የሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሰውንና የአሜሪካ ብራንድ የሆነውን ሴፍዌይ ሱፐር ማርኬት ብራንድ በመግዛት በሐዋሳ ከተማ፣ በአንድ ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሱፐር ማርኬት በመገንባት አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል፡፡
ለከተማው ትልቅ የተባለው ይህ ሱፐር ማርኬት የአካባቢው ገበሬዎች ምርታቸውን በቀላሉ ለግብይት ማቅረብ የሚችሉበትን መንገድ በመፍጠር በተለይ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይሠሩ ለነበሩ የውጭ ዜጎች ይቸገሩበት የነበረውን ዘመናዊ የሱፐር ማርኬት አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡፡ ሱፐር ማርኬቱ ለ100 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደፈጠረ ለማወቅ ተችሏል፡፡