Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልኮሮና ያጠላበት የልጃገረዶች በዓል

ኮሮና ያጠላበት የልጃገረዶች በዓል

ቀን:

ያለፉት ዓመታት የነሐሴ ወር አጋማሽ በሰሜንና ሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞች ልዩ ድባብ የሚያለብሳቸው ከተሜዎቹንም ሆነ ከዚያም ውጪ ያለውን ኅብረተሰብ ቀልብ የሚገዙበት አጋጣሚ  ይፈጥርላቸው የነበረው የልጃገረዶች የአደባባይ በዓል ነበር፡፡  ይህም በዓል ከፍልሰታ ለማርያም በዓል ጋር የተያያዘው እንደያካባቢው አጠራር በትግራይ አሸንዳ፣ ዓይኒ ዋሪ፣ ማርያ፣ ዋዒምቦ፣ በአገው ሻደይ፣ በላሊበላ አሸንድዬ፣ በቆቦ ሶለል ይባላል፡፡

ክብረ በዓሉ  ሴቶች ልጃገረዶች በልዕልና የሚታዩበት፣ በነፃነት ነግሠው የሚጫወቱበትም ነው፡፡  ከሕፃን እስከ አዋቂ የበዓሉ መገለጫ በሆኑ አልባሳትና ማጋጊያጫዎች የሚታዩት ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ነው፡፡ ክብረ በዓሉ ጎልቶ የሚታይባቸው ትግራይና አማራ እንደወትሮው ሁሉ ዘንድሮም በተመሳሳይ እንዳያከብሩት ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ገድቧቸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል በዓሉ እንደቀደመው ጊዜ በአደባባይ እንዳይከበር የወሰነ ሲሆን፣ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እንደያካባቢው ትውፊት ለሳምንታት የሚዘልቀውንአሸንዳን በዓል ልጃገረዶች በየቤታቸው ሲያከብሩ ግን ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በመጠበቅ ሊሆን እንደሚገባም ማሳሰቢያ ሰጥቷል።  በዓሉ “ኮሮናን ለመከላከል አሸንዳ በቤታችን በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ታውቋል፡፡

 

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው፣ አሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል የልጃገረዶች ባህላዊ ፌስቲቫልን ለኮሮና በማያገልጥ መልኩ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው።

 “ለጥንቃቄ የምናደርገው መራራቅ የዘላቂ አብሮነታችን መሠረት ነውበሚል መሪ ቃል ከነሐሴ 16 እስከ 21 ቀን 2012 .ም. በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረው የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል ባህላዊ ክዋኔ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በማቅረብ፣ የፓናል ውይይትና ዓውደ ርዕይ በማዘጋጀት ነው፡፡ ችግኝ ተከላና ደም ልገሳም የበዓሉ አካላት ናቸው፡፡

የክብረ በዓሉ ጥንተ ነገር

በክረምት ወቅት ከሚበቅለው ተክል ስሙን የወረሰው በትግራይ አሸንዳ፣ በሰቆጣ ሻደይ (በኸምጣኛ ቋንቋለምለምማለት ነው) በላሊበላ አሸንድዬ፣ በቆቦ ሶለል ሲባል ዓይንዋ ከሚያምረው ወፍ ‹‹ዓይኒ ዋሪ›› ጋር ልጃገረዶቹን በማነፃፀር በዓሉ በአክሱም ይጠራል፡፡

ከነሐሴ አጋማሽ የሚጀምረውና የተለያዩ ስያሜዎች ያሉት ክብረ በዓሉ መነሻው ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተያይዞ የመጣና መጽሐፋዊ መሠረት እንዳለው ይወሳል፡፡ በተለያዩ ጽሑፎች እንደተጠቀሰው ከዘመን መለወጫ፣ አዳምና ሔዋን ከገነት ሲባረሩ ካገለደሙት ቅጠል ‹‹አዳምና ሔዋን ክብራቸውን ተገፈው ከገነት የተባረሩባትን ዕለት በማሰብ በወቅቱ ያገለደሙትን ቅጠል በምልክትነት በመውሰድ የሻደይ ቅጠልን በገመድ ላይ ጎንጉነው በወገባቸው አገልድመው ያስራሉ፤›› ይላል አንድ መጣጥፍ፡፡

በኖኅ ዘመን የጥፋት ውኃ መጉደሉ በወይራ ቅጠል ካበሰረችው ርግብ፣ ከመጥመቁ ቅዱስ ዮሐንስ አንገት መቆረጥ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት (ፍልስታ) እና ከመስፍኑ ዮፍታሔ ልጅ ታሪክ ጋር ያስተሳስሩታል፡፡ ጎልቶ የሚነገረውና የሚተረከው ግን ከቅድስት ማርያም ፍልሰታ በዓል ጋር የተያያዘው ነው።

ከማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች መካከል የሚገኝና ልዩ ልዩ ቁሳዊ መገለጫዎች አሉት፡፡ የፀጉር አሠራሩ ከአልባሶ እስከ ግልብጭ፣ ከጋመ እስከ ድርብ፣ ከደቃቅ እስከ ጉልህና ከሕፃን እስከ አዋቂ ተቆናጅተው የታዩበትም ጭምር ነው፡፡ ከቱባው ባህል ልብስ አንሥቶ ከዘመናዊው ስፌት ከተገኙት ጃርሲ፣ ሽፎን ቀሚስ ጋር ተውበው የሚታዩበትም ነው፡፡

በመቐለ፣ ዓቢይ ዓዲ፣ ሰቆጣ፣ ላሊበላ፣ ቆቦና ሌሎችም የአካባቢው ከተሞች ነሐሴ አጋማሽ ላይ የከተሜውንም ሆነ እንግዳውን ቀልብ የሚስቡበት ባህል ነው፡፡ ልጃገረዶች ሴቶች በነፃነት ነግሠው አደባባይ ወጥተው ይጫወቱበታል፡፡

ነሐሴ 16 ቀን ከሚከበረው የቅድስት ማርያም በዓል ጋር የተያያዘው ክብረ በዓል ከዋዜማው እስከ ማግስት ልጃገረዶች የአሸንዳ ቅጠልን አሸርጠው አደባባይ በመውጣትና በየቤቱ በመዞር እየጨፈሩና እያዜሙ ያከብሩታል፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ የበዓሉ መገለጫ በሆኑ አልባሳትና መጋጊያጫዎች ተውበው ይታዩበታዋል፡፡ የፀጉር አሠራራቸው ከአልባሶ እስከ ግልብጭ፣ ከጋመ እስከ ድርብ፣ ጋሜ፣ ቁንጮ፣ ሳዱላና ቅርድድ ተሠርተው አደባባይ የሚውሉበት ነው፡፡ ጌጣ ጌጣቸውም ልዩ ልዩ ዓይነት ሕንቆ፣ አልቦ፣ ድሪ፣ ድኮት፣ ጉትቻ፣ ማርዳ፣ መስቀል ሲሆን፣ አለባበሳቸውም በመልጉም /ጥልፍ ቀሚስ/ ሹፎን፣ ጃርሲ ይታጀባል፡፡

የአሸንዳ መንፈስ፣ በፀጉር አሠራርና በአልባሳት፣ በመዋቢያ ቁሶችና በመጋጋጪያዎች ብቻ አይደለም የሚገለጠው፣ እርሱን የሚያገዝፉ የሚያጎሉ የተለያዩ ዘፈኖች ይገኙበታል፡፡ 

ለሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት

ከዓመታት በፊት በመቐለው አሸንዳ በክብር እንግድነት ተገኝተው የነበሩት በምህፃሩ ዩኔስኮ ተብሎ የሚጠራው የመንግሥታቱ ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው እንግዳ፣ ዩኔስኮ የሴቶች በዓል የሆነው አሸንዳ አከባበር ልዩ ትርጉም እንደሚኖረው በምክንያትነት ያብራሩት፣ ‹‹የጾታ እኩልነትን ማረጋገጥና የአፍሪካ አኅጉርን መደገፍ ድርጅቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የትኩረት አቅጣጫ በመሆናቸው ነው፤›› በማለት ነበር፡፡

የነሐሴውን ክብረ በዓል የሰው ልጆች ድንቅ የባህል ቅርሶች ወካይ የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንዲቻል ሁለቱም ክልሎች ባለፉት ዓመታት ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርበው በጋራ ሲያስጠኑ ነበር፡፡ የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች የሠሩት ጥናትም ታትሞ መቅረቡ ይታወሳል፡፡

 የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን ለአንድ አገር ቢያንስ በየሁለት ዓመት ልዩነት ውስጥ የሚመዘግበው ዩኔስኮድረ ገጽ እንዳመለከተው እ.ኤ.አ. 2020 በወካይ ቅርስ ፋይሎች ውስጥ ለኅዳር 2013 .. ለውሳኔ ከሚታዩት 42 ፋይሎች ውስጥ ኢትዮጵያ የለችበትም፡፡ በይደር (Backlog) ፋይል (2020) ውስጥ ያለተጨማሪ ሰነዶች ርዕሳቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ ግን እነ አሸንዳ አሉበት፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...