Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህል“የቆረኑ ጉዞ”

“የቆረኑ ጉዞ”

ቀን:

መሰንበቻውን የወይንሸት በየነ ዘውዴ የቆረኑ ጉዞ ረጅም ልቦለድ ለንባብ በቅቷል፡፡ በአማራና በአፋር ባህል ላይ የሚጠነጥነው ልቦለድ ደራሲዋ በመግቢያው ላይ እንደጠቀሱት፣ ልቦለዱ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ሲሆን ታሪኩ የሚያጠነጥነው ከአዲስ አበባ 245 ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኘው በሰሜን ሸዋ ራሳ በሚባል አካባቢ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት የአብሮነት፣ የመተባበርና የመረዳዳት ባህል ያለው ማኅበረሰብ ነው የሚሉት ደራሲዋ፣ ለዚህ ደግሞ በርካታ የሆኑ መገለጫዎች “ከአበላላችን ጀምሮ ፍቅርን የተላበስን፣ አንደኛችን ያለአንዳችን ምንም የሆንን ኢትዮጵያውያን ነን” በማለት ያሰምሩበታል፡፡

“እኔ ባደግሁበት አካባቢ ነፍስ ካወቅሁበት ጊዜ ጀምሮ የሁለቱ ብሔሮች ግጭት የሚያሳስበኝ አንድነታችንን ማሰብ ስለተሳነን ወንድም ወንድሙን እየገደለ የሚኖርበት በመሆኑ ሁል ጊዜም ይቆጨኛል፡፡ ደማችን አንድ፣ መልካችን አንድ፣ መልክአ ምድራችን አንድ፣ ታዲያ ልዩነታችን እምኑ ላይ ነው? ሁሌም ጥያቄ ይፈጥርብኛል፤” ያሉት ደራሲዋ፣ መጽሐፉን በዋነኛነት ለመጻፍ ያነሳሳቸው “ይህ የወንድማማቾች መገዳደል ቆሞ ፍቅራችንን ለሌላው ዓለም ምሳሌ ሆነን እንድናሳይ ነውና የኢትዮጵያ አምላክ ፍቅርን እንደሸማ ያላብሰን ብያለሁ፤” ብለዋል፡፡

- Advertisement -

ስለ ልቦለዱ ዕይታቸውን ያንፀባረቁት ደራሲት ፀሐይ መልአኩ፣ የኅትመት ውጤቱን “በእውነተኛ ታሪክና ህያው በሆነ የአማራና የአፋር ባህል ላይ የተመሠረተ፣ በውስጥ አዋቂ የተጻፈ ታሪክ፣ በትክክል ዕውቀት የሚያስጨብጥ የሥነ ጽሑፍ ሥራ ነው፤” ብለውታል፡፡ እንደርሳቸው ዳሰሳ፣በአብሮነት ዙሪያ በሚፈጠሩ ሰላማዊ ግንኙነቶች እንዲሁም በአሉታዊ ግጭቶች ወቅት ሁለቱም ማኅበረሰቦች ሰላምና ደስታ የሚያከናውኑበት፣ ችግርና ጉዳታቸውን የሚቆጣጠሩበትና የሚዳኙበት ዘመናት ያስቆጠረ ቱባ ኢትዮጵያዊ ሥርዓታቸው በዚህ መጽሐፍ ታሪክ ውስጥ በጉልህ ይታያል፡፡

የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ማኅበረሰብ፣ ዘመን ላከማቸው የሰከነ የሽምግልና አስተውሎት አክብሮትና ዋጋ እንዳለውና በአገልግሎቱም ማኅበራዊ ቁርኝቱን እንደሚያጠብቅበት ትረካው ያረጋግጣል፡፡ የሚኮራበት የማንነቱ እሴቱ መሆኑን ይመሰክራል፡፡ መነጋገር፣ መደማመጥና ወደ መፍትሔ መራመድ በነጠፈበት በዚህ ዘመን፣ ያ የገጠሩ ባህልና ወግ፣ ሰላምና አንድነት እንዴት እንደሚሠራ፣ የተወሳሰበውን ችግር እንዴት እንደሚፈታ የቆረኑ ጉዞ ጭብጥ ያሳያል ሲሉም አክለውበታል፡፡

የልቦለዱ ገጸ ባህርያት የሚጠቀሙባቸው ቃላት በአካባቢው የሚነገሩ በመሆናቸው፣ አንባቢው ከዘዬዎቹ እንዲተዋወቅ የሚያደርግ በመጨረሻው ገጽ የቃላት መፍቻ ሙዳየ ቃላት ተቀምጦለታል፡፡

የቆረኑ ጉዞ መሸጫ ዋጋ ብር 101.50 ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...