Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊለኢትዮጵያ ቆመናል የሚሉ ሁሉ ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ ጥሪ አቀረቡ

ለኢትዮጵያ ቆመናል የሚሉ ሁሉ ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ ቅዱስ ፓትርያርኩ ጥሪ አቀረቡ

ቀን:

ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ቆመናል የሚሉ ሁሉ ልዩነቶችን በውይይት ፈተው የአገሪቱን ሰላም፣ አንድነትና ልማት እንዲያስቀጥሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ነሐሴ 1 ቀን የተጀመረውና ለሁለት ሳምንታት የሚቆየውን  ጾመ ፍልሰታ ለማርያም አስመልክቶ በዋዜማው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ የዚህ ትውልድ ብቻ ሳትሆን ያለፈውም የወደፊቱም ጭምር መሆኗን በማመልከት፣ ችግሮችን በጠረጴዛ ዙርያ ተወያይቶ መፍታትና ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን ብለዋል፡፡

የዘንድሮ ጾመ ማርያም የሚጾመው ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ በሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋ ተከበው ባሉበት ወቅት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ከእነዚህ አደጋዎች ለመውጣት እግዚአብሔርን መፍራትና ንሥሐ መግባት እንደሚያስፈልጋቸው አመልክተዋል።

- Advertisement -

እግዚአብሔርን መፍራት ማለት በምንሠራው ሥራ፤ በምንናገረው ቃል፤ በምናስበውሳብና ምኞት ሁሉ እግዚአብሔር ያውቅብናል፣ ይፈርድብናል፣ ያየናል የሚል አስተሳሰብ በውስጣችን አድሮ ከክፉ ድርጊት መቆጠብ ነው፤ማለት መሆኑን አስረድተዋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑ የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታን ኮቪድ-19 በመከላከል፣ የተቸገሩትን በመርዳት እንዲያሳልፍም ጥሪ በማቅረብም ሕዝቡ ከይቅርታና እርቅ፤ ከሰላምና አንድነት የተሻለ የችግሮች ማሸነፊያም ሆነ ማስወገጃ እንደሌለው መገንዘብ ይገባልም ብለዋል።

በተያያዘም ፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን፣ በጾመ ፍልሰታ መልዕክታቸው፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጣውን የጥንቃቄ መመሪያ በማክበር እንዲከናወን አስገንዝበዋል፡፡ አያይዘውም በኢትዮጵያ ፖለቲካ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተፎካካሪዎችም ባስተላለፉት መልዕክት፣የበለፀገችና የተረጋጋች አገርን መምራት እንድትችሉ መጀመርያ የድሆችን ልብ አሸንፉ፣ አስቀድማችሁ በሕዝብ ልብ ለመንገሥ ጥረት አድርጉ እንጂ ኃይልን፣ ሁከትንና በደልን መሣሪያ አታድርጉ” በማለት አሳስበዋል።

ምዕመኑ በያለበት አገር ሆኖ ስለ ሰላም፣ ስለ ሕዝቦች አንድነትና ስለ ኮቪድ መወገድ እንዲፀልይ ጥሪ ያቀረቡት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ፣ ያለአግባብ ሀብት በመሰብሰብ መበልፀግ በኃይል ሥልጣን ለመያዝ በማሰብ ብጥብጥና ቀውስን ማንገሥ በአምላክ ፊት ኃጢዓት መሆኑን አመልክተዋል።

ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ በተከሰተው አሰቃቂ ደም መፋሰስ የሞቱትን ወገኖች ነፍስ በመንግሥቱ ያሳርፍ፣ ያዘኑትንም ያፅናና ያሉት ካርዲናሉ፣ የወደመውም ንብረት በሁሉም ድጋፍመልሶ እንዲቋቋም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዘረኝነትንና ጥላቻን በኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ወደ ይቅርታና ወደ ኖርንበት ፍቅርና አብሮነት እንመልሰው ሲሉም አሳስበዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...