ?
 • ምን እያልከኝ ነው?
 • ቢያንስ ፍሬቻ ማሳየት ነበረብዎት፡፡
 • የምን ፍሬቻ ነው?
 • ማለቴ ከቦታው እንደሚነሱ መናገር ነበረብዎት፡፡
 • አልገባኝም?
 • ትልቅ ሥራ ለመሥራት አስበን ነበር እኮ፡፡
 • አውቃለሁ፡፡
 • በዚያ ላይ እኔም ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ነበር ያሰብኩት፡፡
 • ትክክል ነህ ወዳጄ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እርስዎን እንኳን ለማግኘት የከፈልኩትን ዋጋ እኔ ነኝ የማውቀው፡፡
 • እ. . .
 • ከደላላ ጀምሮ የወጣው ወጪ ቀላል አይደለም፡፡
 • ምን ላድርግ?
 • ምን ላድርግ ነው ያሉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • እህሳ፡፡
 • እንደሚነሱ እያወቁ እርስዎ ራስዎ የወሰዱት ገንዘብ ቀላል ነው እንዴ?
 • እ. . .
 • እንደዚህማ አይቀለድብኝም፡፡
 • እኔም እኮ አላወቅኩም ነበር፡፡
 • ቢሆንም ያን ሁሉ ሚሊዮን ብር ሲቀበሉ እኮ ብዙ ነገር ቃል ገብተውልኝ ነበር፡፡
 • ይኼ እኮ ከአቅሜ በላይ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ብዙ ለፍተን እኮ ነው ገንዘቡን ያገኘነው፡፡
 • ቢሳካማ ኖሮ አንተ የበለጠ ሀብታም ትሆን ነበር፡፡
 • አሁን ለማንኛውም ሌላ ጭቅጭቅ አልፈልግም፡፡
 • ማለት?
 • ጥያቄዬ መልሱልኝ ነው፡፡
 • ምኑን?
 • ገንዘቤን!

[ለክቡር ሚኒስትሩ ሌላ ሚኒስትር ስልክ ደወለላቸው]

 • ምንድነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ምኑ?
 • የሚወራው ነዋ፡፡
 • ምን ተወራ ደግሞ?
 • ያልደወለልኝ ሰው የለም እኮ፡፡
 • ማን ደወለልህ?
 • ባለሀብት ቢሉ ደላላ፡፡
 • ምን ብለው?
 • አማልደን ነዋ፡፡
 • የምን ምልጃ?
 • ተበላን እያሉ ነው፡፡
 • ማን ነው የበላቸው?
 • እርስዎ ነዎታ፡፡
 • ምን አድርጌ?
 • አሁን አይደል እንዴ የምሰማው ጉድዎትን?
 • የምን ጉድ ነው?
 • ምን ሲያደርጉ እንደነበር ነዋ?
 • እኔ ከሥራ ውጭ የማውቀው ነገር የለም፡፡
 • ከዝርፊያ ውጭ ማለትዎ ነው?
 • እየተከባበርን፡፡
 • ለማንኛውም ከሰሞኑ ይጀመራል፡፡
 • ምን?
 • ምርመራ ነዋ፡፡
 • በማን ላይ?
 • በእርስዎ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...

ብሔራዊ ባንክ ጥርስ እያወጣ ይሆን እንዴ?

በአመሐ ኃይለ ማርያም ‹‹Better late than never›› (ከቀረ የዘገየ ይሻላል) የኢትዮጵያ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...