Wednesday, April 17, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የውጭ ኩባንያዎች ገንዘብ ለማሸሽና ወጪ ለማናር በሚፈጥሩት ሐሰተኛ ዋጋ የአገር ውስጥ ነጋዴዎች መቸገራቸውን ገለጹ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በርካታ የውጭ ኩባንያዎች ዋጋን አጋኖ በማቅረብ ከውጭ በሚያስገቧቸው የካፒታል ዕቃዎችና ግዓቶች ላይ የሚጭኗቸው ዋጋዎች በአገር ውስጥ ባለሀብቶችና ነጋዴዎች ላይ ትልቅ ጫና ማሳደራቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡

የዕቃዎችን ዋጋ ሆነ ብሎ በማሳነስና በማናር በሚፈጸሙ ድርጊቶች መቸገራቸውን የገለጹ አስመጪዎች፣ በተለይ የታሪፍ ዋጋቸው ከዜሮ እስከ አምስት በመቶ የሆኑ ዕቃዎችን ጨምሮ ቀረጥ ብዙም የማይከፈልባቸውን የካፒታል ዕቃዎች በማስመጣት ሆነ ብለው የዕቃዎችን ተፈጥሯዊ ዋጋ በማዛባት ሰው ሠራሽ ንረት ሲፈጥሩ ይታያሉ፡፡

ወደ ሌሎች አገሮች ካፒታልን በማዛወርና በሕገወጥ የፋይናንስ ግብይት መልኩ እየወጣ ያለውን ካፒታል በተመለከተ ... 2009 ጀምሮ ሲወጡ የነበሩ ሪፖርቶች የሚያረጋግጡት ክስተቱ አትኩሮትን እየሳበ መምጣቱን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን ቁጥብ የውጭ ምንዛሪ መጠን ይኸው ከፍተኛ የካፒታል ማዛወር ወይም ማሸሽ ተግባር በእጅጉ እየታየባት በመምጣቱ የመነጋገሪያ ዕምብርት እንድትሆን አድርጓታል፡፡

ከዓመታት በፊት ተሻሽለው የወጡ አኃዞች እንደሚያመለክቱት ... 1970 እስከ 2010 በነበሩ 30 ዓመታት 24 ቢሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ እንዲሸሽ መደረጉን ይጠቁማሉ፡፡ ካፒታል በከፍተኛ መጠን እየሸሸ መሆኑ ከተመዘገበባቸው ጊዜያት ትልቁን ድርሻ መያዝ የጀመረው ..አ. 2000 በኋላ ያለው ሲሆን፣ በተለይ 2010 ብቻ 3.5 ቢሊዮን ዶላር በአገሪቱ ኢንቨስት ያደረጉ የውጭ ባለሀብቶች ያሸሹት ገንዘብ ከአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በላይ ሆኖ የተመዘገበበት ጊዜም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር፡፡ መረጃዎች ሲፈተሹ፣ ካለፉት 30 ዓመታት ይልቅ ከፍተኛ የካፒታል ሽሽት የተመዘገበባቸው አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ የጀመረችባቸው ጥቂት ዓመታት ሆነው ይገኛሉ፡፡ ካፒታል የማሸሽ መጠኑ ... 2001 ጀምሮ 2.1 ቢሊዮን ዶላር እየተመነደገ መምጣት ሲጀምር፣ ... 2002 እስከ 2009 እንዲሁም 2010 ጀምሮ እያንዳንዱ ዓመት በዓመት በአማካይ 1.4 ቢሊዮን ዶላር መጠን የመዘገበበት የካፒታል መጠን ከአገሪቱ ወጥቷል፡፡

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የመጨረሻዎቹ አራት ዓመታት እንዲሁም የደርግን የመጨረሻዎቹ አሥር ዓመታት መነሻ ያደረጉ ዘገባዎች ያሳዩትም በእነዚህ ጊዜያት ከተመዘገበው የካፒታል ሽሽት ይልቅ ብልጫ ያለው ገንዘብ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ የተመዘገበው መጠን ነው፡፡ ... 1982 ከአገሪቱ የወጣው ካፒታል 2.8 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡

በቅርብ ጊዜ የወጡ መረጃዎችና የባለሙያዎች ግምቶች ከዚህም የላቀ ቁጥር ያመላክታሉ፡፡ ታዋቂው የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያ እዮብ ተስፋዬ (/) ደጋግመው ሲያነሱ እንደሚደመጠው ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ 35 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ሆኖ ተብሎ ዋጋ በማናር በሚፈጸም ድርጊት አገሪቱንና ሕዝቡን ሲያራቁት ኖሯል፡፡ ይህ አድራጎት አሁንም ብሶበት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥም ሲስፋፋ እንደታየ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ 

ከሌሎች በካፒታል ሽሽት ላይ ከተደረጉ ጥናቶች የተለየ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገሮች የታየው ያለ ደረሰኝ የሚካሄዱ የንግድ ልውውጦች እንዲሁም አብዛኛው የሐዋላ ገቢ በአገሪቱ ኦፊሴላዊ የሒሳብ መዛግብት ውስጥ ተካተው አለመገኘታቸው የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ነው፡፡ ያለደረሰኝ የሚካሄዱ የወጪና ገቢ ንግድ ጉዳቶች ከፍተኛ ድርሻ እየያዙ ሲሆን፣ በተለይ ላኪዎች ሆነ ብለው ከገዙበት ዋጋ በታች ደረሰኝ ማቅረባቸው፣ አስመጪዎችም ከገዙበት ዋጋ በላይ ዋጋውን አንረውና አጋነው ደረሰኝ ማምጣታቸው ከአገሪቱ ለሚያፈተልከው ካፒታል ዓይነተኛው መሣሪያ እንደሆነ በርካታ ሪፖርቶች ሲያመላክቱ ይታያል፡፡

እንዲህ ባለው አዙሪት ተጎጂ እየሆኑ እንደመጡ የሚናገሩ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች፣ ሆነ ተብለው ዋጋቸው በሚዛቡና ከተገዙበት ዋጋ በላይ ከፍተኛ ዋጋ በሚጠየቅባቸው ምርቶች ሳቢያ መሠረታዊ ጉዳቶች በአገርና በነጋዴዎች ላይ እየደረሰ እንደሚገኝ ባለሙያዎችም ጭምር ይናገራሉ፡፡

ከእነዚህ ጉዳቶች አንዱ ከውጭ የሚገባው ዕቃ የሚገዛበት ትክክለኛ ዋጋ ዝቅተኛ ሆኖ ሳለ ከፍተኛ እንደሆነ ተደርጎ ስለሚቀርብ አገሪቱ በተጋነነ ሒሳብ ለሚቀርብላት የወጪ ጥያቄ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለማቅረብ መገደዷ ነው፡፡ ለአብነትም አሥር ዶላር ሊገዛ የሚችለው ዕቃ 100 ዶላር እንደተገዛ ተደርጎ ሊቀርብ መቻሉ ነው፡፡

ሌላኛውና ትልቁ ጉዳት አገር ውስጥ አስመጪዎችና በመንግሥት መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር ማድረጉ ነው፡፡ መንግሥት በተለይም ገቢዎች ሚኒስትርና ጉምሩክ ኮሚሽን፣ በአስመጪዎች መካከል የሚታየውን የዋጋ ልዩነት መነሻ ከማጥናትና በሚገባ ከመርመር ይልቅ፣ አነስተኛው ዋጋ የተሰጠው ሆነ ተብሎ ቀረጥ ላለመክፈል እንደተረገ በመቁጠር፣ በከፍተኛ ዋጋ እንደተገዙ የሚያሳዩ የዕቃ ዝርዝሮችን መነሻ በማድረግ የተዛባ የዋጋ ሥርዓት እንዲፈጠር ሲያደርጉና ሲተባበሩ ይታያሉ፡፡

እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ለዓመታት እየታዩ ቢሆንም፣ በመንግሥት በኩል ተጨባጭ ውጤት የሚያመጡ ዕርምጃ እንዳልተወሰደ የሪፖርተር ምንጮች ይልጻሉ፡፡ በዚህ ሳቢያም አላግባብ የተጋነኑ ዋጋዎች የአገር ውስጥ ገበያውን ሲያናጉትና ለዋጋ ግሽበት መባባስ ምክንያት ሆነው እንደቆዩ ይገለጻል፡፡

የመንግሥት ዓብይ ትኩረት ዋጋ አሳንሰው በሚያቀርቡ ላይ አነጣጥሮ እንደቆየ የሚገልጹ አስተያየት ሰጪዎች፣ ይህ የሚያሳየው መንግሥት በሚሰበስበው ገቢ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉን እንደሆነ ይጠቅሳሉ፡፡ የገዙበትን ትክክለኛ ዋጋ በማቅረባቸው በጉምሩክ ኮሚሽንም ሆነ በገቢዎች ሚኒስቴር ተቀባይነት እያጡ የተቸገሩ አስመጪዎች፣ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ዕልባት እንዲሰጥበት ይጠይቃሉ፡፡ 

ስለ ጉዳዩ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፣ እንዲህ ያለው ጥያቄ ያላቸው አስመጪዎች ጥያቄያቸውን ይዘው ወደ ሚኒስቴሩ እንዲመጡ በመግለጽ ምላሽ ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች