Friday, June 21, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው

[ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን አስጠሩት]

  • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • ና ቁጭ በል፡፡
  • ይቅርታ አስቸኳይ ነው?
  • ተቀመጥ አልኩህ እኮ፡፡
  • ብዙ ሥራ ስላለኝ ብዬ ነው፡፡
  • እኔ ለጨዋታ ነው የምፈልግህ?
  • ሥራ ላይ አልመሰሉኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ማለትህ ነው?
  • አይ ጠረጴዛዋ ላይ የተቀመጠውን ነገር አይቼ ነው፡፡
  • ምን አየህ?
  • ካርታ ነዋ፡፡
  • ታዲያ እኔስ ለምን የጠራሁህ ይመስልሃል?
  • እኔንጃ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንድንጫወት ነዋ፡፡
  • ምን?
  • ካርታ ነዋ፡፡
  • እየቀለዱ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • በዚህ ሰዓት ይቀለዳል?
  • ታዲያ ካርታ እንጫወት ሲሉኝ ነዋ፡፡
  • ምን ችግር አለው?
  • የሥራ ሰዓት ነው ብዬ ነዋ፡፡
  • ለዛ አይደል እንዴ እንጫወት የምልህ?
  • አልገባኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምኑ?
  • ሥራ አለኝ እያልኩዎት እኮ ነው፡፡
  • ዋናው ሥራህ ይኼ ነው እያልኩህ ነው እኔ ደግሞ፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • አልሰማህም እንዴ?
  • ምኑን?
  • ፖለቲካ ቁማር መሆኑን?
  • እ…
  • ፖለቲከኛ ነህ አይደል?
  • አዎ ነኝ፡፡
  • ስለዚህ ስለቁማር ጠንቅቀህ ማወቅ አለብህ፡፡
  • ምን እያሉ ነው?
  • ቢያንስ በቀን ከሦስት ሰዓት በላይ ቁማር መጫወት አለብህ፡፡
  • የእውነትዎትን ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ነገርኩህ እኮ፡፡
  • ምኑን?
  • አሪፍ ፖለቲከኛ መሆን ከፈለክ ቁማር መቻል አለብህ፡፡
  • እኔ እኮ ብዙም አይደለሁም፡፡
  • ምን?
  • ቁማር ነዋ፡፡
  • ከዚህ በኋላ መልመድ አለብህ፡፡
  • ወይ ጣጣ፡፡
  • እንደውም ለሁሉም ሠራተኞች መገዛት አለበት፡፡
  • ምን?
  • ካርታ ነዋ፡፡
  • ለምን?
  • አሪፍ ፖለቲከኞች የምናገኘው አሪፍ ቁማርተኞች ማፍራት ከቻልን ብቻ ነው፡፡
  • ስለዚህ ምን እያሉኝ ነው?
  • አንተን ተጨማሪ ኃላፊነት ልሰጥህ ነው፡፡
  • የምን ኃላፊነት?
  • አዲስ የማቋቁመውን ዲፓርትመንት ኃላፊ እንድትሆን ነው፡፡
  • የምን ዲፓርትመንት ሊያቋቁሙ ነው?
  • የቁማር!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከጸሐፊያቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • ምን ሆነሻል?
  • ጉድ ሆንኩ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ንገሪኛ?
  • ተውኝ ተውኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምንድነው የሚያስለቅስሽ?
  • ጉድ ነው የሆንኩት አልኩዎት እኮ፡፡
  • እንዴት?
  • ሲያቀብጠኝ ነው ተውኝ፡፡
  • ለምን አትነግሪኝም የሆንሽውን?
  • እኔ ሹመት ፈልጌ ነው፡፡
  • የምን ሹመት?
  • አሁንማ ተዋረድኩ፡፡
  • ማን ነው ያዋረደሽ?
  • ያ መናጢ ሾፌርዎት ነዋ፡፡
  • እንዴት?
  • ይኸው እርስዎ በሰጡት አቅጣጫ ሁሉም ጀምሯል፡፡
  • ምን?
  • ቁማር መጫወት፡፡
  • እ…
  • እኔም የሰጡትን አቅጣጫ ከዳር ለማድረስ ሌት ተቀን ነበር የምጫወተው፡፡
  • ምንድነው የምትጫወቺው?
  • ቁማር ነዋ፡፡
  • እሺ፡፡
  • ይኸው ያ መናጢ ጉድ ሠራኝ፡፡
  • ምን አደረገሽ?
  • ደመወዜን ሙሉ በላኝ፡፡
  • እ…
  • አሁን ልጄን ምን ላብላት?
  • ወይ ጣጣ፡፡
  • አታሎኝ እኮ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት?
  • የማላውቀውን ጨዋታ ይዞ መጥቶ ነዋ፡፡
  • ምን?
  • ቀዩዋን ያየ፡፡
  • ወይ ጣጣ፡፡
  • ይኸው ባዶዬን አስቀረኝ፡፡
  • አንቺ የማይገባሽን ጨዋታ ለምን ተጫወትሽ?
  • መጀመርያ እኮ በልቼው ነበር፡፡
  • ከዛስ?
  • አንድ ሁለቴ አስበላኝና ከዛማ ላፈኝ፡፡
  • እ…
  • ምን ላድርግ?
  • ቆይ ተረጋጊ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር እያወቁት፡፡
  • ምኑን?
  • የኑሮ ውድነቱን ነዋ፡፡
  • ማን ተጫወቺ ብሎሽ ነው?
  • ምን ላድርግ ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት?
  • ፖለቲካ ቁማር ነው መባሉን ሰምቼ ነዋ፡፡
  • ታዲያ ሕጉን አታውቂም እንዴ?
  • የምኑን?
  • የቁማሩን ነዋ፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • መብላት እንዳለ…
  • እ…
  • መበላትም አለ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከደላላ ወዳጃቸው ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

  • እዚህ ቢሮ አትምጣ አላልኩህም?
  • ምን ላድርግ ክቡር ሚኒስትር? ጥሩ አይደለም ብዬ ነው፡፡
  • ምኑ?
  • በስልክ ማውራቱ፡፡
  • ለምን?
  • እንዴ ስልካችንን ማን እንደሚጠልፈው ይታወቃል?
  • እሱስ ልክ ነህ፡፡
  • ለዛ ነው የመጣሁት፡፡
  • ምን አዲስ ነገር አለ?
  • ተጧጡፏል፡፡
  • ምኑ?
  • ወረራው ነዋ፡፡
  • የምን ወረራ?
  • የመሬት ወረራው፡፡
  • እ…
  • ያልታጠረውን ቦታ ይጠይቁኝ፡፡
  • አይ አንተ?
  • በዚሁ ከቀጠልን መጠየቅ ሁሉ እንችላለን፡፡
  • ምን?
  • ክልል እንሁን ብለን ነዋ፡፡
  • ቀልደኛ ነህ እኮ አንተ፡፡
  • ያሰማራናቸው ልጆች የሚገርሙ ነበር፡፡
  • እንዴት?
  • አስፋልት ራሱ ሳይቀር አጥረው ነበር፡፡
  • እ…
  • ለነገሩ ወዲያው አስፈረስኳቸው፡፡
  • ሌላ ምን አዲስ አለ?
  • ክቡር ሚኒስትር አንድ ቢዝነስ እንድንከፍት አስቤያለሁ፡፡
  • ምን?
  • ቁማር ቤት፡፡
  • እ…
  • በቃ ፖለቲከኛው ሁሉ ተጫዋች ሆኗል፡፡
  • ምን?
  • ቁማር፡፡
  • አትቀልድ?
  • እኛ አዲስ ነገር ማስተዋወቅ እንችላለን፡፡
  • ምን?
  • ቁማሩን በመሬት ማድረግ እንችላለን፡፡
  • ጥሩ ሐሳብ ነው፡፡
  • አዩ በርካታ ባለሥልጣን መሬት ወረራ ላይ ስላለ አሪፍ ቁማር ቤት ከከፈትን ያዋጣናል፡፡
  • ሳተና ነህ እኮ አንተ፡፡
  • ባይሆን አንድ ነገር ላይ መሥራት ነው ያለብን፡፡
  • ምን ላይ?
  • ቁማር አንድ ነገር እንዲሆን፡፡
  • ምን?
  • ሱስ!

[ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው]

  • እያያችሁ ነው አይደል ክቡር ሚኒስትር?
  • ምኑን?
  • ዝግጅታችንን ነዋ፡፡
  • እኛ ሌላ ሥራ ላይ ነን፡፡
  • ቁማር ላይ ነን ማለትዎ ነው?
  • ስማ እኛ ከእናንተ በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር አለ፡፡
  • ምን?
  • ህዳሴ ግድቡ በል ኮሮና ኧረ ስንት ነገር አለ፡፡
  • እኛ እኮ እዚህ አለቅን፡፡
  • እንዴት?
  • ካሁን ካሁን ትመጣላችሁ ብለን ነዋ፡፡
  • ምን ለማድረግ?
  • ልትወስዱን ነዋ፡፡
  • እሱማ መቼ ይቀራል?
  • እስከዛ በሥጋት አለቅና፡፡
  • እና ምን እያልከኝ ነው?
  • ኑ እና ይለይልና፡፡
  • እየቀለድክ መሆን አለበት፡፡
  • ኧረ የምሬን ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እኛ ከእናንተ ጋር ጦርነት አንገባም፡፡
  • እና አትመጡብንም?
  • እናንተ እስክትመጡ ነው የምንጠብቀው፡፡
  • ምን ልናደርግ ነው የምንመጣው?
  • ልትሰጡ ነዋ፡፡
  • ምን?
  • እጃችሁን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...

ብሔራዊ ባንክ ጥርስ እያወጣ ይሆን እንዴ?

በአመሐ ኃይለ ማርያም ‹‹Better late than never›› (ከቀረ የዘገየ ይሻላል) የኢትዮጵያ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...