Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅለአዲስ አበባ ሴት ሸክላ ሠሪዎች ማኅበር የተበረከተው ድጋፍ

ለአዲስ አበባ ሴት ሸክላ ሠሪዎች ማኅበር የተበረከተው ድጋፍ

ቀን:

የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ሴት ሸክላ ሠሪዎች ማኅበር የሕፃናት ማቆያ አገልግሎት ማጠናከሪያና ለሴቶች ንፅህና መጠበቂያ የሚውል ድጋፍ አበርክቷል፡፡ ከድጋፉም የሕፃናት ወተት፣ ዳይፐር፣ ሳኒታይዘር፣ ሞዴስ፣ ሳሙናዎችና አልባሳት ይገኙበታል፡፡ የማኅበሩ አባላት ምርታቸውን በሚያመርቱበትና በሚሸጡበት ሥፍራ ተገኝትው ድጋፉን ያስረከቡት የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞት በኢትዮጵያ ሸክላ ሠሪነት ተንቆ መቆየቱን አስታውሰው፣ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ድርሻ እንዲያበረክት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ አክለውም በዚህ የሸክላ ሥራ የተሠማሩ ሴቶችም ሙያቸው ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለአገራቸው መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ ኩራት ሊሰማቸው ይገባል ብለዋል፡፡ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ በበኩላቸው ማዕከሉ በሰኔ 1 መባቻ በአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ተመርቆ መከፈቱንና በአስተዳደሩ ክትትልና ድጋፍ የሚደረግለትም ነው ብለዋል፡፡ ማዕከሉ 350 ያህል ሴቶች ምርታቸውን ለሽያጭ የሚያቀርቡበት ነው፡፡

ለአዲስ አበባ ሴት ሸክላ ሠሪዎች ማኅበር የተበረከተው ድጋፍ

እኔ ፈራሁ

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...